General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ፡- ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

የኮሌጁ የሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ!!


የኮሌጁ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ የኮሌጁ ሰራተኞች በተገኙበት ዛሬ ህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

በዕለቱ በዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች በኮሌጁ የተከናወኑ የዝግጅት ምዕራፍ ሪፖርቶች ቀርበው ሀሳብ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት መረጃ መሰረት በሩብ ዓመቱ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ከማሟላት አንፃር፣ የተቋሙን መሰረተ ልማት ከማስተካከል አኳያ፣ ነባርና አዳዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ በአግባቡ ከማሰልጠን አንፃር እና ተጓዳኝ ስራዎችን ከመከወን ረገድ ያሉ እምርታዊ ለውጦች እና የነበሩ ክፍተቶች ለውይይት ቀርበው አቅጣጫ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በእቅድ አፈፃፀም ግምገማው ላይ የተገኙት ተሳታፊዎችም በኮሌጁ ያሉ ጥንካሬ እና ክፍተቶችን ›አንስተው መድረኩ በቀጣይ የስራ አቅም እና ተነሳሽነት እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ለኮሌጁ ሰራተኞች እና ሰልጣኞች

በኮሌጁ ግቢ ውስጥ ከ14/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ የብሔራዊ መታወቅያ ምዝገባ እየተከናወነ ስለሆነ በፍጥነት በመመዝገብ የእድሉ  ተጠቃሚ እንድትሆኑ።

ቦታ በኮሌጁ ግቢ ፔፕሲ ሱቅ አጠገብ።
ሰኞ፡- ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም

በኮሌጁ የፀረ  ሙስና ቀን ተከበረ!!

ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ምክኒያት በማድረግ እንደ ተቋም ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሌጁ የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ፡፡

በዓለም ለ21ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የፀረ ሙስና ቀን በኮሌጁ የስነምግባር እና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት "ወጣቶችን ያማከለ የፀረሙስና ትግል፤ የነገን ስብዕና ይገነባል" በሚል መሪ ሀሳብ የኮሌጁ ሰራተኞችና ሰልጣኞች በተገኙበት ተከብሯል።

በዓሉ በፀረ ሙስና ትግሉ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን ለማስቀጠል፣ የትውልድ ስነ ምግባር ግንባታን ለማጠናከር፣ የፀረ ሙስና ትግሉን ህዝባዊ መሰረት በማስያዝ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ታቅዶ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሙስና በስነ ምግባር ውድቀት፣ በቢሮክራሲ መብዛት፣ በተጠያቂነት መጓደል፣ በዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማነስ፣ ባልተማከለ የአሰራር ስርዓት እና መሰል መንስኤዎች የሚከሰት ሲሆን አፈፃፀሙ በጊዜ ሂደት እየሰፋ እና እየረቀቀ በመምጣቱ የሀገርን ሀብት ከዚህ አስከፊ ጥፋት ለመታደግ ሁሉም አካላት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ተብሏል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"