General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
Forwarded from FDRE TVT Institute
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የአመራሮች ካውንስል የመጀመሪያውን መደበኛ ጉባዔ ማካሄድ ጀመረ፡፡
የካቲት 07/2017 ዓ.ም**

የኢትዮጵያን የክህሎት ልማትን በማሳደግ ለአገር እድገት ጠቃሚ ሚና እንዲጫወት የተቋቋመው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የአመራሮች ካውንስል የመጀመሪያውን መደበኛ ጉባዔ በቢሾፍቱ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመክፈቻው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በበጀት ዓመቱ እያሳካ ባላቸው ስራዎች የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡


በአገራችን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ከተለመደ አሠራር የተሻለ ለውጥ ያመጡበት እንደነበር የገለጹት ክብርት ሚኒስትሯ እነዚህ እየታዩ ያሉ ውጤታማ ስራዎች ባህል እንዲሆኑ በማድረግ ወደ ላቀ የስኬት ምእራፍ ለመሸጋገር የመሪዎች ካውንስል ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትር አያይዘውም ዓመተ-ማጽናት ተብሎ በተሠየመው ዓመት የሚካሄድ የመጀመሪያ ጉባኤ በመሆኑ ድርብ ትርጉም እንዳለው ተናግረዋል።


የሚኒስቴሩ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) በበኩላቸው ይህ ካውንስል ተቋማት በራሳቸው የሚመካከሩበት ለውጥ የሚያመጣ ሐሳብ የሚያፈልቁበት መድረክ እንደሆነ ገልጸዋል።

የካውንስሉ ውይይቶች ተቋማት ልምድ በመለዋወጥ በተቋማት መካከል የአፈጻጸም መቀራረብን የሚያመጡበት ፤ የዘርፉን ገጽታ ግንባታ የሚያጠናክሩበት እና ተደማጭነታቸውን የሚያስዱጉ ሃሳቦችን የሚያፈልቁበት ጉባኤ ይሆናልም ብለዋል።


የቴክኒክና ሙያ ስልጠና አመራሮች ምክርቤት ከተቋቋመ ጀምሮ ሰነድ በማዘጋጀት፣ በቀጠናዊ ትስስር የቴክኒክና ሙያ ደንብ እንዲካተት በማድረግ፣ በኮሌጆች መካከል የልምድና ሀብት ልውውጥ በማድረግ፣ ለምክር ቤቱ ምቹ መደላድል የመፍጠር ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን የየገለጹት ደግሞ የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አቶ መለስ ይግዛው ናቸው፡፡


የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩቱ ካውንስሉን ከመመስረት ጀምሮ ጉባኤውን ከማካሄድ አኳያ ቁልፍ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን በጉባኤው ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክ ከድርና ም/ዋና ዳይሬክተሮችን ጨምሮ የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡

ዌብሳይት http://www.ftveti.edu.et/
ፌስቡክ https://www.facebook.com/TVTI.EDU.ET
ቴሌግራም https://t.me/fdretvtinstitute
ቲክቶክ www.tiktok.com/@fdretvtistitute
ሰኞ:- የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ∙ም

   በመሰረተ ልማት ግንባታ የአሰልጣኞች ትሩፋት እንደ ቀጠለ ነው፡፡

የኮሌጁን ተቋማዊ ገጽታ ሳቢና ምቹ ለማድረግ በርካታ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን አሁንም አሻራን በታሪክ ሰነድ ውስጥ ለማስቀመጥ የሚደረገው መታተር እንደ ቀጠለ ይገኛል፡፡

በህንፃና ቢሮ ዕድሳት፣ በእግረኛ መንገድ ስራ፣ በፋውንቴን ስራዎች፣ በከርቭ ስቶን ስራና በመሳሰሉት እንቅስቃሴዎች ላይ የኮንስትራክሽን ዘርፍ አሰልጣኞች ያበረከቱት አስተዋጽኦ የአንበሳውን ድርሻ ይጋራሉ፡፡

በዛሬው ቅኝታችን ደግሞ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰልጣኝ በሚስተናገድባቸውና በርካታ ወርክሾፖች በሚገኝባቸው በተለምዷዊ አጠራር ገርጂ በሚባለው አካባቢ የእግረኛ መንገድ ግንባታና ፋውንቴን ስራዎች ላይ እየተጉ የሚገኙ አሰልጣኞችን ተመልክተናል፡፡

ይህ አካባቢ ብዙ የስልጠና እንቅስቃሴ መኖሩ ብቻ ሳይሆን በኮሌጁ የኮሌጁ ሦስተኛ በር የሚገኝበት እና  ዘመናዊ ሆኖ የተሰራው አዲሱ የካፊና ሬስቶራንት አዳራሽ ያለበት ነው፡፡

በዚህ የእግረኛ መንገድ ግንባታ ላይ ሶፎንያስ ከድርና መለሰ ምንውየለት ከሺፈራው ካባና ትዛዙ ተረፈ ጋር በመተባበር 300 ሜትር ርዝመት ያለውን መንገድ ከ2 ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ሰርተው ለተጠቃሚው ክፍት አድርገዋል፡፡

ይህ ስራ በ2.5 ሜትር ስፋት የተገነባ ሲሆን አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ተደርጎ የተከናውነ ልማት ነው፡፡ የዚህ ስራ መከናወን የ3ኛ በር አገልግሎትን በጥሩ ሁኔታ ማሳለጥ የሚችል መሆኑን ተገንዝበናል፡፡ በሌሎች አሰልጣኞች እየተሰሩ ያሉ ተቋማዊ ስራዎችን በቀጣይ የምንዘግብ ሲሆን በባለቤትነት ስሜት እየተጋችሁ ያላችሁ ባለሙያዎችን   በርቱልን ማለት እንወዳለን፡፡

. "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"