ቅዳሜ፡- ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም
የዲፓርትመንቶች ቅኝት
ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት
በዛሬው የዲፓርትመንቶች ቅኝት ቀዳሚ እይታችን ያደረግነው የኮንስትራክሽን ስልጠና ከፍልን ነው። ኮሌጁ በሀገር አቀፍ ደረጃ በጣም ጥቂት እና በከፍተኛ ውድድር ተመርጠው የሚገቡ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ተማሪዎችን መቀበል አቁሞ ወደ ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ሲሸጋገር አሀዱ ብሎ የጀመረው በዚህ የስልጠና ዘርፍ ነው።
የዛሬ 43 ዓመት 1973 ዓ.ም የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ሲጀምር የኮነስትራክሽን እና ሙያ ት/ቤት በሚል ስያሜ ሲሆን ስልጠና ክፍሉ ቀዳሚውን ቦታ መያዝ ብቻ ሳይሆን የታሪክ ባለቤትነትን ድርሻ ይወስዳል። በወቅቱ በሶቬት ህብረት /ራሻያ/ የቴክኒክ ተራዲኦ ድርጅት አማካኝነት በመታገዝ እንደ ሀገር ብቃታቸው የተረጋገጠ እንቁ ባለሙያዎችን በማፍራት አኩሪ ገድሉን አጽፏል።
በጊዜው እንደ ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ሲሰጡ የነበሩ ሙያዎች 6 ሲሆኑ እነሱም ኤሌክትሪክሲቲ፣ ኤሌክትሮ ጋዝ ዌልዲንግ፣ ፕላምቢንግ፣ ፔንቲንግ ፕላስተሪንግ፣ ውድ ወርክ እና ሬንፎርስመንት ናቸው። እነዚህን ስልጠናዎች ውጤታማ ለማድረግ ኢትዮጵያዊያን እና ከሩሲያ የመጡ መምህራን በትጋት ሰርተዋል።
ውሎ እየታደር ዘመን እየተቆጠረ አዲስ የትምህርት ፖሊሲ ሽግግር መፈጠሩን ተከተሎ ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙ ከኮንስትራክሽን እና ሙያ ት/ቤት ወደ ኮንስትራክሽን እና ሙያ ኮሌጅ ስያሜ ሲቀየር ስልጠና ክፍሉ በቢውልዲንግ ኮንስትራክሽን፣ በሮድ ኮንስትራክሽን፣ በዲራፍቲንግ ቴክኖሎጂ፣ በሰርቬይንግ ቴክኖሎጂ እና በውድ ወርክ ቴክኖሎጂ ስልጠና ሲስጥ ቆይቷል።
የስልጠና ሙያ ፍላጎት እየረቀቀ እና እያደገ መምጣቱን ተከተሎ በስሩ የነበሩ ልዩ ልዩ ሙያዎች በተለያየ ጊዜ ራሳቸውን ችለው ዋና የስልጠና ክፍል በመሆን ሲወጡ አሁን ላይ በቢውልዲንግ እና ሮድ ኮንስትራክሽን ላይ ባሉ ልዩ ልዩ ሙያዎች እያሰለጠነ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ ስትራክቸራል ኮንስትራክሽን ወርክ፣ ፊኒሽንግ ኮንስትራክሽን ወርክ፣ ፐላምቢንግ ኢንስታሌሽን እና ሮድ ኮንስትራክሽን እና ሜንቴናንስ ስልጠና ክፍሉ እየሰጣቸው ያሉ ሙያዎች ናቸው።
ዲፓርትመንቱ አሁን ላይ 55 ወንድ እና 7 እንስት በአጠቃላይ 62 አሰልጣኞች ሲኖሩት 8 ኤ ደረጃ ኢንስትራከተር፣ 48 ቢ ደረጃ አሰልጣኝ፣ 2 ሲ ደረጃ ወርክ ሾፕ ቴክኒሺያን ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ለተለያዩ ደረጃዎች ስልጠና ላይ ይገኛሉ።
ዲፓርትመንቱ አሁን ላይ ለነባር መደበኛ እና የአጫጭር ጊዜ ሰልጣኞችን ከማሰልጠን ባሻገር በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የቢሮ እድሳት በማደረግ፣ በኮሌጁ እየተስሩ ያሉ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች በማከናወን፣ በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት በመስራት እና መሰል ተግባራትን በቅንጅት እየተገበረ ይገኛለል።
ስልጠና ክፍሉ ቀጣይም አዳዲስ ሰልጣኞችን በክብር ተቀብሎ ዘመኑ በደረሰበት የስልጠና ደረጃ ተራማጅ አመለካከት እና በተግባር የተፈተነ ክህሎት ያለው ዜጋን ለማፍራት ዝግጅቱን አጠናቆ እየተጠባበቀ ይገኛል።
ቀጣይ የሌሎች ዲፓርትመንቶችን ቅኝት እንደምንዳስስ ከወዲሁ እንጠቁማል።
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍14
Forwarded from General Wingate Polytechnic college-Official channel
የመመዝገብያ ፎረማችን የነበረበት ችግር ተቀርፎዋል ይህንን ተጠቅመው ይመዝገቡ
The problem with our registration form has been solved. Register using this https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfx3PGn4-PwdmV92p5ggp8jtegBswIH7IBAJbKb7kYhwgu7tw/viewform

Google Docs
20 E.C New Trainees Registration Form
2016E.C New Trainees Registration Form
ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2016 ዓ.ም
አዲስ አመልካች ሰልጣኞችን መመዝገብያ ቅፅ
ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2016 ዓ.ም
አዲስ አመልካች ሰልጣኞችን መመዝገብያ ቅፅ
👍8👎1👏1
General Wingate Polytechnic college-Official channel pinned «የመመዝገብያ ፎረማችን የነበረበት ችግር ተቀርፎዋል ይህንን ተጠቅመው ይመዝገቡ The problem with our registration form has been solved. Register using this https://docs.goo…»
Forwarded from General Wingate Polytechnic college-Official channel
የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የተገልጋይ አስተያየት ማቅረብያ ፎርም
General Wingate Polytechnic College
User feedback form ወይም የሚከተለውን ሊንክ የጫኑ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfwOsDFZhaRhaXxvyOx_yxGRr6yAoZKhP3c978BPM-UT1L8nA/viewform?usp=pp_url

👍2
Forwarded from General Wingate Polytechnic college-Official channel
የመመዝገብያ ፎረማችን የነበረበት ችግር ተቀርፎዋል ይህንን ተጠቅመው ይመዝገቡ
The problem with our registration form has been solved. Register using this https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfx3PGn4-PwdmV92p5ggp8jtegBswIH7IBAJbKb7kYhwgu7tw/viewform
The problem with our registration form has been solved. Register using this https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfx3PGn4-PwdmV92p5ggp8jtegBswIH7IBAJbKb7kYhwgu7tw/viewform
Google Docs
20 E.C New Trainees Registration Form
2016E.C New Trainees Registration Form
ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2016 ዓ.ም
አዲስ አመልካች ሰልጣኞችን መመዝገብያ ቅፅ
ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2016 ዓ.ም
አዲስ አመልካች ሰልጣኞችን መመዝገብያ ቅፅ
👍5
ሰኞ፡- ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም
ከተለያዩ የቻይና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የተውጣጡ ልዑካን ቡደን አባላት ኮሌጁን ጎበኙ!!
ከ13 የቻይና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የተውጣጡ ዲኖች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የተካቱበት ከ40 በላይ አባላት ያሉት ልዑካን ቡደን ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ኮሌጁን ጎበኙ፡፡
ይህ በቻይና አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ልምድ ልውውጥ አካል በሆነው መርሃ ግብር ላይ በኮሌጁ ተገኝተው ምልከታ ያደረጉት የተቋማቱ መሪዎች የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማጠናከር ባሻገር ቀጣይ በሰው ሀብት ልማት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአሰልጣኞች እና ሰልጣኞች ስልጠና እና በተቋማዊ አመራር ዙሪያ ከኮሌጁ ጋር በትብብር ለመስራት ታቅዶ የተደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በጉብኝቱ የማሰልጠኛ ወርክ ሾፖችን፣ የተቋሙን አጠቃላይ ስነ ምህዳር፣ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ምልከታ አደርገዋል፡፡
ለቻይና አሁናዊ ዕድገት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትልቅ ሚና ስለነበረው ተቋማዊ ትብብሩ ለእኛም እንደ ሀገር በኢኮኖሚ እድገትና በዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ በሚያበረክት መልኩ ትብብር ለማድረግ ታቅዶ እንደተካሄደ ተነግሯል፡፡
ኢትዮጵያና ቻይና በመሰረተ ልማት፣ በግብርናው መስክ፣ በቴክኖሎጂዎች ማሸጋገር እና በተለያዩ ስልጠናዎች በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

👍10
Forwarded from General Wingate Students Channel
በስልጠና ላይ ለሚኖር ቅሬታ እንዲሁም ጥቆማ ካለ @Gw2016bot ማሳወቅ ትችላላችሁ።
👍6❤1