ማስታወቂያ
ያሬድ አበበ የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቀድሞ ሰልጣኝ የነበረ ሲሆን አባቱ አቶ አበበ አያሌው ደግሞ የኮሌጃችን ሠራተኛ ናቸው።
ስለሆነም ነገ እሁድ ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም በዋልታ ቴሌቪዥን 9:00 ጀምሮ በሚቀርበው ደሞ አዲስ በተሰኘ የሙዚቃ ባለ ተሰጥኦ ውድድር በ8970 - B1 ላይ ቴክስት በማድረግ እናበረታታው።
ያሬድ አበበ ከባድ የሚባሉ የቀድሞ አንጋፋ አርቲስቶችን ስራ በማቅረብ የተካነ ታዳጊ ነው። ስለሆነም ነገም በሚደረገው ውድድር በድጋፋችን እናበረታታው።
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለተሳትፏችሁ ከወዲሁ እናመሰግናለን።

👍18🏆12
ሰኞ:- ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም
ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ልዑካን በኮሌጁ የስራ ጎበኝት አደረጉ!!
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በሆኑት ዶክተር በከር ሻሌ የተመራ ልዑካን ቡድን በኮሌጁ የተከናወኑ አጠቃላይ ስራዎችን የመስክ ምልከታ ለማድረግ በዛሬው ዕለት በኮሌጁ ተገኝተዋል፡፡
የመስክ ምልከታው በኢፌዲሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሲሆን ዓላማውም በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከእቅድ አፈፃፀም አንፃር ተቋማት ላይ የተከናወኑ ተግባራትን በአካል ለማየት ታስቦ የተደረገ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡
በዚህ ምልከታ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተሩን ጨምሮ ከተለያዩ 7 የፌደራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ይኸውም በተቋማት ደረጃ ከወረቀት ሪፖርት ባለፈ መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ እውነት ለማረጋገጥ ሲሆን በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ደረጃ ለዚህ ምልከታ የተመረጠው ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዕለቱ ለልዑካን ቡድኑ አጠቃላይ የኮሌጁን የስራ እንቅስቃሴ በኮሌጁ ዲኖች አጭር ገለፃ ከተሰጣቸው በኋላ እያንዳንዱን የተከናወነ ስራ እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡
በዚህም ምልክታ ልዑካኑ ከዚህ በፊት ከሰሙት በላይ ባዩት ነገር የበለጠ እንደተደነቁ ጠቁመው በተጨማሪነት ቢሳኩ ያላቸውን ተግባራት ገልፀው ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል፡፡
‹‹ በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

👍10
ማክሰኞ:- ሚያዚያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ኮሌጁ ያደለባቸውን በሬዎች ለበዓል ገበያ አቀረበ!!
በኮሌጁ የከተማ ግብርና ዘርፍ ስልጠና ለመስጠት እና ተቋማዊ የውስጥ ገቢውን ለማሳደግ ከዚህ በፊት ገዝቶ ያደለባቸውን በሬዎች ለትንሳኤ በዓል ገበያ አቀረበ፡፡
የከተማ ግብርና ዲፓርትመንት ለሚሰጣቸው የእንሰሳት ሙያ ስልጠናዎች ወርክሾፕነት እና የኮሌጁን የውስጥ ገቢ አቅም ከፍ ለማድረግ ታቅዶ ተገዝተው እየደለቡ የሚገኙ ከ25 በላይ በሬዎችን ለበዓለ ትንሳኤ ገበያ አቅርቧል፡፡
በሬዎቹ ለኮሌጁ ማህበረሰብ እና ለአካባቢው ነዋሪ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጡ ሲሆን ዝቅተኛው 40 ሺ ብር ከፍተኛው ደግሞ 80 ሺ ብር እየተከፈለባቸውም ይገኛል፡፡
ቀጣይም በሬዎችን በስፋት የማድለብ እና እሴት የተጨመረባቸው የፍጆታ ግብዓቶችን ለማህበረሰቡ በማቅረብ የተቋሙን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ እቅድ መያዙን የገለፁልን ደግሞ በኮሌጁ የውስጥ ገቢ አቅም ማሳደግ ዘርፍ ተጠሪ የሆኑት አቶ አበጀ በለጠ ናቸው፡፡

👍5👏1
ማክሰኞ:- ሚያዚያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳው ግንባታ እየተፋጠነ ነው!!
በኮሌጁ ዋና በር መግቢያ ላይ የሚገኘውና በተለምዶ ትንሹ የእግር ኳስ ሜዳ እየተባለ የሚጠራው ቦታ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የእግር ኳስ ማዘውተሪያ ሜዳ እንዲሆን ታቅዶ በቅርቡ ስራው የተጀመረ ሲሆን አሁን ላይ ግንባታው እየተፋጠነ ይገኛል::
ማህበረሰባዊ የግል አጋሮች ተሳትፎ /Public Private Partnership participation/ በሚለው መርህ መሰረት ፉት ፒች ኃላ/የተ/የግ ድርጅት በተሰኘ ኩባንያ ግንባታው እየተሰራ የሚገኘው የእግር ኳስ መለማመጃ ሜዳ አሁን ላይ ከ4 ውስጥ የአንደኛው ዘመናዊ ሜዳ ግንባታ በፍጥነት እየተሰራ ይገኛል፡፡
ወደ 20 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚጠይቀውን የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ስራ ኮሌጁ የግል አልሚዎችን በመጋበዝ ወደ ስራ ከተገባ ጥቂት ቀናት ተቆጥረዋል፡፡
ሜዳው አርቲፊሻል ሳር ማልበስን ጨምሮ ልዩ ልዩ ግብዓቶች የሚሟሉለት ሲሆን ስራው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በማህበረስብ አገልገሎት ዘርፍ የአካባቢው ወጣቶች በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ፣ የኮሌጁ ተቋማዊ ገጽታ ማራኪ እንዲሆን፣ የኮሌጁ የውስጥ ገቢ እንዲያድግ፣ ለተለያዩ የጤና ስፖርት ቡድኖችና ለኮሌጁ ማህበረሰብ ስፖርታዊ እንቀስቃሴ እንዲያደርጉ ታስቦ ወደ ስራ መገባቱን መዘገባችን ይታወቃል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

👍13❤3👌2
ማክሰኞ:- ሚያዚያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደረገ።
የ2016 የትምህርት ዘመን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሐምሌ 9 እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ/ም ደግሞ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል ተብሏል።
በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ከሐምሌ 6 እስከ 7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናልም መባሉን ሰምተናል።
መረጃውን እውቁልኝ ብሎ በማህበራዊ ትስስር ገጽ ያጋራው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ነው።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ምንጭ፡- የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

👍13❤4