ማክሰኞ:- መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም
የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በኮሌጁ ጉብኝት አደረጉ!!
የአዲስ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሌጁ ትምህርታዊ ጉብኝት አደረጉ፡፡
በዕለቱ ከ150 በላይ የሚሆኑ እና ከ11ኛ ክፍሎች የተውጣጡ ተማሪዎች ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የኮሌጁን ተቋማዊ ስነ ምህዳር እና አጠቃላይ የስራ እንቅሰቃሴ ገለፃ ተሰጥቷቸው የልዩ ልዩ ዲፓርትመንቶችን ወርክሾፖች እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡
የጉብኝቱ መሰረታዊ ዓላማ ቀጣይ የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱ በኋላ ወደ ቴክኒክና ሙያ ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች ስለ ሙያ ስልጠና ከአሁኑ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው እና ለምርጫ እንዳይቸገሩ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡
ከዚህ ባሻገር አሁን ላይ እስከ ደረጃ 2 ያለውን የሙያ ስልጠና ከቀለም ትምህርት ጋር አቀናጅተው ስለሚማሩ ወርክሾፖችን በመጎብኘት መሰረታዊ መረጃ ለማሰጨበጥ ይረዳል መባሉንም ሰምተናል፡፡
ተማሪዎቹ በተሰጣቸው ማብራሪያ እና በጉብኝት ወቅቱ ባዩት የስራ እንቅስቃሴ በጣም እንደተደሰቱ ገልፀው የሙያ ትምህርት ለመማር ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው ምስክርነትን ሰጥተዋል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

አርብ፡- መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም
በኮሌጁ የስራ አፈፃፀምና የሪፎርም ትግበራ ግምገማ ተካሄደ!!
ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት የኮሌጁ የ8 ወር ዕቅድ አፈፃፀም እና የስራና ክህሎት ቢሮ የሪፎርም ትግበራ ሂደት ቀርቦ ውይይት ተደረገበት፡፡
በውይይቱ ላይ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ አካማሪ አቶ ቸርነት በላቸው፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ እና የኮሌጁ አመራሮች ተገኛተዋል፡፡
እንደ ኮሌጅ ከአዲሱ የቴክኒክና ሙያ እሳቤ አተገባበር ጋር በተያያዘ ያለውን አፈፃፀም ያቀረቡት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ሲሆኑ በተቋሙ ከ11 የቴክነክና ሙያ ዘረመሎች /DNA/ አንፃር የተከናወኑ አበየት ተግባራትን በየዘርፉ አቅርበዋል፡፡
በዚህም ተቋሙን ለሰራተኞችና ሰልጣኞች ምቹ ከማድረግ ረገድ፣ የኢንዱስትሪዎችን ገበያ ፍላጎት ያደረገ ስልጠና ከመስጠትና ከግሉ አልሚ ጋር በአጋርነት ከመስራት አንፃር፣ በአካባቢ ፀጋ ለይቶ ከማሰልጠንና ተቋማዊ ኢንተርፕራይዞችን ፈጥሮ የሀብት ማግኛ ከማድረግ አኳያና መሰል ሀሳቦች በአፈፃፀሙ ተገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የከተማ አስተዳደሩ ስራና ክህሎት ቢሮ የሰራቸውንና እያከናወናቸው ያሉትን የሪፎርም ትግበራ ያቀረቡት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የቢሮ አካማሪ አቶ ቸርነት በላቸው ሲሆኑ አሰራሩን ማስተካከል፣ አመራሩን መልሶ ማደራጀት፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ የስራ አካባቢን ለአገልግሎት ምቹ ማድረግ፣ የዲሲፕሊን ክፍተቶች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰድ የሚሉት ሲተገበሩ በቀጣይ መረጃዎችን በቴክኖሎጂ አጠናክሮ መቀጠል፣ የተቋማት አካባቢያዊ ፀጋ ልየታን መተግበር፣ የኮሌጆችን ኢንተርፕራይዞች አጠናክሮ ማስቀጠል የሚሉት ተግባራት ይገኙበታል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎችም በቀረበው ተቋማዊ አፈፃፀምና ቢሮው እየተገበረው ባለው የሪፎርም ስራ ጠንካራ አቅሞች ናቸው ያሏቸውን አድንቀው፤ ማስተካከያ ቢደረግባቸው የሚሏቸውን ደግሞ ገንቢ አስተያየቶች አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም ከመድረኩ የማጠቃለያ ምላሾች ተሰጥተው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

ረቡዕ:- መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም
የመስከረም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በኮሌጁ የሚሰጠውን የሙያ ስልጠና ምልከታ አደረጉ!!
በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኘው መስከረም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሌጁ ትምህርታዊ ጉብኝት አደረጉ፡፡
በዕለቱ 135 የሚሆኑ ተማሪዎች ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የኮሌጁን ተቋማዊ ስነ ምህዳር እና አጠቃላይ የስራ እንቅሰቃሴ ገለፃ ተሰጥቷቸው የተለያዩ ዲፓርትመንቶችን ወርክሾፖች እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡
የጉብኝቱ መሰረታዊ ዓላማ አሁን ላይ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፉ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ በተጓዳኝነት የሚሰጥ በመሆኑ ስለሙያ ስልጠና አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው፡፡
ተማሪዎቹ እየተማሯቸው የሚገኙትን የሙያ ዘርፍ ስልጠና ወርክሾፖች የተመለከቱ ሲሆን እነሱም ኮንስትራክሽን፣ ጋርመንት /ልብስ ስፌት/፣ ከተማ ግብርና እና ሆቴል / ምግብ ዝግጅት/ የተግባር ስልጠና መስጫዎችን ተመልክተዋል፡፡
ተማሪዎቹ በተሰጣቸው ማብራሪያ እና በጉብኝት ወቅቱ ባዩት የስራ እንቅስቃሴ በጣም መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡
ሰሞኑን የአዲስ ከተማ እና የጀ/ ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች በተመሳሳይ በተቋሙ ትምህርታዊ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የኮሌጁን የሙያ ስልጠና ሂደት የተለያዩ ት/ቤቶች ጉብኝት እንዲያደርጉ የሚያስተባብረው በኮሌጁ የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን ቢሮ ስር የስራ ትስስርና ካውንስሊንግ የስራ ክፍል ነው፡፡

አርብ:- መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም
በኮሌጁ አሰልጣኞች የተሰራ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ቀረበ!!
ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በቡድን የሰሩ አሰልጣኞች የጥናት ውጤት ሰነዳቸውን በትናንትናው ዕለት ለውውድር አቀረቡ።
በዚህ ውድድር 5 የጥናትና ምርምር ሰነዶች ለባለሙያዎች ቀርበው ምዘና የተደረገባቸው ሲሆን በሁሉም ዘርፎች የተሰሩ የምርምር ተግባራት የኮሌጁን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ይረዳሉ ተብሏል።
የተግባራዊ ጥናትና ምርምሩ ዓላማ እንደ ተቋም የራስን ችግር በራስ አቅም ለመፍታት ያቀደ ሲሆን ሁሉም ጥናቶች የተነሱበትን ክፍተቶች ለመሙላት የሚችሉ ናቸው ተብሏል።
በውድድሩ ርዕሰ ጉዳዩ አንገብጋቢ ችግር መሆኑ፣ ከችግሩ ጋር የተሰናሰለ ዓላማ መቀረጹ፣ ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ርቀት፣ በምርምር ሂደቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ወዘተ የሚሉ መስፈርቶች ተካተዋል።
እንደ ተቋም 9 ተግባራዊ ጥናትና ምርምር እየተሰራ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለግምገማ የቀረቡት 5ቱ ናቸው።
አሸናፊው ሰነድ እንደ ከተማ በቴክኒክና ሙያ ሳምንት ከአቻ ተቋማት ስራ ጋር ውድድር የሚጠብቀው ሲሆን ባለፈው ዓመት በኮሌጁ የተሰራው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በከተማ ደረጃ አንደኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ አይዘነጋም፡፡
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"