General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ:- ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

የኮሌጁ ሜታል ማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንት የዶሮ ኬጂዎችን እያመረተ ነው!!

የኮሌጁ ሜታል ማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስር ለሚገኙ ወረዳዎች አገልግሎት የሚውል የዶሮ ኬጂዎችን በማምረት ላይ ይገኛል፡፡

ዲፓርትመንቱ እያንዳንዳቸው 50 ዶሮዎችን የሚይዙ 48 ኬጂዎች እና 100 ዶሮዎችን ማስተናገድ የሚችሉ 24 የዶሮ ኪጂዎችን በጥራት አምርቶ ለማስረከብ እየተጋ ነው፡፡

እየተሰሩ ያሉ ኬጂዎች ለእንቅላል ጣይ ዶሮዎች መኖሪያ አገልግሎት  እንደሚውሉ የተገለጸ ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኙ የወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤቶች የከተማ ግብርና ውጤት በሆኑት የሌማት ትሩፋት ስራዎች ላይ አጠናክረው እንዲሰሩ ያግዛል መባሉን ሰምተናል፡፡

ዲፓርትመንቱ ከዚህ በፊት ለከተማይቱ ኮሪደር ልማት አገልግሎት የሚውሉ የኮንቲነር ሱቆችን ጨምሮ የተለያዩ የብረታ ብረት ምርት ውጤቶችን በጥራትና በፍጥነት ሰርቶ አስረክቧል፡፡     

የስልጠና ዘርፉ በኮሌጁ በአካባቢያዊ የመልማት ፀጋ ልየታም ከተመሩጡ 5 ዲፓርትመንቶች መካከል አንዱ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ 

   ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
አርብ:- ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

ኮሌጁ የተቋሙን የውሃ ፍላጎት ምላሽ የሰጠ የከርሰ ምድር ውሃ አስቆፈረ!!

  ለኮሌጁ የውሃ እጥረት  ሙሉ በሙሉ ምላሽ የሚሰጥና ለአካባቢውም ማህበረሰብ መትረፍ የሚችል የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮው ተጠናቆ በዛሬ ዕለት ውሃው መውጣት ጀምሯል፡፡

ቁፋሮው በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት የተደረገ ሲሆን 282 ሜትር ወይም ከሩብ ኪሎ ሜትር በላይ ጥልቀት እንዲኖረው ተደርጓል፡፡

ጉድጓዱ ዲስቻርጅ የማድረግ አቅሙ ሲገመት በሰከንድ ከ10 ሊትር በላይ ውሃ መስጠት እንደሚችልም ተነግሯል፡፡

በዘርፉ ባለሙያዎች የላብራቶሬ ትንተና ተሰጥቶበት እና ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራዎች ተከናውነውለት በቅርብ ጊዜ በሙሉ አቅም ወደ አገልግሎት ይገባል መባሉን ሰምተናል፡፡

በተያያዘ የውሃ ዜና የኮሌጁ የፕላምቢንግ ሙያ አሰልጣኞች ወደ 3 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የግቢውን አጠቃላይ የውሃ መስመር ሙሉ በሙሉ በአዲስና አሁን ላይ በሚገኝው የውሃ መስመር ቴክኖሎጂ /ከብረት ወደ ፕላስቲክ/ በመቀየር የውሃ ስርጭት መጠንና ጥራት እንዲሻሻል አድርገዋል፡፡
 
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ማክሰኞ:- ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በዲጂታላዜሽንና በኢትዮ ኢንኮዲስ ስልጠና ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተደረገ!!

በተቋሙ እየተከናወነ ያለውን የዲጂታላዜሽን የትግበራ ጉዞ እና በኢትዮ ኢንኮዲስ ስልጠና ሂደት ዙሪያ ለኮሌጁ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ።

በመድረኩ ላይ ተቋሙን ለማዘመን የተተገበሩ የዲጂታላይዜሽን ስራዎች ተነስተዋል።

ከዚህ ባሻገር ከአይ ሲ ቲ የሙያ ዘርፎች ጋር የተያያዙ እና እንደ ሀገር ለ5 ሚሊዮን ዜጎች የስልጠና ዕድል የተመቻቹ 4 ሙያዎች ላይ ሁሉም ሰራተኞችና ሰልጣኞች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምቹ ሁኔታ በማመቻቸት ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

ስልጠናዎቹ በበየነ መረብ እየተሰጡ ሲሆን ሙያዎቹም ዳታ ሳይንስ ፋንዳሜንታል፣ አንድሮይድ ደቨሎፐር ፋንዳሜንታል፣ ፕሮግራሚንግ ፋንዳሜንታል እና አርቲፊሻል ኢንቴሌጀንት ፋንዳሜንታል ናቸው።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ማክሰኞ:- ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ∙ም

ፋዊ ስለስልጠና ድጋፍ ፕሮግራሙ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ!!

የአፍሪካ ሴት የትምህርት ባለሙያዎች ፎረም /FAWE/ ከማስተር ካርድ ፋውንደሽን ጋር በመተባበር ስለሚያደርገው የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ ፕሮግራም ይዘት ዙሪያ በዛሬ ዕለት ከባለ ድርሻ አካላት በኮሌጁ ውይይት አካሂዷል።

በዕለቱ የፋዊ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅና የድርጅቱ ሰራተኞች፣ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የትምህርት ቢሮ ተሳታፊዎች፣ በአዲስ ከተማና በልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ርዕሳነ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ከልዩ ልዩ ድርጅቶች ጥሪ የተደረገላቸው ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

ፋዌ ኢትዮጵያ ቻፕተር እና ፋዌ አፍሪካ ከማስተር ካርድ ፋውንደሽን ጋር በመተባበር የሃርድ ስኪል ስልጠና ለሚከታተሉ ሰልጣኞች የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲትሆኑ እያደረገ ይገኛል፡፡

እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሮጀክቱ የተተገበርባቸው ጀነራል ዊንጌት እና አዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ሲሆኑ በሁለቱ ተቋማት እየሰለጠኑ ለሚገኙ ሰልጣኞች የተለያዩ ድጋፎችን እየሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

የዛሬው መድረክ ዓላማ ባለ ድርሻ አካላቱ ስለቴክኒክና ሙያ ስልጠና በቂ ግንዛቤ ኖሯው ወደ ዘርፉ ለሚቀላቀሉ ሰልጣኞች የማስተዋወቅ ስራ እንዲያካሂዱ ለማድረግ ነው ተብሏል።

ፕሮግራሙ 80 ከመቶ ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከ5 እስከ 10 ፐርሰንት ለአካል ጉዳተኛ ከ10 እስከ 15 ፐርሰንቱ ደግሞ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ዜጎች ዕድል መስጠቱ ታውቋል፡፡

የፕሮጀክቱ ትግበራ ሰባት ዓመት ቆይታ ሲኖረው የመጀመሪያው ዓመት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"