ሰኞ:- የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ∙ም
በመሰረተ ልማት ግንባታ የአሰልጣኞች ትሩፋት እንደ ቀጠለ ነው፡፡
የኮሌጁን ተቋማዊ ገጽታ ሳቢና ምቹ ለማድረግ በርካታ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን አሁንም አሻራን በታሪክ ሰነድ ውስጥ ለማስቀመጥ የሚደረገው መታተር እንደ ቀጠለ ይገኛል፡፡
በህንፃና ቢሮ ዕድሳት፣ በእግረኛ መንገድ ስራ፣ በፋውንቴን ስራዎች፣ በከርቭ ስቶን ስራና በመሳሰሉት እንቅስቃሴዎች ላይ የኮንስትራክሽን ዘርፍ አሰልጣኞች ያበረከቱት አስተዋጽኦ የአንበሳውን ድርሻ ይጋራሉ፡፡
በዛሬው ቅኝታችን ደግሞ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰልጣኝ በሚስተናገድባቸውና በርካታ ወርክሾፖች በሚገኝባቸው በተለምዷዊ አጠራር ገርጂ በሚባለው አካባቢ የእግረኛ መንገድ ግንባታና ፋውንቴን ስራዎች ላይ እየተጉ የሚገኙ አሰልጣኞችን ተመልክተናል፡፡
ይህ አካባቢ ብዙ የስልጠና እንቅስቃሴ መኖሩ ብቻ ሳይሆን በኮሌጁ የኮሌጁ ሦስተኛ በር የሚገኝበት እና ዘመናዊ ሆኖ የተሰራው አዲሱ የካፊና ሬስቶራንት አዳራሽ ያለበት ነው፡፡
በዚህ የእግረኛ መንገድ ግንባታ ላይ ሶፎንያስ ከድርና መለሰ ምንውየለት ከሺፈራው ካባና ትዛዙ ተረፈ ጋር በመተባበር 300 ሜትር ርዝመት ያለውን መንገድ ከ2 ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ሰርተው ለተጠቃሚው ክፍት አድርገዋል፡፡
ይህ ስራ በ2.5 ሜትር ስፋት የተገነባ ሲሆን አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ተደርጎ የተከናውነ ልማት ነው፡፡ የዚህ ስራ መከናወን የ3ኛ በር አገልግሎትን በጥሩ ሁኔታ ማሳለጥ የሚችል መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በሌሎች አሰልጣኞች እየተሰሩ ያሉ ተቋማዊ ስራዎችን በቀጣይ የምንዘግብ ሲሆን በባለቤትነት ስሜት እየተጋችሁ ያላችሁ ባለሙያዎችን በርቱልን ማለት እንወዳለን፡፡
. "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

ቅዳሜ:- የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ∙ም
ኮሌጁ በISO ትግበራ ለ2ኛ ዙር በተደገው ምዘና የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገቡ እንኳን ደስ አላችሁ ተብላችኋል!!
ይህ የተባለው በኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የኮሌጁ የመጀመሪያ ዓመት የISO ትግበራ ሰርቪላንስ ኦዲት ግምገማ ውጤት ይፋ በተደረበት ዕለት ነው፡፡
ኮሌጁ በጥራት አመራር ስርዓት በማለፍ እንደ ሀገር በISO ሰርቲፋይድ የሆነ የመጀመሪያው የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ሆኖ የተመዘገበው የዛሬ ዓመት ሲሆን ከአንድ ዓመት ቆይታ በኃላ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል የሚለውን ለማረጋገጥ በኢትዮጵያ የተስማሚነት ድርጅት የ3 ቀናት ምልከታ ተደርጓል፡፡
በዚህም ምርመራ ምንም ግኝት የሌለው ብቻ ሳይሆን በየጊዜው የሚታዩ ለውጦች አስደማሚ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ በተለይ በሰራተኛው ላይ የሚታየው የስራ ተነሳሽነትና በራስ የመተማመን ብቃት መጎልበቱ እንዲሁም የደንበኞች እርካታ በማደጉ አሁን ላይ የአዳዲስ ሰልጣኞች ፍላጎት ቁጥር መጨመር እምርታዊ ዕድገት ነው ተብሏል፡፡ ምቹ የስልጠና አካባቢ መፈጠር መቻሉም እንዲሁ፡፡
የሰርቪላንስ ኦዲቱ አካዳሚክና አዲሚኒስትሬትቭ ስታፉን በናሙና ምልከታ የተደረገ ሲሆን ከየካቲት 11 እስከ የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ቆይታ ነበረው፡፡
በመጨረሻም ባለሙያዎቹ ያሉ ውጫዊ ዕድሎችንና የውስጥ ጥንካሬዎችን በማቀናጅት እየተተገበሩ ያሉ ተከታታይ ለውጦችን ማስቀጠል ይኖርባችኋል የሚል ምክረ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡
ሰርቪላንስ ኦዲት ማለት ተቋማት በISO ሰርቲፋድ ከተደረጉ በኋላ እስከ ሶስት ዓመት ድረስ ያላቸውን ብቃት በየዓመቱ የሚመረመርበት ሂደት ነው።
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"