General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ማክሰኞ:- መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

በሰልጣኞች መካከል ሲደረግ የቆየው የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ በኮንስራክሽን ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት አሸናፊነት ተጠናቀቀ!!

በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ /ፊኒሽንግ/ እና ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ /ICT/ ዲፓርትመንቶች መካከል በተደረገ የሰልጣኞች የእግር ኳስ ፍፃሜ ጨዋታ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ሰልጣኞች ዋንጫውን አሸነፉ፡፡

ከየካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ ዲፓርትመንቶች የተውጣጡ 14 ቡድኖች ሲጫወቱ ቆይተው ለፍፃሜ የደረሱት ሁለቱ ቡድኖች ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ ፉክክር በታየበት አጓጊ ውድድር ተጫውተው ድል ለኮንስትራክሽን ሰልጣኞች ቀርባለች፡፡

ጨዋታው ምንም እንኳን 3 እኩል ሜዳ ላይ ቢጠናቀቅም መጨረሻ ላይ በተሰጠው የፍፁም ቅጣት ምት የኮንስትራክሽን /ፊኒሽንግ/ ዲፓርትመንት ግብ ጠባቂ አንድ ጎል በመከላከሉ በፍፁም ቅጣት ምቱ 5ለ4 በሆነ ትልቅ ትንቅንቅ ጨዋታው ተጠናቋል፡፡

በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑት የዲፓርንመንቱ ሰልጣኞች የዋንጫ እና የገንዘብ ሸልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ሽልማቱም በኮሌጁ ዋና ዲን በአቶ መለሰ ይግዛው አማካኝነት ተሰጥቷቸዋል፡፡

የእግር ኳስ ውድድሩ የተዘጋጀው በኮሌጁ ሰልጣኝ መማክርት አማካኝነት እንደሆነ እና ዓላማውም በሰልጣኞች መካከል የመተባበር እና የውድድር መንፈስን ለማሳደግ ታቅዶ እንደተዘጋጀ የመማክርቱ ም/ሰብሳቢ ሰልጣኝ ኤልያስ ሙልጌታ ነግሮናል፡፡


"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍16😢4🏆1
ረቡዕ:- መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

ለ14ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ!!

ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ ለሚከበረው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት በተለያዩ ዘርፎች ተወዳድሮ አሸናፊ ለመሆን የሚያስችል በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ፡፡

4 የማምረቻ፣ 5 የምርት እና 1 የአገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን በማምረት እንዲሁም አሰልጣኞች በ14 ሙያዎች፣ ሰልጣኞች በ9 ዘርፎች እና ኢንተርፕራይዞች ደግሞ 5 በሚሆኑ የሙያ መስኮች የክህሎት ውድድር ለማድረግ እቅድ መያዙን ከቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ምክትል ዲን አቶ ደሜ መርሻ ሰምተናል፡፡

ምክትል ዲኑ አክለውም የዘንድሮው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች፣ የፋሽን ሾው ትርኢቶች፣ የICT ዘርፍ ፈጠራዎችና መሰል ስራዎች የበዓሉ ዝግጅት አካል ናቸው፡፡ ብለዋል፡፡

እንደ ተቋም 7 የሚሆኑ ችግር ፈቺ ተግባራዊ የጥናት እና ምርምር ስራዎች እየተጋጁ ሲሆን ቀጣይ መጋቢት 27 ቀን 20 16 ዓ.ም ደግሞ በኮሌጅ ደረጃ የክህሎት ውድድር እንደሚጀመር ታውቋል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍9
ረቡዕ:- መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

የኮሌጁ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የንብረት አያያዜን ከማኑዋል ወደ ዲጅታል ላሸጋግር ነው አለ!!

ዳይሬክቶሬቱ ይህንን ያሳወቀው እንደ ከተማ አስተዳደር የለማውን ዘመናዊ የንበረት አስተዳደር ሶፍትዌር አጠቃቀም ለሚመለከታቸው የዳይሬክቶሬቱ እና የመንግስት ህንፃ አስተዳደር እና አገልግሎት ጽ/ቤት ባለሙያዎች ስልጠናዎችን እየሰጠ ባለበት ጊዜ ነው፡፡

በዚህ ስልጠና ላይ 16 ባለሙያዎች እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን ከንብረት ጋር የተያያዙ ጽንሰ ሀሳባዊ ገለፃ ከመሰጠቱ ባሻገር መሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም እና አጠቃላይ በለማው ሶፍትዊር ዙሪያ ተግባራዊ የክህሎት ስልጠና በኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ /ICT/ ዲፓርትመንት አሰልጣኞች እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የተቋሙን ንብረት በቀላሉ ለመቆጣጠር፣ አሰራሩን ለማዘመን እና የንብረት አጠቃቀምን ፍትሐዊነት ለማምጣት ያስችል ዘንድ ተግባራዊ ለማድረግ የታቀደው ዲጅታላይዜሽን ስርዓት ስልጠናው እንደተጠናቀቀ ወደ ስራ ይገባል ያሉን የኮሌጁ ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ጨመዳ ናቸው፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም ስርዓቱ የንብረት ብክነትን እና የተንዛዛ አሰራርን ያስቀራል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን እና የከተማ አስተዳደሩ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለዚህ ተግባር የለማው ሶፍትዌር በሁሉም የመንግስት ተቋማት ይተገበር ዘንድ ከዘርፉ ለተውጣጡ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና እንደሰጠ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍73
ይህንን link ከፍተው በመሙላት የበኩሎን ይወጡ
አርብ:- መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም

ለኮሌጁ ሰልጣኞች በተቋማዊ ስነ ምግባር ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!!

ለኮሌጁ ሰልጣኞች በተቋማዊ ስነ ምግባር ዙሪያ ላይ ትኩረት ያደረገ የ2 ቀን ስልጠና ተሰጠ፡፡

የኮሌጁ የስነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት በስነምግባር ምንነትና አስፈላጊነት፣ በሰልጣኞች የስነምግባር ክበብ ምንነትና ጥቅም እንዲሁም የብልሹ አሰራር ዓይነቶች፣ የመከላከያ መንገዶች እና ስነ ምግባር ከሰልጣኞች የስልጠና አሰጣጥ አንጻር ያለውን ትርጉም ወዘተ በተመለከተ መጋቢት 18 እና 19 ቀን 2016 ዓ.ም የ2 ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

       "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍115👎1
አግሮ ዞን ዲዛይን