ቅዳሜ:- ሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም
በስነ ምግባርና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!!
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን በመጡ ባለሙያዎች በስነ ምግባርና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ለኮሌጁ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ።
ስልጠናው ሁለት ቀናት የፈጀ ሲሆን በስነ ምግባርና በመልካም አስተዳደር፣ በሙስና መከላከል እና በጥቅም ግጭት ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ነው።
የስልጠናው ዓላማ ህዝብን ለማገልገል የተቀመጠውን የመንግስት የአሰራር ስርዓት ተከብሮ ከሙስናና ከብልሹ ተግባር ነጻ የሆነ ዜጋ መፍጠር ነው።
የስልጠናው ፋይዳ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍንና ከሙስናና ብልሹ አሰራር የጸዳ ፍትሀዊ አገልግሎት ለሁሉም ዜጎች በእኩል ደረጃ ለመስጠት ነው ተብሏል።
በነገራችን ላይ በዓለማችን ሙስናን ተፋልመው ለዜጎቻቸው ፍትሀዊ አገልግሎት መስጠት ከቻሉ ሀገራት ውስጥ አንደኛዋ ደንማርክ ስትሆን ፊላንድ በ2ኛነት ትከተላለች። ከአፍሪካ ደግሞ ቦትስዋና ስትሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ 35ኛ ላይ ትገኛለች።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

👍2
ቅዳሜ:- ሚያዚያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም
አሰልጣኞቹ ተግባራዊ ጥናትና ምርምራቸውን አቀረቡ!!
ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በቡድን የሰሩ አሰልጣኞች የጥናት ውጤት ሰነዳቸውን በትናንትናው ዕለት ለውውድር አቀረቡ።
በዚህ ውድድር 4 የጥናትና ምርምር ሰነዶች ለባለሙያዎች ቀርበው ምዘና የተደረገባቸው ሲሆን በሁሉም ዘርፎች የተሰሩ የምርምር ተግባራት የኮሌጁን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ይረዳሉ ተብሏል።
የተግባራዊ ጥናትና ምርምሩ ዓላማ እንደ ተቋም የራስን ችግር በራስ አቅም ለመፍታት ያቀደ ሲሆን ሁሉም ጥናቶች የተነሱበትን ክፍተቶች ለመሙላት የሚችሉ ናቸው ተብሏል።
በውድድሩ ርዕሰ ጉዳዩ አንገብጋቢ ችግር መሆኑ፣ ከችግሩ ጋር የተሰናሰለ ዓላማ መቀረጹ፣ ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ርቀት፣ በምርምር ሂደቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ወዘተ የሚሉ መስፈርቶች ተካተዋል።
በዚህ ውድድር የአዳዲስ ሰልጣኞችን መጠነ ማቋረጥ ለመቀነስ የተሰራው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሰነድ ቀዳሚውን ደረጃ ይዟል።
እንደ ተቋም 7 ተግባራዊ ጥናትና ምርምር እየተሰራ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለግምገማ የቀረቡት 4ቱ ናቸው።
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍8👏2🏆2❤1
ማስታወቂያ
ያሬድ አበበ የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቀድሞ ሰልጣኝ የነበረ ሲሆን አባቱ አቶ አበበ አያሌው ደግሞ የኮሌጃችን ሠራተኛ ናቸው።
ስለሆነም ነገ እሁድ ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም በዋልታ ቴሌቪዥን 9:00 ጀምሮ በሚቀርበው ደሞ አዲስ በተሰኘ የሙዚቃ ባለ ተሰጥኦ ውድድር በ8970 - B1 ላይ ቴክስት በማድረግ እናበረታታው።
ያሬድ አበበ ከባድ የሚባሉ የቀድሞ አንጋፋ አርቲስቶችን ስራ በማቅረብ የተካነ ታዳጊ ነው። ስለሆነም ነገም በሚደረገው ውድድር በድጋፋችን እናበረታታው።
ውድ ቤተሰቦቻችን ስለተሳትፏችሁ ከወዲሁ እናመሰግናለን።

👍18🏆12
ሰኞ:- ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም
ከተለያዩ የፌደራል መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ልዑካን በኮሌጁ የስራ ጎበኝት አደረጉ!!
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በሆኑት ዶክተር በከር ሻሌ የተመራ ልዑካን ቡድን በኮሌጁ የተከናወኑ አጠቃላይ ስራዎችን የመስክ ምልከታ ለማድረግ በዛሬው ዕለት በኮሌጁ ተገኝተዋል፡፡
የመስክ ምልከታው በኢፌዲሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሲሆን ዓላማውም በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከእቅድ አፈፃፀም አንፃር ተቋማት ላይ የተከናወኑ ተግባራትን በአካል ለማየት ታስቦ የተደረገ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡
በዚህ ምልከታ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተሩን ጨምሮ ከተለያዩ 7 የፌደራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ይኸውም በተቋማት ደረጃ ከወረቀት ሪፖርት ባለፈ መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ እውነት ለማረጋገጥ ሲሆን በቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ደረጃ ለዚህ ምልከታ የተመረጠው ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዕለቱ ለልዑካን ቡድኑ አጠቃላይ የኮሌጁን የስራ እንቅስቃሴ በኮሌጁ ዲኖች አጭር ገለፃ ከተሰጣቸው በኋላ እያንዳንዱን የተከናወነ ስራ እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡
በዚህም ምልክታ ልዑካኑ ከዚህ በፊት ከሰሙት በላይ ባዩት ነገር የበለጠ እንደተደነቁ ጠቁመው በተጨማሪነት ቢሳኩ ያላቸውን ተግባራት ገልፀው ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል፡፡
‹‹ በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

👍10
ማክሰኞ:- ሚያዚያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ኮሌጁ ያደለባቸውን በሬዎች ለበዓል ገበያ አቀረበ!!
በኮሌጁ የከተማ ግብርና ዘርፍ ስልጠና ለመስጠት እና ተቋማዊ የውስጥ ገቢውን ለማሳደግ ከዚህ በፊት ገዝቶ ያደለባቸውን በሬዎች ለትንሳኤ በዓል ገበያ አቀረበ፡፡
የከተማ ግብርና ዲፓርትመንት ለሚሰጣቸው የእንሰሳት ሙያ ስልጠናዎች ወርክሾፕነት እና የኮሌጁን የውስጥ ገቢ አቅም ከፍ ለማድረግ ታቅዶ ተገዝተው እየደለቡ የሚገኙ ከ25 በላይ በሬዎችን ለበዓለ ትንሳኤ ገበያ አቅርቧል፡፡
በሬዎቹ ለኮሌጁ ማህበረሰብ እና ለአካባቢው ነዋሪ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጡ ሲሆን ዝቅተኛው 40 ሺ ብር ከፍተኛው ደግሞ 80 ሺ ብር እየተከፈለባቸውም ይገኛል፡፡
ቀጣይም በሬዎችን በስፋት የማድለብ እና እሴት የተጨመረባቸው የፍጆታ ግብዓቶችን ለማህበረሰቡ በማቅረብ የተቋሙን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ እቅድ መያዙን የገለፁልን ደግሞ በኮሌጁ የውስጥ ገቢ አቅም ማሳደግ ዘርፍ ተጠሪ የሆኑት አቶ አበጀ በለጠ ናቸው፡፡

👍5👏1