General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ፡- ህዳር 27 ቀን 2017 ዓ.ም

በፋይናንስ፣ በጀት እና ንብረት አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!!

በፋይናንስ፣ በጀት እና ንብረት አጠቃቀም ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ በመጡ ባለሙያዎች ለኮሌጁ ሰራተኞች ተሰጠ፡፡

በዚህም የንብረትና ጠቅላላ አገልገሎት፣ የመንግስት ግዢ አስተዳደር፣ የፋይናንስ፣ የውስጥ ኦዲት፣ የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ፣ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች ባለሙያዎች እና የወርክ ሾፕ ቴክኒሻኖች እንዲሁም ለእነዚህ ዘርፎች አጋዥ እንዲሆኑ የተዋቀሩ ልዩ ልዩ የኮሚቴ አባላትን ጨምሮ    ያሳተፈ የ10 ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን  ያዘጋጀውና በኃላፊነት ያስተባበረው የኮሌጁ የውስጥ የኦዲት ዳይሬክቶሬት ሲሆን ዳይሬክቶሬቱ በሚያደርገው የውስጥ ኦዲት ክትትልና ድጋፍ አማካኝነት የታዩ አንዳንድ ግድፈቶችን ለማረምና   የሚስተዋሉ የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ታቅዶ መሆኑ ተገልጿል።

ስልጠናው በፋይናንስ መመሪያዎች አፈጻጸምና በመዋቅራዊ አሰራር ሂደት ዙሪያ ንድፈ ሃሳባዊ እና ተግባራዊ ልምምድ በማድረግ የተሰጠ ሲሆን ተቋማዊ የሃብት ብክነትና የአሰራር ጥሰት እንዳይፈጠር ያግዛል መባሉንም ሰምተናል።

ስልጠናው በመሰረታዊነት ያተኮረባቸው በሂሳብ አያያዝ፣ በግዢ ስርዓት አፈጻጸም፣ በንብረት አያያዝና አጠቃቀም እና በኦዲት አሰራር ስርዓት እንዲሁም በበጀት ክትትልና አጠቃቀም ዙሪያ ነው።

የስልጠና አቀራረብም ሆነ ይዘት በጣም ጥሩ እንደነበር ተሳታፊዎች ገልጸው የዚህ አይነት  ስልጠና ቀጣይነት ባለው ጊዜ ከተሰጠ በአሰራር ላይ የሚገጥሙ ችግሮችን በማስቀረት እና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ረገድ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ ነውም ተብሏል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
https://t.me/gwstudent

ማስታወቂያ

ለኮሌጁ ሰልጣኞች

ከኮሌጁ ይህ ዋናው የቴሌግራም ገጽ በተጨማሪ በሰልጣኝ ካውንስል የሚተላለፉ ሰልጣኝ ነክ መረጃዎችን በዚህ ተጨማሪ ገጽ መከታተል ትችላላችሁ።
ረቡዕ፡- ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም

የጥንቃቄ መልዕክት ማስታወቂያ!!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለመዲናይቱ ነዋሪዎች፣ በተለያዩ ሁኔታዎች ላይ ለሚገኙ ወጣቶችና ተማሪዎች ስለ አዋኪ ጉዳዮች ምንነት፣ አጋላጭ ምክኒያቶች፣ የሚያደርሱት ጉዳቶች እና የተጠያቂነት ሂደቶች ዙሪያ ትኩረት ያደረጉ ይዘቶችን ያካተተ የድምጽ መልዕክት ስለላከ ለጥንቃቄ ይረዳችሁ ዘንድ እንደሚከተለው አድርሰንላችኋል።

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
አርብ:- ታህሳስ  4 ቀን 2017 ዓ∙ም

ፋዊ ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ሰልጣኞችና ቤተሰቦቻቸው ስለ ፕሮግራሙ በኮሌጁ ገለፃ ሰጠ!!

የአፍሪካ ሴት የትምህርት ባለሙያዎች ፎረም /FAWE/ ከማስተር ካርድ ፋውንደሽን ጋር በመተባበር የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ሰልጣኞችና ቤተሰቦቻቸው ስለፕሮግራሙ ይዘት ግንዛቤ ሰጠ።

በዕለቱ የፋዊ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ እና የቦርድ ሰብሳቢ፣ የድርጅቱ ሰራተኞች፣ የኮሌጁ አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።

ፋዌ ኢትዮጵያ ቻፕተር እና ፋዌ አፍሪካ ከማስተር ካርድ ፋውንደሽን ጋር በመተባበር የሃርድ ስኪል ስልጠና ለሚከታተሉ ሰልጣኞች የትምህርትና ስልጠና ድጋፍ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲትሆኑ አድርጓል፡፡

እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው ጀነራል ዊንጌት እና አዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ሲሆኑ በሁለቱ ተቋማት እየሰለጠኑ ለሚገኙ ሰልጣኞች ስለ ድርጅቱ ምንነት፣ የሚሰጣቸው ድጋፍ ዓይነቶች እና ከሰልጣኞችና ቤተሰቦቻቸው የሚጠበቅ ትጋት ምን እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።

ፋዊ በምዕራፍ ሁለት ፕሮግራሙ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና /TVET/ ላይ ትኩረት አድርጎ ከ15 - 25 የዕድሜ ክልል የሚገኙ ወጣቶችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው።

ፕሮግራሙ 80 ከመቶ ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከ5 እስከ 10 ፐርሰንት ለአካል ጉዳተኛ ከ10 እስከ 15 ፐርሰንቱ ደግሞ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ዜጎች ዕድል መስጠቱ ታውቋል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
አርብ፡- ታህሳስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ለሚሰጡ አሰልጣኛኞች ስልጠና ተሰጠ!!

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት ለሚሰጡ የኮሌጁ አሰልጣኛኞች የ5 ቀናት ስልጠና ተሰጠ::

በኮሌጁ የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲን ቢሮ በኩል 40 ለሚሆኑ አሰልጣኞች ከኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ትግበራ ጋር በተያያዘ ስልጠና ተሰጥቷል።

ስልጠናው ከህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን ይዘቱም ድጋፍ ከሚሰጥባቸው ማዕቀፎች መካከል በኢንተርፕርነርና በካይዘን ትግበራ ዙሪያ መሆኑን ሰምተናል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››