General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሰኞ:- ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም

ማስታወያቂ!!

ለኮሌጁ ሰራተኞች በሙሉ

ሙያ እና ክህሎት ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረውን የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ምክኒያት በማድረግ ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ በአሮጌው አዳራሽ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት የፓናል ውይይት ይደረጋል፡፡

ስለሆነም በዕለቱ ሰዓት አክብራችሁ በመገኘት እንዲትሳተፉ ተብላችኋል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
2👍1👎1
Forwarded from fikir
👍2🙏2
አስቸኳይ ለአጠቃላይ የኮሌጁ ሰራተኞች

ዛሬ በቀን 05/10/16 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ላይ ስለምትፈለጉ በኮሌጁ አሮጌው አዳራሽ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

ኮሌጁ
👍1
ረቡዕ:- ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም

በኮሌጁ የፓናል ውይይት መድረክ ተካሄደ!!

14ኛውን የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ምክኒያት በማድረግ ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ የፓናል ውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

በዚህ መድረክ ላይ የኮሌጁ ሰራተኞች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ ተወካዮች እና የፓናል ውይይት አቅራቢ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ የመወያያ ጽሑፎች በሁለት የዘርፉ ምሁራን ተጋባዥ እንግዶች ቀርበዋል፡፡ አንደኛው በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዓላማ፣ ስትራቴጂክ እና መርሆች ላይ ያተኮረ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በግሪን TVET፣ በዲጂታላይዜሽን፣ በተቋማዊ መሰረተ ልማት ግንባታ እና በአሰልጣኞች አቅም ማጎልበት ላይ መሰረት ያደረገ ሰፊ ትንታኔ ተሰጥቷል፡፡

በዚህ የፓናል ውይይት መድረክ የቴክኒክ እና ሙያ ዘርፍ በተቋም፣ በከተማ አስተዳደር፣ በሀገር ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ በጎ እምርታዎችና ፈታኝ ተግዳሮቶች በጥልቀት ተዳሰዋል፡፡

በወቅቱ የፓናል መድረኩ ተሳታፊዎችም ውስጣዊ እና ውጫዊ ተጽዕኖዎችን በማንሳት ከእያንዳንዳችን ምን ይጠበቃል የሚለውን ገንቢ ሀሳብ አንስተዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡ ሀሳቦች ላይ ማጠቃለያ ተሰጥቶ እና ቀጣይ መሰል መድረኮች በስፋት እንደሚኖሩ ተጠቁሞ የዕለቱ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡

14ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ቴክኒክ እና ሙያ ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ቃል ከሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በከተማ ደረጃ በቴክኖሎጂ ኤግዚቪሽን እንደሚከበር መዘገባችን ይታወቃል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍8👌1
Forwarded from ንጉሡ ዳንኤል
👍7👎2
ቅዳሜ፦ ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ∙ም

                          "ኢድ ሙባረክ''

ለኮሌጃችን የእስልምና እምነት ተከታይ ሰራተኞች፣ ሰልጣኞች እና አጋሮቻችን በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የበጎነት ይሆን ዘንድ እንመኛለን::

ጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
👍178🙏4