General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
በነገው ዕለት ለምትመረቁ የኮሌጃችን ሰልጣኞች በሙሉ እንኳን ለምረቃ በዓል ቀናችሁ በሰላም አደረሳችሁ!

በነገው እለት ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ሚወስዱ ባስ ሚነሱባቸው ቦታ እና አስተባባሪዎች
አስኮ
ይሳቅ ሰይፉ         +251 98 526 5461
አብርሃም እሸቱ    +251 97 372 6272
ማፉዝ ወግአየው    +251967452450

አየርጠና

ፍሮምሲስ ዮሃንስ  +251924898428
ዮናስ ሰለሞን         +251 91 355 2815
ሃብታሙ               093 294 0553

ዊንጌት

እስቲፋኖስ ዘውዱ         +251 91 138 0537
ቃልአብ የማነ                +251973412760
ሮባ ኢተፋ                     +251 96 135 8978
👍3
ለውድ ተመራቂዎች በድጋሚ

ነገ ሐሙስ(16/12/16ዓ.ም) የምረቃ ፕሮግራማችሁ በሚሊኒዬም አዳራሽ መሆኑ ይታወቃል። ቀኑ የስራ ቀን በመሆኑ መንገድ መዘጋጋት ስለሚኖር ይዘዋችሁ የሚሄዱት መኪኖች ከ12:30 በኋላ ስማይጠብቋቹ 12:00 በመገኘት ትራንስፓርቱን እንድትጠቀሙ እያሳወቅን በግል የምትሄዱ ከ1:30 ተኩል በኋላ ወደ አዳራሹ መግባት ስለማይቻል እንደደረሳችሁ ቶሎ በመግባት ከመድረኩ ፊትለፊት ባለው ወንበሮች እንድትቀመጡ እናሳውቃለን

ኮሌጁ
👍15👎5
ረቡዕ፡- ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ

ለኮሌጃችን አስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች በሙሉ

ለኮሌጃችን አስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ሐሙስ እና አርብ ይሰጣል የተባለው የ2 ቀን ግምገማዊ ስልጠና ነገ ሐሙስ የኮሌጁ ሰልጣኞች ምረቃ ስነ ስርዓት ስለሆነ ስልጠናው አርብ እና ቅዳሜ ማለትም ነሐሴ 17 እና 18 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን ሁሉም የዘርፉ ሰራተኞች በተቀያሬው ቀናት ሰዓት አክብራችሁ እንዲትገኙ እናሳውቃለን፡፡

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
👍3👎1
ረቡዕ፡- ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

በኮሌጁ እንደ ክላስተር ለአሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረው ግምገማዊ ስልጠና ተጠናቀቀ!!

በጀነራል ዊንጌት ክላስተር ስር ለሚገኙ አሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረው ግምገማዊ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቆ ማጠቃለያ ተሰጠ፡፡

ግምገማዊ ስልጠናው ህብረ ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ለጋራ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የቀረበ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ አማካኝነት እንደ ከተማ የተዘጋጀ ነበር፡፡

አዲስ ዕይታና አዲስ አስተሳሰብ ያለዉ ምርታማ ሰራተኛን፣ ለሃገር ዘላቂ ሰላምና ዕድገት የሚተጋ ሀገር ወዳድ ዜጋን እንዲሁም ከትርክት የዘለለ በምክንያት እና በእውነት የሚያምን አሰልጣኝን ለመፍጠር ነው የተባለለት ግምገማዊ ስልጠና የመወያያ ሰነድ በማቅረብ እና በተለያየ ደረጃ ላይ በሚገኙ አመራር አካላት የቡድን ውይይት በማድረግ ሲካሄድ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍101🏆1
ሐሙስ፡- ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሲሰለጥኑ የነበሩ ከ5ሺ በላይ ሰልጣኞች በሚሊኒየም አዳራሽ ተመረቁ!!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ 14 የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሲሰለጥኑ የቆዩ 5180 ሰልጣኞች ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ  በድምቀት የተመረቁ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 835ዎቹ በጀነራል  ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሲሰለጥኑ የነበሩ ናቸው።

በዕለቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ  አቶ ጥራቱ በየነን  ጨምሮ ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የኮሌጆች አመራር፣ አሰልጣኞች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

የመዲናይቱ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለተመራቂዎች ‹‹የእንኳን ደስ አላችሁ!!›› መልካም ምኞታቸውን ገልጸው ‹‹የሀገራችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ በተለይ በክህሎትና በስነ ምግባር የታነፀ፣ የስራ ባህልን መመሪያው ያደረገና በአስተሳሰብ የዳበረ፣ ትጉህ የሆነና ተለውጦ የሚለውጥ የሰው ኃይል ስለሚስፈልግ እጆቻችሁን ለስራ አዕምሯችሁን ለለውጥ  ማዘጋጀት አለባችሁ፤ ችግሮችን የተሻገሩ የተጉና የሰሩ ናቸው›› ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በ2016 ዓ/ም በተካሄደው የክህሎት ውድድር የተሻለ ወጤት ላስመዘገቡ እና ልዩ ልዩ ቴክኖሎጂዎችን ለፈጠሩ ሰልጣኞች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸው መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍14👏21🙏1
ሐሙስ፡- ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም                                                                                                                  
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር  እና የተጠሪ ተቋማት አመራር አካላት በኮሌጁ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ!!

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር  እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዛሬ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡

‹‹የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ›› በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደ  የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሌሎች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ የተጠሪ ተቋማቱ እና የኮሌጁ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም የኮሌጁ ተመራቂ ሰልጣኞች በቦታው በመገኘት ግቢውን በልዩ ልዩ እጽዋት የማልበስ ስራ ላይ ተሳትፈዋል።

የዚህ ዓመት ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ መርሃ ግብር አካል በሆነው የችግኝ ተከላ ንቅናቄ መሰረት በዛሬው ዕለት በኮሌጁ ከ6000 በላይ ችግኞች መትከል የተቻለ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 4ሺው /66.6 በመቶው/  ቡና፣ አቡካዶ፣ አፕልና ሌሎችን ጨምሮ የአትክልት እና ፍራፍሬ  እፅዋት ናቸው፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍184👌1