General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ቅዲሜ፡- የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም

ለኮሌጃችን ሰራተኞች፣ ሰልጣኞች እና አጋሮቻችን በሙሉ እንኳን ለ129ኛው የአደዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

አደዋ በመሰዋትነት የተገኘ አክሊል፣ የአንድነት ህብር ገጽታ፣ የክብር ተራራ ከፍታ፣ የጥቁር ህዝቦች ኩራት፣ የንጋት ብርሃን ወገግታ፣ የታሪክ እንቁ ማህደር፣ የአሸናፊነት ኃይል ጥግ፣ የነፃነት መጎናፀፊያ ዳር፣ የሀበሻ ጀብዱ ሀቅ ዘመን ተሻጋሪ ድል ነው፡፡

በዓሉ  የሰላም፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የበጎነት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

    "በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ሐሙስ:- የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

ከኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ውይይት ጋር ተደረገ!!  

በኮሌጅ የቴክኖሎጂ ልማትና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ ድጋፍ ከሚደረግላቸው የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ጋር ውይይት ተደረገ፡፡  

የውይይት መድረኩ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስር ከሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ጋር ሲሆን በዕለቱ በአዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ድጋፍ የሚደረግላቸው ጭምር ተገኝተዋል።

የውይይቱ ዓላማ የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በክህሎት እና በፈጠራ ስራ የዳበሩ በስራቸውም ውጤታማ ሆነው እንዲቀጥሉ ማስቻል ነው ተብሏል።

በመድረኩ ላይ በአራቱ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አግባቦች መሠረት ለኢንተርፕራይዞች ሲሰጥ የቆየው ድጋፍ ላይ የታዩ እምርታዊ ለውጦችና የተስተዋሉ ክፍተቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

እኛ ጋር ያለው ትልቁ አቅም ሙያ ነው፤ ይህንን ደግሞ ተቋሙ ሳይሰስትና ሳይሰለች እናንተን ለመደገፍ ይሰራል በእናንተ በኩል ያለው ተነሳሽነትና ፍላጎት የበለጠ ሊዳብር ይገባል ያሉት የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ናቸው።

መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ ሲሆኑ የኮሌጁን የድጋፍ ሁኔታ ሪፓርት ያቀረቡት ደግሞ የዘርፉ ም/ዲን አቶ ደሜ መርሻ ናቸው።

የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾቹ በጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲደረግላቸው የቆየው ድጋፍ ለስራቸው ከፍተኛ ለውጥ እንዳስገኘላቸው በምስጋና ገልፀው ቢስተካከል የሚሉትን ገንቢ ሀሳብ ጠቁመዋል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
አርብ:- የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

           በኮሌጅ ደረጃ የክህሎት ውድድር ተካሄደ!!

በኮሌጅ ደረጃ የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተካሄደ።

እንደ ሀገር ለ4ኛ እንደ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ የሚካሄደው የዘንድሮው የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር " ብሩህ አዕምሮዎች፣ በክህሎት የበቁ ዜጎች!" በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

እንደ ኮሌጅ የክህሎት ውድድር የተደረገባቸው ዲፓርንመንቶች ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሪክሲቲና ኤሌክትሮኒክስ፣ ቴክስታይል ሌዘር ጋርመንት፣ ሜታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ሆቴልና ሆስፒታሊቲ እና ውድ ወርክ ቴክኖሎጂ ናቸው፡፡

በዚህ ውድድር 42  ሰልጣኞች በ13 ሙያዎች በኮሌጅ ደረጃ የክህሎት ውድድር ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ከሁሉም ዘርፎች 1ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ ተወዳዳሪዎች ቀጣይ በክላስተር ደረጃ በሚደረገው ውድድር ይካፈላሉ፡፡
 
በዚህ ዓመት የአሰልጣኞች እና አንቀሳቃሾች ክህሎት ውድድር እንደማይደረግ ታውቋል፡፡
       
         "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
To All 2017 Graduating Trainees

First of all, congratulations to all 2017 graduating trainees! We are pleased to announce that the training period for this year is coming to an end, and the graduation day is approaching. Therefore, the Trainee Council has made various plans to enhance the graduation atmosphere. One of our main plans is to create GC (Graduation Class) T-shirts for the graduating trainees.

Therefore, all graduating trainees who wish to order a T-shirt are requested to deposit the payment into the bank account from today, Monday, July 1, 2017, to July 7, 2017. Bring the bank deposit slip to the Council office to register your T-shirt size and name. Price: 450 Birr, Bank Account: Commercial Bank of Ethiopia 1000667783554 Yisak Seifu & Elias Mulugeta & Dibora Kiflu

For more information, please call: 0904738226 or 0985265461.
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ለ2017 ዓ.ም እጩ ተመራቂ ሰልጣኞች በሙሉ

በቅድሚያ የ2017 ዓ.ም እጩ ተመራቂ ሰልጣኞች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን የዘንድሮ አመት የስልጠና ጊዜ እየተገባደደ እንዲሁም የምርቃት ቀን እየተቃረበ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም የምርቃት ድባቡን ለማምጣት በሰልጣኝ ካውንስል የተለያዩ እቅዶች ተይዘዋል። ከነዚህም አንዱ ለተመራቂ ሰልጣኞች የGC ቲሸርት ማሰራት ዋነኛው እቅዳችን ነው።

ስለዚህ ተመራቂ ሰልጣኞች በሙሉ ቲሸርት ማሰራት የምትፈልጉ ሰልጣኞች ከዛሬ ሰኞ 1/07/2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ 7 / 7 /2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ብሩን በባንክ አስገብታችሁ ደረሰኙን በመያዝ ካውንስል ቢሮ መጥታችሁ የ ቲሸርት ልኬታችሁን እና ስማችሁን እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን ።

የአንድ ቲሸርት ዋጋ 450 ብር ብቻ ሲሆን የባንክ አካውንት : የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000667783554 Yisak Seifu & Elias Mulugeta & Dibora Kiflu

ለበለጠ መረጃ : በ0904738226 ወይም 0985265461 ላይ መደወል ይችላሉ።