አስቸኳይ ለአጠቃላይ የኮሌጁ ሰራተኞች
ዛሬ በቀን 05/10/16 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ላይ ስለምትፈለጉ በኮሌጁ አሮጌው አዳራሽ እንድትገኙ እናሳውቃለን።
ኮሌጁ

👍1
ረቡዕ:- ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም
በኮሌጁ የፓናል ውይይት መድረክ ተካሄደ!!
14ኛውን የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ምክኒያት በማድረግ ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ የፓናል ውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
በዚህ መድረክ ላይ የኮሌጁ ሰራተኞች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ ተወካዮች እና የፓናል ውይይት አቅራቢ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በዕለቱ በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ የመወያያ ጽሑፎች በሁለት የዘርፉ ምሁራን ተጋባዥ እንግዶች ቀርበዋል፡፡ አንደኛው በቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዓላማ፣ ስትራቴጂክ እና መርሆች ላይ ያተኮረ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በግሪን TVET፣ በዲጂታላይዜሽን፣ በተቋማዊ መሰረተ ልማት ግንባታ እና በአሰልጣኞች አቅም ማጎልበት ላይ መሰረት ያደረገ ሰፊ ትንታኔ ተሰጥቷል፡፡
በዚህ የፓናል ውይይት መድረክ የቴክኒክ እና ሙያ ዘርፍ በተቋም፣ በከተማ አስተዳደር፣ በሀገር ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ በጎ እምርታዎችና ፈታኝ ተግዳሮቶች በጥልቀት ተዳሰዋል፡፡
በወቅቱ የፓናል መድረኩ ተሳታፊዎችም ውስጣዊ እና ውጫዊ ተጽዕኖዎችን በማንሳት ከእያንዳንዳችን ምን ይጠበቃል የሚለውን ገንቢ ሀሳብ አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም በቀረቡ ሀሳቦች ላይ ማጠቃለያ ተሰጥቶ እና ቀጣይ መሰል መድረኮች በስፋት እንደሚኖሩ ተጠቁሞ የዕለቱ ዝግጅት ተጠናቋል፡፡
14ኛው የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ቴክኒክ እና ሙያ ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ቃል ከሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በከተማ ደረጃ በቴክኖሎጂ ኤግዚቪሽን እንደሚከበር መዘገባችን ይታወቃል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

👍8👌1
ረቡዕ:- ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም
የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በኮሌጁ ጉብኝት አደረጉ!!
የጀ/ ታደሰ ብሩ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ ጉብኝት አደረጉ፡፡
በዕለቱ ከ100 በላይ የሚሆኑ እና ከ10ኛ እና ከ12ኛ ክፍሎች የተውጣጡ ተማሪዎች ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የኮሌጁን ተቋማዊ ስነ ምህዳር እና አጠቃላይ የስራ እንቅሰቃሴ ገለፃ ተሰጥቷቸው የልዩ ልዩ ዲፓርትመንቶችን ወርክሾፖች እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡
የጉብኝቱ መሰረታዊ ዓላማ ተማሪዎቹ ቀጣይ የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱ በኋላ የተወሰኑት ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲያመሩ ቀሪዎቹ ደግሞ ወደ ተቋማችን የሚቀላቀሉ በመሆናቸው ከአሁኑ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው እና ለምርጫ እንዳይቸገሩ ያግዛቸዋል ተብሏል፡፡
ከዚህ ባሻገር አሁን ላይ 10ኛ ክፍል የሆኑ ተማሪዎች ቀጣይ የሙያ ስልጠናን ከቀለም ትምህርት ጋር አቀናጅተው ይማሩ ዘንድ አቅጣጫ በመቀመጡ እና ትግበራ በመጀመሩ ለእነሱም መሰረታዊ መረጃ ለማሰጨበጥ ይረዳል መባሉን ሰምተናል፡፡
ተማሪዎቹ በተሰጣቸው ማብራሪያ እና በጉብኝት ወቅቱ ባዩት የስራ እንቅስቃሴ በጣም እንደተደሰቱ ገልፀው የሙያ ትምህርት ለመማር ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው ምስክርነትን ሰጥተዋል፡፡
በተመሳሳይ ከሳምንታት በፊት ከአስራ ስምንት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ርዕርሳነ መምህራን እና ከሶስት ክፍለ ከተሞች ትምህርት ጽ/ቤቶች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች በኮሌጁ ተገኝተው የጋራ ምክክርና ጉብኝት ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

👍9❤2