General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.97K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሰኞ:- መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

አሻራ እንነካለን፣ አሻራችንንም እናስቀምጣለን!!

የኮሌጁ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በሰራተኞች ዲጂታል የሰዓት መቆጣጠሪያ አጠቃቀም እና አጠቃላይ የፐብሊክ ሰርቫንቱ መብት እና ግዴታዎች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ተደረገ፡፡

እንደ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ሰርቫንቱ መብት እና ግደታ የተደነገገባቸውን አዋጆች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች በማጣቀስ ለተሳታፊዎች በገለፃ ያቀረቡት የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሯ መቅደስ አባይ ናቸው፡፡

በገለፃው ላይ የዲጂታል የሰዓት መቆጣጠሪያ ስርዓት /የጣት አሻራ/ አጠቃቀም ዙሪያ በስፋት ተነስቷል፡፡ እንደ ኮሌጅ ከማኑዋል ወደ ወረቀት አልባ ዲጂታል ስርዓት መሻጋገራችን ግድ ይለናል ምክኒያቱም የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች መፈልፈያ ቋት ሆነን ለሌሎች ስናሸጋገር የእኛ የቴክሎጂ አጠቃቀማችን መዘግየት የለበትም ያሉት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ናቸው፡፡ ዋና ዲኑ አክለውም ኮሌጃችንን በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፖሊ ቴክኒክ ለማድረግ የያዝነው ራዕይ እውን የሚሆነው የጊዜ አጠቃቀማችን ውጤታማ ሲሆን ነው ነገር ግን የተዘረጋው ስርዓት ከተቋሙ የስራ ባህርይ እና ከሰራተኛው የስራ ጠባይ ጋር ቅን ተዛምዶ እንዲኖረው ይደረጋል ብለዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር የተቋሙን የውስጥ ገቢ በማሳደግ ኮሌጁ የሚሰጠውን አገልግሎት ለማዘመንና ሰራተኛውን ለመደጎም ሁሉም ዲፓርትመንቶች ባቀረቡት የምርትና የአገልግሎት ፕሮፖዛል መሰረት በፍጥነት ወደ ስራ እንዲገቡ አቅጣጫ የተሰጠ ሲሆን የተወሰኑ ዘርፎች ወደ ገበያው መቀላቀላቸው ተገልጿል፡፡

በመጨረሻም የስራ ሰዓታችንን ለመከታተል የጣት አሻራ እንነካለን፣ ኮሌጃችንን የሚመጥን ስራ በመስራት ለቀጣይ ትውልድ አሻራችንን እናስቀምጣለን በሚለው ገዢ ሀሳብ ማጠቃለያ ተስጥቶ ተጠናቋል፡፡

ለኮሌጁ አሰልጣኞች ብቻ የሰዓት መከታተያያ ስርዓቱ ወደ ዲጂታል ከተቀየረ አንድ ዓመት ማስቆጠሩ ይታወሳል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍111👎1
ማክሰኞ:- ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

የጨረታ ማስታወቂያ

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኮሌጁ የእንሰሳት እርባታ ጣቢያ የሚገኙ የቀንድ ከብቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡

በመሆኑም ለጨረታ የቀረቡ የቀንድ ከብቶችን መግዛት የምትፈልጉ አካላት በሙሉ ጨረታው ከወጣበት ከመጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ወንድ ጥጆችን፣ የወተት ላሞችን እና ጊደሮችን መጫረት የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰንዱን ከኮሌጁ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማግኘት እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡

ሰፊውን ዝርዝር መረጃ የሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም አዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ መመልከት የሚችሉ መሆኑንም እንገልፃለን፡፡

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
👍51😢1
ማክሰኞ:- ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኮሌጁ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት ስጦታ ተደረገ!!

በኮሌጁ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው 121 ሰራተኞች የበዓል መዋያ የሚሆን የዘይት እና ዱቄት ስጦታ ተደርጓል፡፡

ስጦታው ነገ የሚከበረውን የእስልምና እምነት ተከታይ የኢድ አልፈጥር በዓል እና ከሳምንታት በኋላ ለሚከተለው የክርስትና እምነት ተከታዮች የትንሳኤ በዓልን ምክኒያት በማድረግ የተበረከተ ነው፡፡

የማዕድ ማጋራት ዓላማው በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ጫና ላይ ላሉ የስራ ባልደረቦች የመተሳሰብ እና የመረዳዳት ባህል ለማጠናከር እና የአንዱን ችግር ሌላዉ እንዲጋራ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
👍94🙏1
ማክሰኞ:- ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

"ኢድ ሙባረክ''

ለኮሌጃችን የእስልምና እምነት ተከታይ ሰራተኞች፣ ሰልጣኞች እና አጋሮቻችን በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ አልፈጥር ረመዳን በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የበጎነት ይሆንላችሁ ዘንድ እንመኛለን።

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
18👍11👏2
አርብ:- ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም

የባህላዊ ዕደጥበብ ስራዎችን ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ሰልጣኞች አጠናቀቁ!!

ከሶስት ክፍለ ከተሞች ተውጣጥተው የተለያዩ ባህላዊ የዕደጥበብ ስራዎችን ሲሰለጥኑ የነበሩ ሰልጣኞች አጠናቀቁ፡፡

በኑሮ ማሻሻያ ሴፍትኔት መርሃ ግብር ተጠቃሚ የሆኑ እና ከአራዳ፣ ከአዲስ ከተማ እና ከጉለሌ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከ200 በላይ ሰልጣኞች ባህላዊ መገልገያ የሆኑ የዕደ ጥበብ ስራዎችን አመራረት ስልጠና ሲከታተሉ ቆይተው በዛሬው ዕለት አጠናቀዋል፡፡

ስልጠናው የቃጫ ቦርሳ እና የሰፌድ ስፌት ማምረት ሁለት ሙያዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ከ3 ወር ቆይታ በኃላ ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡

ስልጠናው ኮሌጁ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ እና ኤልቢ /ELBEE/ ማኑፋክቸሪንግ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው፡፡ ኤልቢ ማኑፋክቸሪንግ ድርጅት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን እና የሙያው አሰልጣኞችን ጨምሮ ሌሎች ኃላፊነቶችን በመወጣት ትልቁን አበርክቶ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ከሰልጣኞቹ መካከል ጥሩ ችሎታ ያላቸው 40 ፐርሰንቱ በድርጅቱ በቋሚነት የሚቀጠሩ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በራሳቸው እየሰሩ ኑሯቸውን እንዲደጉሙ ይደረጋል መባሉንም ሰምተናል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍6