General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሐሙስ:- መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

ስነምግባር

ስነምግባር ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከህብረተሰብ፣ ከተለያዩ ተቋማት /ለምሳል ከሃይማኖት እና ሌሎች/፣ ከህግ እና ፍትህ አካላት ወዘተ የሚመነጭ ሲሆን ስነ ምግባር ሰላምን ለማሰፈን፣ ሁሉም ሰው በእኩልነትና በመከባበር እንዲኖር ለማድረግ፣ የጋራ ተጠቃሚነትንና እድገትን ለማምጣት፣ ወዘተ ይጠቅማል፡፡
ስነ ምግባር ወሳኝ የሆኑ የህይወት መርሆዎችን በመከተል የሚኖር ሲሆን በመርህ ለመኖር ደግሞ ሁለንተናዊ የሆነ የሞራል ባህርይ መላበስ ያስፈልጋል፡፡
የኮሌጁ የስነምግባርና ጸረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍1
ሐሙስ:- መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

ሁሉን አቀፍ ተቋማዊ የልማት ገጽታዎቻችን እንደ ቀጠሉ ናቸው!!

ኮሌጁ በዚህ በጀት ዓመት እጅግ በርካታ የስራ ስኬቶችን ያስመዘገበበት ጊዜ ሲሆን በርካታዎቹ ስራዎች ተጠናቀዋል፤ የተወሰኑት ጥቂት ጊዜን ይሻሉ አንዳንዶቹ ደግሞ እቅድ ተይዞላቸዋል፡፡

ተቋሙን ምቹ የስራ ከባቢ እና ለእይታ ሳቢ ለማድረግ እየተከወኑ ካሉ ዘረፈ ብዙ ትጋቶች መካከል ትልቁን ሚና የሚጋሩት የኮንስትራክሽን ዘርፍ አሰልጣኞች ናቸው፡፡ ስልጠና ዘርፉ በተለያዩ አሰልጣኞች ታቅደው እየተተገበሩ ያሉ በርካታ ፕሮጀክቶችን የያዘ ሲሆን በዚህ ምልከታችን በሁለት አሰልጣኞች እየተሰራ ያለን የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና የአደባባይ ስራ በአጭር እንቃኛለን፡፡

በሁለት በኩል መተላለፊያ የሚሆኑ እና በቴራዞን ንጣፍ ለመስራት እቅድ የተያዘላቸውን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ጨምሮ በልዩ ልዩ አበባዎችና ሳሮች እንዲያሸበርቁ ታልሞ እየተሰራ የሚገኝን መለስተኛ አደባባይ ለመስራት ሲታትሩ ሁለት የዘርፉን አሰልጣኞች በካሜራችን ዐይን ተመልክተናል፡፡

600 ካሬ ሜትር ገደማ በሚሸፍን ቦታ ላይ የመንገድ እና የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን እየሰሩ ያሉ 2 አሰልጣኞች መርጋ አብዲሳ እና ገረመ ፍሪሳ ናቸው፡፡ አሰልጣኞቹ በኮሌጁ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በመመልከት እነሱም የራሳቸውን አሻራ ለማኖር በማስብ ለመስራት መነሳታቸውን ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ በፊት የነበረው ገጽታ ምቾትን የሚነሳ ነበር፡፡ ይህ ፕሮጀክት አሁን ላይ 80 ከመቶው መጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ አሰልጣኞቹ የገለፁ ሲሆን ከ20 ቀናት ባልበለጡ ጊዜያት ለማጠናቀቅ ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ውበት ማምጣት ብቻ ሳይሆን ኮሌጁን የሚገልጽ ልዩ ልዩ አስተማሪ ይዘት እና ቅርጽ እንዲኖረው ይደረጋልም ተብሏል፡፡ እኛም እንደሁል ጊዜው ብርቱ እጆች እና በጎ ተግባሮች ይቀጥሉ እያልን ቀጣይ በሌሎች ተመሳሳይ ቅኝቶች እስከምንመለስ ቸር ቆዩን፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍41
አርብ:- መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

ለሬጅስትራር ጽ/ቤት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ!!

ለኮሌጁ ሬጅስትራር ጽ/ቤት ባለሙያዎች በደንበኛ አያያዝ ዙሪያ ዛሬ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡፡

የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ ለጽ/ቤቱ ባለሙያዎች የተሰጠው ስልጠና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ ፈታኝ ነገሮችን የሚያሳይ እና ማሻሻያ ስልቶችን የሚጠቁም ነው፡፡

ስልጠናውን ያዘጋጀው በስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን ቢሮ ስር የጥናት፣ ምርምርና ፐብሊኬሽን የስራ ክፍል ሲሆን ሬጅስትራር ጽ/ቤት ከሰልጣኝ ቅብላ እስከ ስልጠና ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ስጦታ ድረስ ባለው ጌዜ ከደንበኞች ጋር ሰፊ እና ቀጥተኛ ግንኙነት ስላለው ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም እና የደንበኞችን ፍላጎት ያማከለ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል ታቅዶ መዘጋጀቱን ከስራ ክፍሉ አስተባባሪ ምስራቅ ደለሳ ማረጋገጥ ችለናል፡፡

አስተባባሪዋ አክለውም የጥናት፣ ምርምርና ፐብሊኬሽን የስራ ክፍል ተግባራዊ ጥናት እና ምርምር በማድረግ ክፍተቶች እንዲሞሉ ማድረግ ሲሆን ይህ ስልጠና እንዲሰጥ የተደረገውም በጥናቱ ግኝት መሰረት መስተካከል ካለባቸው ትግበራዎች አንዱ ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡ ስልጠናው የተሰጠው ደግሞ በሄኖክ አብርሃም ነው፡፡

የኮሌጁ ደንበኞች የመጀመሪዎቹ ሰልጣኞች ናቸው፤ ሁለተኛዎቹም ሰልጣኞች ናቸው፤ ሶስተኛ እና አራተኛም እነሱ ስለሆነም በሁሉም የስራ እንቅስቃሴ ሰልጣኝ ተኮር ስራዎችን መስራት የሁል ጊዜ ተቀዳሚ ትኩረታችን ነው፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍163
ማክሰኞ:- መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ

ለኮሌጁ ሰልጣኞች በሙሉ

የኮሌጁ የስነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት በስነምግባር ምንነትና አስፈላጊነት፤ በሰልጣኞች የስነምግባር ክበብ ምንነትና ጥቅም እንዲሁም ብልሹ አሰራር ከተማሪዎች የስልጠና አሰጣጥ አንጻር ያለውን ትርጉም በተመለከተ ለ2 ቀናት ስልጠና አዘጋጅተናል፡፡

በመሆኑም ከመጋቢት 18 – 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ---- 11፡00 ሰዓት ለ2 ተከታታይ ቀናት አስተዳደር ህንፃ 4ኛው ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስልጠናው ስለሚሰጥ በዕለቱ እና በሰዓቱ እንድትገኙ እናሳውቃለን ፡፡

የኮሌጁ የስነምግባርና ጸረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት
👍1
ማክሰኞ:- መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

በሰልጣኞች መካከል ሲደረግ የቆየው የእግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታ በኮንስራክሽን ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት አሸናፊነት ተጠናቀቀ!!

በኮንስትራክሽን ቴክኖሎጂ /ፊኒሽንግ/ እና ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ /ICT/ ዲፓርትመንቶች መካከል በተደረገ የሰልጣኞች የእግር ኳስ ፍፃሜ ጨዋታ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ሰልጣኞች ዋንጫውን አሸነፉ፡፡

ከየካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ ዲፓርትመንቶች የተውጣጡ 14 ቡድኖች ሲጫወቱ ቆይተው ለፍፃሜ የደረሱት ሁለቱ ቡድኖች ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ ፉክክር በታየበት አጓጊ ውድድር ተጫውተው ድል ለኮንስትራክሽን ሰልጣኞች ቀርባለች፡፡

ጨዋታው ምንም እንኳን 3 እኩል ሜዳ ላይ ቢጠናቀቅም መጨረሻ ላይ በተሰጠው የፍፁም ቅጣት ምት የኮንስትራክሽን /ፊኒሽንግ/ ዲፓርትመንት ግብ ጠባቂ አንድ ጎል በመከላከሉ በፍፁም ቅጣት ምቱ 5ለ4 በሆነ ትልቅ ትንቅንቅ ጨዋታው ተጠናቋል፡፡

በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑት የዲፓርንመንቱ ሰልጣኞች የዋንጫ እና የገንዘብ ሸልማት የተበረከተላቸው ሲሆን ሽልማቱም በኮሌጁ ዋና ዲን በአቶ መለሰ ይግዛው አማካኝነት ተሰጥቷቸዋል፡፡

የእግር ኳስ ውድድሩ የተዘጋጀው በኮሌጁ ሰልጣኝ መማክርት አማካኝነት እንደሆነ እና ዓላማውም በሰልጣኞች መካከል የመተባበር እና የውድድር መንፈስን ለማሳደግ ታቅዶ እንደተዘጋጀ የመማክርቱ ም/ሰብሳቢ ሰልጣኝ ኤልያስ ሙልጌታ ነግሮናል፡፡


"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍16😢4🏆1
ረቡዕ:- መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

ለ14ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ!!

ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ ለሚከበረው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት በተለያዩ ዘርፎች ተወዳድሮ አሸናፊ ለመሆን የሚያስችል በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ፡፡

4 የማምረቻ፣ 5 የምርት እና 1 የአገር በቀል ቴክኖሎጂዎችን በማምረት እንዲሁም አሰልጣኞች በ14 ሙያዎች፣ ሰልጣኞች በ9 ዘርፎች እና ኢንተርፕራይዞች ደግሞ 5 በሚሆኑ የሙያ መስኮች የክህሎት ውድድር ለማድረግ እቅድ መያዙን ከቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ምክትል ዲን አቶ ደሜ መርሻ ሰምተናል፡፡

ምክትል ዲኑ አክለውም የዘንድሮው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች፣ የፋሽን ሾው ትርኢቶች፣ የICT ዘርፍ ፈጠራዎችና መሰል ስራዎች የበዓሉ ዝግጅት አካል ናቸው፡፡ ብለዋል፡፡

እንደ ተቋም 7 የሚሆኑ ችግር ፈቺ ተግባራዊ የጥናት እና ምርምር ስራዎች እየተጋጁ ሲሆን ቀጣይ መጋቢት 27 ቀን 20 16 ዓ.ም ደግሞ በኮሌጅ ደረጃ የክህሎት ውድድር እንደሚጀመር ታውቋል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍9