General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሰኞ፡- ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም   

      በኮሌጁ ለተለያዩ ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ!!

በኮሌጁ ለተለያዩ ሰራተኞች ልዩ ልዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ለ5 ቀናት ተሰጠ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ለአሰልጣኞች የኢኖቬቲቭ ፔዳጎጂ እና ለሴት ሰራተኞች ደግሞ የስርዓተ ፆታ ስልጠና ከጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት ተሰጥቷል፡፡

ለአሰልጣኞች በተሰጠው የኢኖቬቲቭ ፔዳጎጂ ስልጠና ላይ ከኮሌጁ አሰልጣኞች ባሻገር የሌሎች ኮሌጆች አሰልጣኞች እና በአካባቢው ከሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተውጣጡ መምህራን እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡ አሰልጣኞቹ በዘርፉ ላይ በማሰልጠን እና በማማከር አገልግሎት ሰፊ እውቀት እና የካበተ ልምድ ያላቸው ሲሆን ዘመኑን የዋጅ እና የሰልጣኙን ስነ ልቦና የተረዳ አሰልጣኝ ለመፍጠር ታቅዶ የተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ስልጠናው የእያንዳንዱን አሰልጣኝ አቅምን ከማሳደግ ባሻገር ከሌሎች ኮሌጆች እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ጋር ያለውን የስራ መስተጋብር ለማጠናከር ጭምር ታስቦ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በኮሌጁ ለሚገኙ ሴት ሰራተኞች woman empowerment ላይ ያተኮረ የስርዓተ ፆታ ስልጠና በባለሙያ ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናው ሴቶች ላይ ተፅዕኖ ከሚፈጥሩ ማህበራዊ እና ባህላዊ ሁነቶች ተጠብቀው ያለባቸውን ልዩ ልዩ ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ለማስቻል ነው ተብሏል፡፡ ሁለቱም ዓይነት ስልጠናዎች በስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ እና በልዩ ልዩ ምልከታ ጥናት መሰረት መካሄዳቸውን የኮሌጁ ተቋማት ልማት እና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን ቢሮ አሳውቆናል፡፡

      ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍5
ረቡዕ፡- ጥቅምት 21 ቀን 2016 ዓ.ም

የመጨረሻው መጀመሪያ!!

ኮሌጁን በአይሶ 9001፡2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ ለማስደረግ በሁሉም ሰራተኞች ዘንድ እየተከወኑ ያሉ የስራ ትጋቶች የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ነው፡፡

አይሶ /ISO – International Organization for standardization/ ዓለማቀፋዊ የጥራት መለኪያ ስርዓት ሲሆን 9001 ደግሞ ለጥራት ማናጅመንት ስርዓት /QMS – quality management system/ የተሰጠ ዓለማቀፋዊ ኮድ ነው፡፡ ኮሌጁን በአይሶ 9001፡2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ ለማስደረግ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ሰራተኞች እንድ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ ሆነው ስታንዳደርዱን ለማስጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

ኮሌጁ በአገልግሎት ዘርፍ የሚሰጠውን ዓለም አቀፋዊ የአይሶ ሰርተፊኬት በእጁ ለማስገባት የመጨረሻው መጀመሪያ ምዕራፍ ዋዜማ ላይ ይገኛል፡፡ የኮሌጁን አሰራር ለማዘመን እና የሚሰጠው አገልግሎት ፈጣን፣ ቀልጣፋ እና ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ተከውነዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት በተመደቡ አማካሪዎች አማካኝነት ከክፍተት ዳሰሳ ጥናት እስከ ሙሉ ትግበራ ምዕራፍ ድረስ ለረጅም ጊዜ ክትትል እና ድጋፍ ሲደረግ ቆይቶ አሁን ላይ የመጨረሻውን የውጪ ኦዲት ምርመራ ለማከናወን ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ተይዟል፡፡ ይህ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው፡፡

167 ሀገራት አባል የሆኑበት ISO ለ1.3 ሚሊዮን ድርጅቶች የጥራት መለኪያ ስርዓት ሰርተፊኬት ያበረከተ ሲሆን ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም የዚህን ልኬት ምስክር ወረቀት ለመቀበል የሚወስነው የቀጣይ ሳምንት የኢንስፔክሽን ውጤት ነው፡፡ ለትግበራው መጨረሻ ለሰርተፊኬቱ ደግሞ መባቻ በሆነው ሳምንታዊ ሸር ጉድ በሁሉም የስራ ዘርፍ ላይ የሚገኙ አጠቃላይ የኮሌጁ ማህበረሰብ በትጋት ድርሻቸውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍19
Forwarded from Mekdes Abay
👍3
አርብ፡- ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ታላቅ የምስራች ነው እንኳን ደስ አላችሁ!!

ኮሌጁ በአይሶ 9001፡2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ ሆነ!!

ኮሌጁን በአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ ለማስደረግ ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት በመጡ ኦዲተሮች የጥራት ኦዲት ሲደረግ ቆይቶ አሁን ላይ የጥራት ማናጅመንቱን ስርዓት ማሟላቱ ተገልጿል፡፡

ኮሌጁን በአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ ለማስደረግ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ለ10 ወራት ያህል ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች ስታንዳደርዱን ለማስጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡

በዚህ ሁሉን አቀፍ ቅንጅታዊ የስራ ትጋት ኮሌጁ ዓለም አቀፋዊ የጥራት አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህ ስኬት ኮሌጁ በ2022 ዓ.ም በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ እውን ለማድረግ መንገድ የጠረገ ሂደት ነው፡፡

ይህ እውቅና ይገኝ ዘንድ በተለያየ ደረጃ ላይ የምትገኙ የተቋሙ አመራር አካላት የመሪነታችሁ ሚና የላቀ ነው እና እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ የኮሌጃችን አሰልጣኞችና የልዩ ልዩ ዘርፍ ባለሙያዎች ቅንጅታዊ ተሳትፏችሁ እና ያልተቋረጠ ትጋታችሁ ፍሬ አፍርቶ ይህንን ውጤት ለማየት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡ አሁን ላይ እየሰለጠናችሁ ያላችሁ ሰልጣኞቻችን እና ከዚህ በፊት በተለያዩ ዘመናት በኮሌጃችን በልዩ ልዩ ሙያዎች ሰልጥናችሁ የነበራችሁ ቤተሰቦቻችን ኮሌጃችሁ በዓለም አቀፍ ስታዳርድ መመዘገቡን ስታውቁ የሚሰማችሁ ደስታ ታላቅ እንደሆነ ስለምንገነዘብ እናንተምን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን፡፡ በዝርዝር እና በቁጥር ገልፀን የማንጨርሳችሁ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆናችሁ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የእናንተ ከፍተኛ አጋርነት ድምር ውጤት ኮሌጃችንን ወደ አንደኛው የስኬት ምዕራፍ እንዲሸጋገር አበርክቷችሁ ከቃላት በላይ ነው እና እናንተም በያላችሁበት አንኳን ደስ አላችሁ፡፡

ኮሌጁ በዚህ የጥራት አመራር ስርዓት ማለፉ የደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማርካት፣ የተቋማችንን ገጽታ ለማሳደግ፣ ቀጣይ እና ተከታታይ ለውጥ ለማምጣት፣ የሰራተኞችን ተሳትፍ ይበልጥ ለማጎልበት፣ ስራዎችን አቀናጅቶ ለማስራት እና መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ ለመስጠት ያስችለዋል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍33
ቅዳሜ፡- ህዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም

ኮሌጁ አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቀቀ!!

ኮሌጁ የ2016 ዓ/ም አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል የሚያበቃውን ሁሉን አቀፍ ቅድመ ዝግጅት አጠናቀቀ፡፡

በሰው ሀብት አቅም ግንባታ ስራ፣ በስልጠና ግብዓት ማሟላት፣ በአደረጃጀት እና በአሰራር ስርዓት መዋቅራዊ ዝግጅት እና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሰፊ ተግባራትን በማከናወን ዘመኑን የዋጀ ስልጠና ለመስጠት ግዙፍ ዝግጅት አድርጓል፡፡

ኮሌጁ አሁን ላይ ወደ 2000 የሚጠጉ ነባር ሰልጣኞች ሲኖሩት አጠቃላይ በሶስቱም የስልጠና መርሃ ግብሮች ማለትም በቀን፣ በማታ እና በቅዳሜ እና እሁድ በቀጣይ አዳዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስልጠን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በየደረጃዎቹ የሚያስቀመጥጠውን የመቁረጫ ነጥብ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

በኮሌጁ ስልጠና የሚሰጥባቸው የዲፓርትመንት ብዛት 12 ሲሆኑ የሙያ ዘርፎቹ ደግሞ 48 ናቸው፡፡ በአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ የሆነውን ኮሌጃችንን ፈጥናችሁ ለመቀላቀል በጉጉት እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ በርካታ አዳዲስ አመልካቾች እንዳላችሁ እንገነዘባለን፡፡ በእርግጥም ምርጫችሁ ትክክለኛ ቦታ ነው፡፡ በጥቂት ዓመታት ውስጥ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፖሊ ቴክኒክ ለመሆን ራዕይን አንግቦ እየተጋ ያለ አንጋፋ የስልጠና ተቋም ነው፡፡

ውድ ደንበኞቻችን እኛም እናንተን ተቀብለን ምርጫችሁን መሰረት ያደረገ ሙያዊ ስልጠና ለመስጠት የምንጠብቀው የስልጠና መቁረጫ ነጥቡን የመጀመሪያ ደወል ነውና ወቅታዊ መረጃዎቻችንን በቻናሎቻችን ሁል ጊዜ ይከታተል፤ የመረጃ ማድረሻ ገጾቻችንንም ለሌሎች በማሳወቅ እንዲቀላቀሉ አድርጉ፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍56