General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
Forwarded from Teshe
3😢1
Forwarded from Teshe
👍52
ሐሙስ:- ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ከተለያዩ ኮሌጆች የመጡ አካላት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጉብኝት አደረጉ!!

ከተለያዩ ኮሌጆች የመጡ አካላት በዛሬው ዕለት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

በዕለቱ በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት፣ የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጁ ማናጅመንትና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት እና የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት ናቸው፡፡

ኮሌጁ አሁን ላይ በአይ ኤስ /ISO/ 9001፡2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ መሆኑ፣ በዲጂታላይዜሽን ስራዎች የላቀ ደረጃ ላይ መገኘቱ፣ በኢነርጂ ዘርፍ የልህቀት ማዕከል ለመሆን ዘመኑን የዋጀ ግብዓት ማሟላቱ፣ የግቢውን ፋሲሊቲ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በስፋት መታየቱ እና መሰል እንቅስቃሴዎች መኖራቸው ልምዱን ይጋሩ ዘንድ ከቅርብም ከሩቅም ያሉ በርካታ ተቋማት እየጎበኙት ይገኛሉ።

በዛሬው ቀን ጉብኝት ያደረጉ አካላትም የተሰሩ አብየት ፕሮጀክቶችን በምልከታ፣ ልዩ ልዩ ተግባራትን በገለጻ፣ እና የለውጥ አሰራሮችን በውይይት ልምድ ይቀስሙ ዘንድ ተደርጓል።

ባሳለፍነው ሳምንት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን የሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ዲኖች እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ ኮሌጆች ዲኖች በኮሌጁ ተገኝተው በመጎብኘት ልምድ የወሰዱ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ የተቋማቸውን ማናጅመንት እና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት ይዘው በመምጣት ልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍104👌2
አርብ:- የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም

ለ3ኛ ዙር የስራ ላይ ልምምድ የህይወት ክህሎት ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች አጠናቀቁ፡፡

ለ3ኛ ዙር የስራ ላይ ልምምድ የህይወት ክህሎት ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቀቁ፡፡

ኮሌጁ በዚህ ዙር ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የተቀበላቸውን 395 ሰልጣኞች ስልጠና አጠናቆ የክፍለ ከተማውና የወረዳው የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አስመርቋል፡፡

ወጣቶቹ በ10 ቀናት በቆታቸው መሰረታዊ የህይወት ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ፣ የስራ ዝግጁነት ብቃቶችን እንዲጨብጡ እና የህይወት ልምዳቸውን እንዲያጎለብቱ ታልሞ የተሰጠ ሲሆን ከስልጠና በኋላ ለ6 ወራት ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ለተግባር ስራ ልምምድ የሚሄዱ መሆኑ ታውቋል፡፡

ኮሌጁ ከዚህ በፊት ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የመጡ ወጣቶችን በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዙር ስልጠና ሰጥቶ ወደ ተግባር ስራ ልምምድ እንዲወጡ አድርጓል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍71
አርብ:- የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም

የሐዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች በኮሌጁ ጉብኝት አደረጉ!!

የሐዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

በዕለቱ በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የሐዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማናጅመንትና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት ሲሆኑ ኮሌጃችን በአይ ኤስ /ISO/ 9001፡2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ መሆኑ ተከትሎ እነሱም በዚህ ሂደት ላይ በመገኘታቸው የአሰራር ልምድ ለማግኘት ፈልገው መምጣታቸው ተገልጿል፡፡

በዕለቱ የሐዋሳ ልዑካኑ ቡድን አባላት በኮሌጁ የተሰሩ አብየት ፕሮጀክቶችንና የተሟሉ ግብዓቶችን በምልከታ፣ ልዩ ልዩ ተግባራትን በገለጻ፣ እና የለውጥ አሰራሮችን በውይይት ልምድ እንዲወስዱ ተደርጓል።

የሐዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቴክስታይልና ጋርመት ቴክኖሎጂ ዘርፍ እንደ ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን በEASRIP ፕሮጀክት አማካኝነት በርካታ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍14👏42
ጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብ በሙሉ ዛሬ(12/06/16) 4 ሰዓት ላይ የወንድማችን የሰልጣኝ ቤካም ሌንጂሶ የመታሰብያ የሻማ ማብራት ፕሮግራም ስላለ በፕሮግራሙ ላይ ባስኬት ball ሜዳ እንድትገኙ እናሳስባለን።
😢30👍10🙏81