General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ:- ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም

የባህላዊ ዕደጥበብ ስራዎችን ስልጠና ሲከታተሉ የነበሩ ሰልጣኞች አጠናቀቁ!!

ከሶስት ክፍለ ከተሞች ተውጣጥተው የተለያዩ ባህላዊ የዕደጥበብ ስራዎችን ሲሰለጥኑ የነበሩ ሰልጣኞች አጠናቀቁ፡፡

በኑሮ ማሻሻያ ሴፍትኔት መርሃ ግብር ተጠቃሚ የሆኑ እና ከአራዳ፣ ከአዲስ ከተማ እና ከጉለሌ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከ200 በላይ ሰልጣኞች ባህላዊ መገልገያ የሆኑ የዕደ ጥበብ ስራዎችን አመራረት ስልጠና ሲከታተሉ ቆይተው በዛሬው ዕለት አጠናቀዋል፡፡

ስልጠናው የቃጫ ቦርሳ እና የሰፌድ ስፌት ማምረት ሁለት ሙያዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን ከ3 ወር ቆይታ በኃላ ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡

ስልጠናው ኮሌጁ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ እና ኤልቢ /ELBEE/ ማኑፋክቸሪንግ ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው፡፡ ኤልቢ ማኑፋክቸሪንግ ድርጅት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን እና የሙያው አሰልጣኞችን ጨምሮ ሌሎች ኃላፊነቶችን በመወጣት ትልቁን አበርክቶ ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ከሰልጣኞቹ መካከል ጥሩ ችሎታ ያላቸው 40 ፐርሰንቱ በድርጅቱ በቋሚነት የሚቀጠሩ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በራሳቸው እየሰሩ ኑሯቸውን እንዲደጉሙ ይደረጋል መባሉንም ሰምተናል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍6
አርብ:- ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም

በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ የተመራ ልዑካን ቡድን በኮሌጁ ምልከታ አካሄደ!!

በኢፌዲሪ ስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ወ/ሮ ነበያ መሐመድ የተመራ ልዑካን ቡድን ዛሬ ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ የመስክ ምልከታ አካሄደ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ኮሌጆች ከአዲሱ የቴክኒክ እና ሙያ 4ቱ እሳቤዎች እና 11ዱ ዘረመሎች ትግበራ አንፃር ያሉበትን ደረጃ ምልከታ ለማድረግ አቅዶ እየሰራ ያለው የድጋፍ እና ክትትል ስራ ሲሆን በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተደረገውም የዚሁ አካል እንደሆነ ተገልፃል፡፡

ልዑካን ቡድኑ የተቋሙን አሁናዊ ቁመና በገለፃ፣ በምልከታ እና በውይይት የተመለከተ ሲሆን ኮሌጁ ባለበት ደረጃ እንደ ሀገር በብዙ ዘርፎች ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆኑ በርካታ የለውጥ እምርታዎች ያሉት መሆኑን ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡

ቡድኑ በተቋሙ ሁሉን አቀፍ ለውጥ እጅግ ተደምሞ ቀጣይ ኮሌጁ ትኩረት ሰጥቶና አጠናክሮ ሊሰራባቸው ይገባል ያላቸውን ተግባራት ምክረ ሀሳብ ሰጥቷል።

የአዲሱ ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርትና ስልጠና አራቱ እሳቤዎች የሚባሉት ስልጠና ከስልጠና በላይ፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ ከዳቦ በላይ፣ የስራ ዕድል ፈጠራ ከስራ በላይ እና የኢንዱስትሪ ሰላም ከግኝኙነት በላይ የሚሉት ናቸው፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍112
ቅዳሜ:- ሚያዚያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም

ለኮሌጁ እንሰሳት ተንከባካቢ ሰራተኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው!!

ለኮሌጁ የዶሮ እርባታ እና የወተት ላሞች እርባታ ጣቢያ ሰራተኞች በተቋሙ የከተማ ግብርና ዲፓርትመንት አሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

ስልጠናው ከዶሮ እርባታ አንፃር፣ ከውተት ላሞች እንክብካቤ ረገድ እና ከእንሰሳት ጤና አጠባበቅ አኳያ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ስልጠናውን ያዘጋጀው የንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ሲሆን ስልጠናውን የሰጠው ደግሞ የከተማ ግብርና ዲፓርትመንት ነው፡፡ ስልጠናው 15 ቀናት የተያዘለት ሲሆን 10ሩን በተግባራዊ ልምምድ የሚሸፈን እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የስልጠናው አስፈላጊነት ምርታማነትን ለማሳደግ እና የእንሰሳቱን አካላዊ ጤና ለመጠበቅ ታቅዶ መዘጋጀቱን የንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ደረጀ ጨመዳ ገልፀውልናል፡፡

የእንሰሳቱን ጤና መጠበቅ እና ምርታማነትን ማሳደግ የእንሰሳት ተዋጽኦ ምርት አቅርቦቱን ለኮሌጁ ማህበረሰብ ከመጨመር ባሻገር የዲፓርትመንቱን የስልጠና ሂደት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ይረዳል ያሉን ደግሞ የከተማ ግብርና ዲፓርትመንት ኃላፊ አቶ ታሪኩ በቀለ ናቸው፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍12👎1