Ye-buna (የቡና)
1.83K subscribers
113 photos
46 videos
2 files
95 links
የቡና ኮንተንት የሚሰሩ ሰዎች በስጦታ ፣በአባልነት እና በሽያጭ ገንዘብ የሚያገኙበት መድረክ ነው።
ለበለጠ መረጃ https://www.ye-buna.com ይጎብኙ።
Download Telegram
ሊንኩን በመንካት ለጎፋ ሕዝብ የቻላችሁትን አድርጉላቸ👇
https://ye-buna.com/charite_detail?yebuna=66a39cdea5a96_gofafundraise

ከዚህ የከፋ ምን አለ?#ይነበብ

ወዳጆቼ፦ እውነት በአካል በቦታው ሆኖ ማየት ምነኛ ይከብዳል?😭 አስክሬን ተቆፍሮ ተገኝቶ ''እንኳን ደስ አለ/ሽ'' እየተባባሉ እንደማየት...አንድት እናት ''ኤሬሳይ በተኮ ታ የክኬ ባይ (አስክሬኑ ቢገኝ አላለቅስም ነበር)'' ስትል እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ። ''ልጄ ላይ ቆሜ ይሆናል'' የምትል እናትን ማየት ለህልና ይከብዳል። አባት ፡ እህት ፡ ወንድም ፡ አጎት ፡ የአጎት ልጆችን ያጣ ወጣት ልጅ እንደማየት ምን የሚያሳዝን ነገር አለ። አንድ አባት ደግሞ ''ሁለቱ ልጆቼ እዚህ ጋ ቆመው አይቻለሁ ፡ እዚህ ጋ ብትቆፍሩልኝ አገኛቸው ነበር'' እያሉ መስማት ያማል ፤ በእውነት ልብ ይሰብራል። ከሁሉም በላይ ደግም ምንም ማድረግ ሳትችል ስትቀር ''ያማል'' የሚለው ቃል አይገልጸውም። የሟቾቹ ቁጦር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ 260 አልፏል። 'እግዚአብሔር የወደደውን አደረገ' ከማለት ውጭ ምን እላለሁ?