General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሰኞ:- የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ∙ም

   በመሰረተ ልማት ግንባታ የአሰልጣኞች ትሩፋት እንደ ቀጠለ ነው፡፡

የኮሌጁን ተቋማዊ ገጽታ ሳቢና ምቹ ለማድረግ በርካታ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን አሁንም አሻራን በታሪክ ሰነድ ውስጥ ለማስቀመጥ የሚደረገው መታተር እንደ ቀጠለ ይገኛል፡፡

በህንፃና ቢሮ ዕድሳት፣ በእግረኛ መንገድ ስራ፣ በፋውንቴን ስራዎች፣ በከርቭ ስቶን ስራና በመሳሰሉት እንቅስቃሴዎች ላይ የኮንስትራክሽን ዘርፍ አሰልጣኞች ያበረከቱት አስተዋጽኦ የአንበሳውን ድርሻ ይጋራሉ፡፡

በዛሬው ቅኝታችን ደግሞ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰልጣኝ በሚስተናገድባቸውና በርካታ ወርክሾፖች በሚገኝባቸው በተለምዷዊ አጠራር ገርጂ በሚባለው አካባቢ የእግረኛ መንገድ ግንባታና ፋውንቴን ስራዎች ላይ እየተጉ የሚገኙ አሰልጣኞችን ተመልክተናል፡፡

ይህ አካባቢ ብዙ የስልጠና እንቅስቃሴ መኖሩ ብቻ ሳይሆን በኮሌጁ የኮሌጁ ሦስተኛ በር የሚገኝበት እና  ዘመናዊ ሆኖ የተሰራው አዲሱ የካፊና ሬስቶራንት አዳራሽ ያለበት ነው፡፡

በዚህ የእግረኛ መንገድ ግንባታ ላይ ሶፎንያስ ከድርና መለሰ ምንውየለት ከሺፈራው ካባና ትዛዙ ተረፈ ጋር በመተባበር 300 ሜትር ርዝመት ያለውን መንገድ ከ2 ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ሰርተው ለተጠቃሚው ክፍት አድርገዋል፡፡

ይህ ስራ በ2.5 ሜትር ስፋት የተገነባ ሲሆን አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ተደርጎ የተከናውነ ልማት ነው፡፡ የዚህ ስራ መከናወን የ3ኛ በር አገልግሎትን በጥሩ ሁኔታ ማሳለጥ የሚችል መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በሌሎች አሰልጣኞች እየተሰሩ ያሉ ተቋማዊ ስራዎችን በቀጣይ የምንዘግብ ሲሆን በባለቤትነት ስሜት እየተጋችሁ ያላችሁ ባለሙያዎችን   በርቱልን ማለት እንወዳለን፡፡

. "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"