General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ማክሰኞ:- መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም

የኮሌጁ የስነ ምግባርና ፀረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት እቅድ ውይይት ተደረገበት!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስነ ምግባርና ፀረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት የ 2017 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ትናንት መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

ዳይሬክቶሬቱ በተያዘው በጀት ዓመት ትኩረት አድርጎ የሚሰራቸውን የክትትልና የግንዛቤ ስራዎችን የሚያሳይ እቅድ የኮሌጁ ሰራተኞች በተገኙበት አቅርቦ አወያይቷል፡፡

በዕለቱ ለውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ የተቋማት ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ሰባሁዲን ሁሴን ሲሆኑ ም/ዲኑ በንግግራቸው በ2017 በጀት ዓመት ዳይሬክቶሬቱ መልካም አስተዳደር የበለጠ እንዲሰፍን እና የሙስናና ብልሹ አሰራር እሳቢዎችና ተግባራት እንዳይፈጸሙ ለመከላከል በትኩረት ለመስራት ያግዘው ዘንድ እቅዱን ለባለድርሻ አካላት ማሳወቁ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡::

በወቅቱ የስራ ክፍሉን እቅድ ለተሳታፊዎች ያቀረቡት ደግሞ የኮሌጁ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት አቦነህ ናቸው፡፡ ዳይሬክተሯ ከእቅድ ውይይት ባሻገር እንደ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከናወነውን የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ተግባር ገለፃ በመስጠት ቀጣይ ሁሉም ሰራተኞች በተዘጋጀው ቅጽ መሰረት የሀብታቸውን መጠን የሚሞሉበትን ሂደት አሳውቀዋል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ሐሙስ፦ መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ∙ም

ለኮሌጃችን የክርስትና እምነት ተከታይ ሰራተኞች፣ ሰልጣኞች እና አጋሮቻችን እንኳን ለ2017 ዓ.ም የደመራ እና የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የበጎነት ይሆንላችሁ ዘንድ ምኞታችን የላቀ ነው።

                የጀነራል  ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
በአዲስ ምዝገባና ሌሎች ጉዳዮች ጥያቄ ካላችሁ አሁን live ላይ ነን ግቡና ጠይቁ
ቅዳሜ፡- መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የቀድሞዎቹ የጀነራል ዊንጌት ተማሪዎች ከግማሸ ክፍለ ዘመን ቆይታ በኋላ ተገናኙ!!

የቀድሞው ጀነራል ዊንጌት አዳሪ ት/ቤት ተማሪዎች የነበሩ በ50ኛ ዓመታቸው ዛሬ መስከረም 18 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሌጁ ተገናኙ።

የዛሬዎቹ እንግዶች ከተለያዩ የሀገራችን ግዛቶች በ8ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የመጨረሻዎቹ አዳሪ ተማሪዎች ሆነው ልክ በዛሬዋ ዕለት መስከረም 18 ቀን 1967 ዓ.ም ጀነራል ዊንጌት አዳሪ ት/ቤትን ተቀላቀሉ።

ጀነራል ዊንጌት ት/ቤት እግራቸው የረገጠበትን ቀን 50ኛ ዓመት ምክኒያት በማድረግ በዛሬው ዕለት ከያሉበት ቦታና የኑሮ ሁኔታ ተሰባሰበው የዊንጌት ትዝታቸውን ሲያወጉና ሲጎበኙ ቆይተዋል።

የቀድሞዎቹ ተማሪዎች የበርካታ ክህሎት ባለጸጋዎችና ሀገራቸውን በልዩ ልዩ የሙያ መስክ ሲያገለግሉ የነበሩ ሲሆን ለበርካታ ስኬታቸው መነሻ የጀነራል ዊንጌት ቆይታ ታላቅ አስተዋጽኦ እንደነበረው ገልጸዋል።

የጀነራል ዊንጌት ቆይታቸውን አጠናቀው ህይወት በመራቻቸው ጎዳን የተበተኑት የቀድሞዎቹ ተማሪዎች ጀነራል ዊንጌትን የተቀላቀሉበትን ወደ ኋላ 50 ዓመታትን ቆጥረውና ከያሉበት ተጠራርተው የቀድሞ ት/ቤታቸውን እንደ መሰብሰቢያ ጥላ በመቁጠር በዛሬው ዕለት በናፍቆት ተገናኝተዋል።

ያ የልጅነት ዕድሜ ልዩ ትዝታ እንደ ማግኔት ስቦ አንድ ላይ ያሰባሰባቸው የቀድሞዎቹ ተማሪዎች በብዙ የህይወት ውጣ ውረድ ተፍትነውና በብዙ የዓለማችንና የሀገራች ክፍሎች ተበትነው ዛሬ ላይ መሰባሰብ ሲችሉ በተማሪነት የነበራቸውን ትውስታና ገጠመኝ ለማወጋት ችለዋል።

አንዳንዶቹ ከአገር ውጪ ሆነው ርቀት ገድቧቸው፣ አንዳዶቹ ደግሞ እርፍተ ዘመን ገትቷቸው ሌሎቹም በልዩ ልዩ ምክኒያቶች በዕለቱ ባይገኙም በልቦና መንፈስ ተቃቅፈው፣ ሃሳብ ለሃሳብ ተናበውና ለቀጣይ ገና በዓል ዳግም ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው ተለያይተዋል።

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
Saturday: September 28, 2024

The former students of General Wingate meet after half a century!!

Former students of General Wingate Boarding School met at the college on their 50th anniversary today, September 28, 2024.

Today's guests joined General Wingate Boarding School on this day, September 28, 1974, as the last boarding students from various states of our country who scored high marks in the 8th grade.

On the occasion of the 50th anniversary of the day General Winget set foot in the school, they have met from their current location and living conditions to discuss and visit their memories of Wingate.

The former students are rich in many skills and have been serving their country in different professional fields and they stated that General Wingate's stay had a great contribution to many of their success.

The former students who completed their stay at General Wingate and dispersed in the streets where they led their lives, counted back 50 years when they joined General Wingate and were swept away from where they were.

That special memory of childhood attracted and brought them together like a magnet. The former students who have faced many ups and downs in life and scattered in many parts of the world and country are able to come together today to talk about their memories and experiences as students.

Some of them were away from the country and some of them were not present on the day due to various reasons.

"Information access through Advanced Services"