General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ:- ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ∙ም

በኮሌጁ የአቻ ለአቻ ውይይትና የባህርይ ለውጥ ስልጠና ተሰጠ!!

በኮሌጁ ጤና ባሙያዎች ሁለት ቀናት ቆይታ የነበረው የአቻ ለአቻ ውይይትና የባህርይ ለውጥ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በዚህ መድረክ የኮሌጁ ሰራተኞችና ከሰልጣኞች የተወከሉ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ጥቅምት 21 እና 22 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በዚህ ቆይታ በህይወት ክህሎት፣ በስርዓተ ፆታ፣ በኤች አይ ቪ ሚኒስትሪሚንግና መሰል ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ተችሏል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ለ2017 ዓ.ም አዲስ ተመዝጋቢዎች

በኮሌጁ የ2017 አዲስ application form እስከ 22/02/2017ዓ.ም ሞልታችሁ ያመለከታችሁ ሰልጣኞች አሁን ላይ የማጣራት(screening) ተሰርቶ ከ1 እስከ 3 ከመረጣቿቸው ሙያዎች ውስጥ 1 ሙያ ደርሷችሁmessage ደርሷቹዋል።

በቅድምያ Registration ከመጀመራቹ በፊት ይህንን ያዘጋጁ;-
1.ከ8ኛ -12ኛ ክፍል ያለውን ዶክሜንት scan(photo) አርጋችሁ መያዝ
2.ክፍያ የከፈላቹበትን ደረሰኝ scan(photo) አርጋችሁ መያዝ
ከዛም በኮሌጁ Registration website; https://gwptc.aatvetb.edu.et/ በመግባት registration form የሚለውን በመጫን Registration እንድታከናውኑ እያሳወቅን ፎርሙ ላይ Year of commencement የሚልበት 1ኛ ክፍል የገባቹበትን አመተ ምህረት Payement method በሚልበት ደሞ offline በማለት ምዝገባቹን እንታጠናቅቁ እናሳውቃለን።

ለበለጠ መረዳት ዌብሳይቱ ላይ Registration guide የሚለውን ይመልከቱ

ከ22/2/2017 ዓ.ም በኋላ የተመዘገባችሁ screening እስኪሰራ በትዕግስት ጠብቁ
Registration ይህንን በማየት ማከናወን ትችላላቹ
ሰኞ:- ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ∙ም

    ከ3ሺ 300 በላይ አዳዲስ ሰልጣኞች በ2 ሳምንት ተመዘገቡ!!

ኮሌጁ የ2017 ዓ.ም አዳዲስ ሰልጣኞችን  ከጥቅም 15 ቀን 2017 ዓ∙ም ጀምሮ በበየነ መረብ /online/  እና በሀርድ ኮፒ ለ2 ሳምንታት የመዘገበ ሲሆን በዚህም 3365 የሚሆኑ አዳዲስ ሰልጣኞችን መዝግቧል።

ኮሌጁ አሁን ላይ በISO 9001:2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ መሆኑ፤ የስልጠና ጥራቱን ለማሳደግ ከግዙፍ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራቱ  እና ባለው ተቋማዊ ዘርፈ ብዙ ፋሲሊቲዎች ለስልጠና ጥራቱ ትኩረት መስጠቱ ተመራጭነቱን ይበልጥ ስላሰፋው ከፍተኛ ተመዝጋቢ ካላቸው የመዲናችን ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ ተርታ ይሰለፋል።

ውድ አዳዲስ ተመዝጋቢዎች! በመሉ እምነት እኛን ተማምናችሁ መርጣችሁን ስለመጣችሁ እናመሰግናለን።

የምዝገባ ቀናትን በተመከለተ ምንም እንኳን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ለማጠናቀቅ ቢታቀድም በተለያየ ምክኒያት ምዝገባቸውን ላላጠናቀቁ አመልካቾች ተጨማሪ 4 ቀናት ዕድል ተመቻችቷል።                                                    
ስለሆነም እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ባሉበት ሆነው በበየነ መረብ /online/ ወይም በኮሌጁ በአካል በመገኘት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ስናበስርዎት በታላቅ ደስታ ነው።      

የሙያ ምርጫን በተመለከተ በማታና በቅዳሜና እሁድ ለምትሰለጥኑ በፍላጎታችሁ የምትስተናገዱ ሲሆን ለቀን አመልካቾች ደግሞ ከቢዝነስ፣ ከአይሲቲ፣ ከአውቶሞቲቭ እና ከፉሽን ዲዛይን ዲፓርትመንቶች ውጪ ባሉ ሙያዎች እንደ ምርጫችሁ ትስተናገዳላችሁ።  

ስለሆነም በተቀመጡበት ቀሪ ቀናት ፈጥነው እንዲመዘገቡ እየመከርን ከዚያ በኋላ የመመዝገቢያ ሰንደቁ /ሊንኩ/ የሚዘጋ መሆኑን እንገልፃለን።

   "በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"