General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
Forwarded from AB 🌍 K-Raj
ኢንስቲትዩቱ ከቴክኒክና ሙያ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጋር በቅርበት እንዲሰራ ጥያቄ ቀረበ፡፡

ከጄነራል ዊንጌት ፓሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ የተውጣጡ አመራሮችና ሰራተኞች ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት አደረጉ፡፡

በውይይቱ ወቅት በኢንስቲትዩቱ ስለበለፀጉ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የቴክኖሎጂ ውጤቶችና የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ በኢንስቲትዩቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከቴክኒክና ሙያ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጋር በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ ልማት እና ተያያዥ መስኮች በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

በተጨሪም ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚያቋቁማቸውን የኤ.አይ ክበባት በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎች ብሎም በኮሌጆች ደረጃ ማስፋፋት ስለሚቻልባቸው መንገዶች ሀሳብ ቀርቧል፡፡

የውይይቱ ተካፋይ አካላት በኢንስቲትዩቱ የተመለከቱት የቴክኖሎጂ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆኑን በመግለፅ ሊበረታታ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
👍7👎3
Forwarded from fikir
👎12👍8
ማክሰኞ፡- የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

የEASTRIP ፕሮጀክት ሁለት ዓመት ተጨማሪ ቆይታ እንዲኖረው ተወሰነ!!

በኮሌጁ የEASTRIP ፕሮጀክት ትግበራ ሁለት ዓመት ተጨማሪ የጊዜ ቆይታ እና የገንዘብ ጭማሪ እንዲኖረው ተወሰነ፡፡

የጊዜ እና የበጀት ጭማሪው ብስራት ይፋ የሆነው በሀገር አቀፍ ደረጃ የEASTRIP ፕሮጀክት ከሚተገበርባቸው ኮሌጆች የተውጣጡ የፕሮጀክት ጽ/ቤት ባለሙያዎች፣ የኮሌጅ ኃላፊዎች እና የወርልድ ባንክ ተወካዮች ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ባደረጉት የስራ ግምገማ ላይ ነው፡፡ ይህም የበጀት እና የጊዜ ቆይታ ጭማሪ ስራዎችን በጥራት እና በተቀላጠፈ መንገድ ለማጠናቀቅ እድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

በዕለቱ የምስራቅ አፍሪካ እና የኢትዮጵያ EASTRIP ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ በዓለም ባንክ የፕሮጀክቱ ተጠሪዎች፣ በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የዘርፉ ተወካዮች፣ እንደ ሀገር ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው ኮሌጆች ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ዛሬ በተዘጋጀው መድረክ በየኮሌጆቹ ያለው የፕሮጀክት አፈፃፀም ግምገማ ውይይት፣ በፕሮጀክቱ የቀጣይ ጊዜ እቅድ ዝግጅት እንዲሁም በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በፕሮጀክቱ የተጀመረው የኮንስትራክሽን ስራ ሂደት ምልከታ ተደርጓል፡፡

የEASTRIP ፕሮጀክት በኢነርጂ ዘርፍ የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን በ5 ዓመት የፕሮጀክት ትግበራ ቆይታ በምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ከዓለም ባንክ 14.85 ሚሊዮን ዶላር ይዞ በመምጣት በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍152🙏1
ሐሙስ፡- የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 ሰርተፊኬቱን ተቀበለ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የISO 9001:2015 ሰርተፊኬቱን ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ተቀበለ!!

ኮሌጁ የተለያዩ የክብር እንግዶች በተገኙበት የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርተፊፌቱን የተቀበለ ሲሆን በዕለቱ የኢፌዲሪ ስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነበያ መሐመድ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኤፍሬም አድማሱ፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራን ጨምሮ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በወቅቱ የጀነራል ዊንጌት ፖሉ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው በእንኳን ደህና መጣችሁ እና በመግቢያ ንግግራቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የተቀበልነው ሰርተፊኬት አሁን ላይ የምንገኝበትን የብቃት ደረጃ የሚያመላክት እና ቀጣይ ለምንደርስበት ራዕይ የጉዞ ድልድይ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ኤፍሬም አድማሱ በበኩላቸው በቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ትልቁ ሀብት ሙያ ሲሆን ተቋማቱ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መፈልፈያ ቋትነት፣ ለቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከልነት እና ለኢንዱስትረው ክፍለ ኢኮኖሚ ችግር ፈቺ ምርምር ጣቢያነት ማገልገል ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በዕለቱ የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርተፊኬቱን የኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ከወ/ሮ መዓዛ አበራ ተቀብለዋል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍263👏1
አርብ፡- የካቲት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ለኮሌጃችን ሰራተኞች፣ ሰልጣኞች እና አጋሮቻችን በሙሉ እንኳን ለ128ኛው የአደዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

አደዋ በመሰዋትነት የተገኘ አክሊል፣ የአንድነት ህብር ገጽታ፣ የክብር ተራራ ከፍታ፣ የጥቁር ህዝቦች ኩራት፣ የንጋት ብርሃን ወገግታ፣ የታሪክ እንቁ ማህደር፣ የአሸናፊነት ኃይል ጥግ፣ የነፃነት መጎናፀፊያ ዳር፣ የሀበሻ ጀብዱ ሀቅ፣ ……………… ነው፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የበጎነት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍113