General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሰኞ፡- ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም

ኮሌጁ ከቻይናው ሻንሲ ፖሊ ቴክኒክ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የቻይናው ሻንሲ ፖሊ ቴክኒክ ኢንስቲትዩት ስልጠናን በትብብር አብሮ ለመስራት የሚያስችል መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ኃላፊዎች ባለፈው አርብ ታህሳስ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ ተገኝተው የወርክ ሾፖች ጉብኝት እና የስራ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከመግባቢያ ስምምነት መፈራረም ባሻገር የ2 ዓመት የስራ እቅድ በጋራ ማቀድ ተችሏል፡፡

ከዚህ በፊት 11 የቻይና የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች የመጡ የስራ ሃላፊዎች በኮሌጁ ተገኝተው የወርክ ሾፖች ጉብኝትና የስራ ውይይት መደረጉን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍26
ማክሰኞ፡- ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም

የ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ መደበኛ የቀን ሰልጣኞች ስልጠና ተጀመረ!!

በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2016 ዓ.ም ላይ ለመሰልጠን ያመለከቱ አዲስ ገቢ መደበኛ የቀን ሰልጣኞች ዛሬ ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ስልጠና ጀመሩ፡፡

በዚህ የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የኮሌጁ ዲኖች በመድረኩ ተገኝተው ለአዳዲስ ሰልጣኞች ስለ ስልጠና አሰጣጡ ሂደት እና በስልጠና ሂደቱ ማድረግ የሚገባቸውን የስልጠና ዲሲፕሊን አስገንዝበዋል፡፡

በዚህ የስልጠና በጀት ዓመት ከ3300 በላይ መደበኛ አዳዲስ ሰልጣኞች በ3ቱም የስልጠና መርሃ ግብራት ለመሰልጠን ያመለከቱ ሲሆን ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በሁለት እጥፍ መጨመሩ ታውቋል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍3411👏4🏆3
Forwarded from Ambachew Gets Su
👍153
ሐሙስ:- ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

ለአዳዲስ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና ተሰጠ!!

በኮሌጅ የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲን ቢሮ በኩል ለአዳዲስ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ከታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የ3 ቀናት ስልጠና ተሰጠ፡፡

ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ 90 የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ከአራቱ የድጋፍ ማዕቀፎች መካከል ስለሂሳብ መዝገብ አያያዝ እና ስለኢንተርፕርነር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡

በዚህ ስልጠና ላይ የተሳተፉት ከኮሌጁ ሙያዊ ድጋፍ ለማግኘት በ2016 ዓ.ም ወደ ኮሌጁ የመጡ አዲስ ኢንተርፕራይዞች ሲሆኑ በንግድ እና አገልግሎት ዘርፍ የተደራጁ መሆናቸው ታውቋል፡፡

አሁን ላይ በተለያየ ዘርፍ የተደራጁ 510 የሚሆኑ ነባር እና አዲስ ኢንተርፕራይዞች በኮለጁ ሙያዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛሉ።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍115🏆1