General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ:- መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በኮሌጁ አሰልጣኞች የተሰራ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ቀረበ!!

ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በቡድን የሰሩ አሰልጣኞች የጥናት ውጤት ሰነዳቸውን በትናንትናው ዕለት ለውውድር አቀረቡ።

በዚህ ውድድር 5 የጥናትና ምርምር ሰነዶች ለባለሙያዎች ቀርበው ምዘና የተደረገባቸው ሲሆን በሁሉም ዘርፎች የተሰሩ የምርምር ተግባራት የኮሌጁን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ይረዳሉ ተብሏል።

የተግባራዊ ጥናትና ምርምሩ ዓላማ እንደ ተቋም የራስን ችግር በራስ አቅም ለመፍታት ያቀደ ሲሆን ሁሉም ጥናቶች የተነሱበትን ክፍተቶች ለመሙላት የሚችሉ ናቸው ተብሏል።

በውድድሩ ርዕሰ ጉዳዩ አንገብጋቢ ችግር መሆኑ፣ ከችግሩ ጋር የተሰናሰለ ዓላማ መቀረጹ፣ ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ርቀት፣ በምርምር ሂደቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ወዘተ የሚሉ መስፈርቶች ተካተዋል።

እንደ ተቋም 9 ተግባራዊ ጥናትና ምርምር እየተሰራ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለግምገማ የቀረቡት 5ቱ ናቸው።

አሸናፊው ሰነድ እንደ ከተማ በቴክኒክና ሙያ ሳምንት ከአቻ ተቋማት ስራ ጋር ውድድር የሚጠብቀው ሲሆን ባለፈው ዓመት በኮሌጁ የተሰራው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በከተማ ደረጃ አንደኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ አይዘነጋም፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ኮሌጁ ከአዳስ ሚዲያ ኔትወርክ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ጋር በመተባበር በየሳምንቱ ቅዳሜ በአንድ ገፅ አምድ ላይ ልዩ ልዩ ሳምንታዊ መረጃዎችን የሚያሰራጭ ሲሆን የዛሬዋ መጋቢት 20 ዕትም ላይ ደግሞ በተቋሙ የሚተገበሩ የዲጂታላዜሽን ስርዓተ ትግበራ ጋር የተያያዘ መረጃን በ19ኛው ገጿ ላይ  ሀተታ ይዛ ወጥታለች።

     መልካም ንባብ!!
ቅዳሜ:- መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም

              "ኢድ ሙባረክ''

ለኮሌጃችን የእስልምና እምነት ተከታይ ሰራተኞች፣ ሰልጣኞች እና አጋሮቻችን በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የበጎነት ይሆንላችሁ ዘንድ እንመኛለን።

   የጀነራል  ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ረቡዕ:- መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም

በክላስተር ደረጃ የክህሎት ውድድር ተካሄደ!!

በክላስተር ደረጃ የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተካሄደ።

እንደ ሀገር ለ4ኛ እንደ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ የሚካሄደው የዘንድሮው የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር "ብሩህ አዕምሮዎች፣ በክህሎት የበቁ ዜጎች!" በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

እንደ ክላስተር በ14 ሙያዎች የክህሎት ውድድር የተደረገ ሲሆን ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ12 የመወዳደሪያ መስኮች ላይ 12 ሰልጣኞችን አሳፏል፡፡ አብዛኛዎቹ ውድድሮች በኮሌጁ የተደረጉ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ በዊንጌት ክላስተር ስር በሚገኙ ኮሌጆች ነው፡፡

የክህሎት ውድድር የተደረገባቸው ዲፓርንመንቶች ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሪክሲቲና ኤሌክትሮኒክስ፣ ቴክስታይል ሌዘር ጋርመንት፣ ሜታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ሆቴልና ሆስፒታሊቲ እና ውድ ወርክ ቴክኖሎጂ ሲሆኑ በውድድሩ ተሳታፊ የሆኑት በኮሌጅ ደረጃ በነበረው ፋክክር በየዘርፉ ቀዳሚ የነበሩት ናቸው፡፡

በኮሌጅ ደረጃ ውድድር የተደረገው ከሁለት ሳምንት በፊት ሲሆን በዚህ ዓመት የአሰልጣኞች እና የአንቀሳቃሾች ክህሎት ውድድር እንደማይደረግ መግለፃችን ይታውቋል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ማክሰኞ:- መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

በክላስተር ደረጃ የአሰልጣኞች ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ተካሄደ!!

በክላስተር ደረጃ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር  የሰሩ  አሰልጣኞች የጥናት ውጤት ሰነዳቸውን በትናንትናው ዕለት ለውውድር አቀረቡ።

በዚህ ውድድር 3  የጥናትና ምርምር ሰነዶች ለባለሙያዎች ቀርበው ምዘና የተደረገባቸው ሲሆን በጀነራል ዊንጌት ክላስተር ስር ያሉ ኮሌጆች ከየተቋማቸው የመጀመሪያ ደረጃ ውጤት ያገኙ ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የተግባራዊ ጥናትና ምርምሩ ዓላማ እንደ ተቋም የራስን ችግር በራስ አቅም ለመፍታት ያቀደ ሲሆን ሁሉም ጥናቶች የተነሱበትን ክፍተቶች ለመሙላት የሚችሉ ናቸው ተብሏል።

በውድድሩ ርዕሰ ጉዳዩ አንገብጋቢ ችግር መሆኑ፣ ከችግሩ ጋር የተሰናሰለ ዓላማ መቀረጹ፣ ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ርቀት፣ በምርምር ሂደቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ወዘተ የሚሉ መስፈርቶች ተካተዋል።  እንደ ክላስተር ከ3ቱ አሸናፊው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በከተማ ደረጃ ለሚደረገው ውድድር የሚቀርብ ሲሆን በዚህ ውድድር በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞች የተሰራው ቀዳሚውን አጠናቋል፡፡ 

መጨረሻ ዓመት ላይ በሚሰሯቸው ፕሮጀክቶች እና ድህረ ልምምዶች ላይ የሰልጣኞችን ልል ክህሎት  እንዲት ማሳደግ ይቻላል? በሚለው ወቅታዊ  ርዕስ ላይ የተሰራው የኮሌጁ የጥናት ሰነድ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ባለፈው ዓመት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  የተሰራው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በከተማ ደረጃ አንደኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ አይዘነጋም፡፡ 

   "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ሐሙስ፡ - ሚያዚያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

ማስታወቂያ

ለኮሌጁ ማህበረሰብ በሙሉ

የወደቁትን አንሱ የነደያን በጎ አድራጎት ማህበር ጧሪና ቀባሪ የሌላቸውን አዛውንቶች፣ የአዕምሮ ህሙማን እና አሳዳጊ የሌላቸው ልጆችን እየሰበሰበ ከሚንከባከቡ ጥቂት ድርጅቶች አንዱ ነው፡፡

ይህንን ሰብዓዊ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ደግሞ ከማህበረሰሰቡ፣ ከድርጅቶችና ከተለያዩ ለጋሽ አካላት በማሰባሰብ ነው፡፡

ስለሆነም ወድ የኮሌጃችን ማህበረሰብ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ማህበሩ እገዛ የሚሆን ሁለችንም በምንችለው አበርክቷችንን እናድርግ እያለን ይኸውም ተሰብስበው የሚሰጡ ስጦታዎች በጥሬ ገንዘብና በቁሳቁስ /በአልባሳት/ ነው፡፡

ስለሆነም አገልግሎት የሚሰጡና በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ አካላት ሊሆኑ የሚችሉ አልባሳትን እና በጥሬ ገንዘብ የበኩላችሁን ድጋፍ እንድታደርጉ እየገለጽን የበጎነት ስጦታችሁን በኮሌጁ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮና በቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲን ቢሮ ማድረስ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡

ሌላም መንገድ አለ የኮሌጁ ሰራተኞች ለሆናችሁ ደግሞ ከሚያዚያ 6 ቀን እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ያለውን የምሳ ድጎማ ኩፖን ለድጋፉ ይዋልልኝ ካላችሁ ካፌ ሄዳችሁ ማሳወቅ ትችላላችሁ፡፡

ድጋፋችንን ለሚሹ አካላት በምንችለው ስናበረክት በውስጣችን የሚታተመው የበጎነት ደስታና የመንፈስ እርካታ እጅግ የላቀ ነው፡፡

የኮሌጁ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ