General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሐሙስ:-ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም

አዲስ በተቀረፀው የሰልጣኞች ስነ ምግባር መመሪያ ዙሪያ ከሰልጣኞች እና ከሰልጣኞች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ካላቸው አካላት ጋር ውይይት ተደረገ!!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ቢሮ ተዘጋጅቶ በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ 15 የመንግስት ቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ላይ በሚተገበረው የሰልጣኞች የስነ ምግባር መመሪያ ዙርያ ከሰልጣኞች እና ከሰልጣኞች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ካላቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።

በ4 ክፍሎች እና በ27 አንቀፆች የተሰነደው መመሪያ ሰልጣኞች ህግና ደንብ አክብረው እንዲማሩ፣ በተቋሙ ውስጥ ሁሉን አቀፍ አዎንታዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው፣ ተቋማዊ ሥርዓት እንዲሰፍን፣ የስልጠና ጥራት እንዲረጋገጥ እና ምቹ የመማር ማስተማር አካባቢን ለመፍጠር ታቅዶ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

መመሪው የስነ ምግባር ግድፈት ዓይነቶች እና የእርምት እርምጃዎችን ብቻ ሳይሆን ሰልጣኞች መጠቀም ያለባቸውን ሙሉ መብት እና መወጣት ያለባቸውን ግዴታ በስፋት ይዘረዝራል፡፡

በመመሪያው ዙሪያ ከሰልጣኞች ጋር ውይይት የተደረገው ዛሬ ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ደግሞ ትናንት ህዳር 5 ቀን ነው፡፡

በኮሌጅ ደረጃ በስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን የሚመራ የሰልጣኞች ዲሲፕሊን ኮሚቴ እንደሚዋቀር ተገልጿል።

መመሪያው ረቂቅ በመሆኑ ከመፅደቁ በፊት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይቶ የጋራ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ ነው ያሉን ደግሞ የኮንስትራክሽን ስልጠና ክፍል ተጠሪ እና በመመሪያ ዝግጅቱ የጀነራል ዊንጌት ተወካይ የሆኑት አሰልጣኝ ኤፍሬም ጥላሁን ናቸው።

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍231
ሰኞ 10/03/2016 ዓ.ም ምዝገባ ይጀመራል በምስሉ ላይ የተገለፀውን ቅደም ተከተል በመከተል በ https://www.aatvetb.edu.et/ ድህረገፅ ገብተው ይመዝገቡ

Galmeen Wixataa (10/03/2016 A.L.H) eegalma, marsariitii https://www.aatvetb.edu.et/ seenuun tartiiba suuraa irratti mul'atu hordofuun galmaa'aa.

Registration Will start Monday( Nov 20/2023), log in to the website https://www.aatvetb.edu.et/ and register by following the order shown in the image.
👍12
Forwarded from Bank of Abyssinia
ባንካችን አቢሲንያ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን የአፖሎ የተማሪ አምባሳደር በማድረግ፣ አፖሎን ለደንበኞች በማስተዋወቅ እና በምዝገባ ባሳኩት መጠን የኮሚሽን ክፍያ ለመክፈል አስፈላጊውን ዝግጅት ጨርሷል፡፡ ስለሆነም የአፖሎ አምባሳደር ለመሆን ፍላጎት ያላቸውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አወዳድሮ ለመውሰድ ተዘጋጅቷል፡፡ ከተጨማሪ የገቢ ምንጭ ባለፈ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ሲወጡ የሥራ ልምድ ይሆናቸው ዘንድ ያላቸውን ችሎታ የሚያሳድጉበት፤ እንዲሁም እንደሚያሳዩት ውጤትና ተነሳሽነት ሌሎች ሽልማቶችን የሚያገኙበትን አጋጣሚ አቢሲንያ ባንክ ፈጥሯል፡፡
የዚህ እድል ተሳታፊ ለመሆን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ነጥቦች፣
የከፍተኛ ትምህርት እየተከታተላችሁ መሆኑን የሚገልፅ የተማሪ መታወቂያ፤
የአፖሎ አካውንት ባለቤት መሆን፤ ከ150 ቃላት ባልበለጠ ራሳችሁን የሚገልፅ አጭር ፅሁፍ እና
በቀላሉ ለመሙላት በተዘጋጀው የማመልከቻ ገጽ ከ150 ቃላት ባልበለጠ ለምን የአፖሎ አምባሳደር ለመሆን እንደፈለጋችሁ መግለፅ ብቻ ናቸው፡፡ ስለሆነም ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጠቀም ይመዝግቡ፡፡

https://apolsup.bankofabyssinia.com/studentAgent


ከአፖሎ ጋር ተፍ ተፍ በሉ፡፡
ከስራ በፊት ስራ ጀምሩ፡፡
ጠቀም ያለ የሪፈራል ኮሚሽንም አግኙ!
👍14