General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሐሙስ፡- የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 ሰርተፊኬቱን ተቀበለ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የISO 9001:2015 ሰርተፊኬቱን ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ተቀበለ!!

ኮሌጁ የተለያዩ የክብር እንግዶች በተገኙበት የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርተፊፌቱን የተቀበለ ሲሆን በዕለቱ የኢፌዲሪ ስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነበያ መሐመድ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኤፍሬም አድማሱ፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራን ጨምሮ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በወቅቱ የጀነራል ዊንጌት ፖሉ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው በእንኳን ደህና መጣችሁ እና በመግቢያ ንግግራቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የተቀበልነው ሰርተፊኬት አሁን ላይ የምንገኝበትን የብቃት ደረጃ የሚያመላክት እና ቀጣይ ለምንደርስበት ራዕይ የጉዞ ድልድይ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ኤፍሬም አድማሱ በበኩላቸው በቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ትልቁ ሀብት ሙያ ሲሆን ተቋማቱ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መፈልፈያ ቋትነት፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከልነት እና ለኢንዱስትረው ክፍለ ኢኮኖሚ ችግር ፈቺ ምርምር ጣቢያነት ማገልገል ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በዕለቱ የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርተፊኬቱን የኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ከወ/ሮ መዓዛ አበራ ተቀብለዋል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍263👏1
አርብ፡- የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ለኮሌጃችን ሰራተኞች፣ ሰልጣኞች እና አጋሮቻችን በሙሉ እንኳን ለ128ኛው የአደዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

አደዋ በመሰዋትነት የተገኘ አክሊል፣ የአንድነት ህብር ገጽታ፣ የክብር ተራራ ከፍታ፣ የጥቁር ህዝቦች ኩራት፣ የንጋት ብርሃን ወገግታ፣ የታሪክ እንቁ ማህደር፣ የአሸናፊነት ኃይል ጥግ፣ የነፃነት መጎናፀፊያ ዳር፣ የሀበሻ ጀብዱ ሀቅ፣ ……………… ነው፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የበጎነት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍113
ማክሰኞ፡- የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8ን ምክኒያት በማድረግ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ሰልጣኞች የታብሌት ሽልማት ተበረከተላቸው!!

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8ን ምክኒያት በማድረግ ከሁሉም ዲፓርትመንቶች የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ 41 ሴት የኮሌጃችን ሰልጣኞች ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2016 ዓ.ም የታብሌት ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

በኢትዮጵያ ለ48ኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ113 ጊዜ የሚከበረው ማርች 8 የሴቶች ቀን በኮሌጃችን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የመጡ ባለሙያዎች፣ የኮሌጁ ዲኖች፣ ሰራተኞች እና ሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡

መርሃ ግብሩ በአደባባይ ፌስቲቫል እና አዳራሽ ውስጥ በተደረገ አውደ ጥናት የተካሄደ ሲሆን መድረኩን ያዘጋጀው የኮሌጁ ስርዓተ ፆታ ተወካዮች ከሰልጣኝ መማክርት አባላት ጋር በመተባበር ነው ተብሏል፡፡

አደዋ ለጥቁር ህዝቦች የነፃነት ጮራን የፈነጠቀ ሲሆን ማርች 8 ደግሞ የሴቶች እኩልነትን ለማረጋገጥ የተደረገ ታሪካዊ ቀን ነው፡፡ ስለሆነም ዛሬ እያከበርን ያለነው ሁለቱ በዓላት የፍትህ ጥያቄዎችን ለማስመለስ የተደረጉ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ በዓላት ናቸው ያሉት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ሴት እህት፣ ሴት እናት፣ ሴት ልጅ እና ሴት ሚስት በመሆን የዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ኃላፊነት የምትሸከም ብትሆንም በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ባህላዊ እና ፖለቲካዊ ጫናዎች ሲደርስባቸው ቆይቷል፡፡ ስለሆነም አሁን ላይ ማርች 8ን ስናከብር ሴቶች እንደማንኛውም ሰብአዊ ዜጋ መብታቸው እንዲከበርና እንክብካቤን እንዲደረግላቸው ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል በማለት የተናገሩት ደግሞ የኮሌጁ የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን አቶ አድማሱ በቀለ ናቸው፡፡

ማርች 8 እንደ ጎርጎሮሳዊያን የዘመን ቀመር 1908 ላይ በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ ነዋሪ የሆኑ 15,000 ሴቶች የተሻሻለ የሥራ ሰዓት እንዲኖር፣ የደመወዝ ክፍያ እኩልነት እንዲፈጠር እና የመምረጥ መብታቸው እንዲከበር ለጥያቄ አደባባይ የወጡበት ቀን ሲሆን በ1975 ዓ.ም ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሴቶች ቀንን በዓለም አቀፍ ደረጃ በይፋ እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍13