General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ረቡዕ:- መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም

የታደሰው ካፌ ዛሬ በይፋ ስራ ጀመረ!!

ዕፁብ ድንቅ ሆኖ በመታደስ ዛሬ ስራ የጀመረው የኮሌጁ ሰራተኞች መዝናኛ ክበብ ከምን ተነስቶ የት እንደደረሰ የሚያስቃኝ በወፍ በረር ለመዳሰስ ሞከረን፡፡

ኮሌጁ በዚህ ዓመት ከሰራቸው የብዙ ብዙ ስኬቶች አንዱ ነባሩን የሰራተኞች ካፌ ስርነቀላዊ እና እምርታዊ በሆነ ለውጥ ማደስ ነው፡፡ የዚህ ፕሮጀክት ዋና መሪ የዲራፍቲንግ ቴክኖሎጂ አሰልጣኝ እና የአርትቴክት ባለሙያ አሰልጣኝ ሳሙኤል ኤሊያስ ናቸው፡፡ ለዚህ ስራ ተነሳሽነታችሁን ያመጣው ገፊ ምክኒያት ምንድን ነው የሚለውን ጥያቄ ለአሰልጣኝ ሳሙኤል አነሳን፡፡ ‹‹በኮሌጁ የበላይ ኃላፊዎች ተቋማዊ ለውጥን ለማምጣት በሚደረገው አዳዲስ ሀሳቦችን የማሰባሰብ ሂደት ላይ ተነስቼ በመጀመሪያ ደረጃ ለሰራተኞች ምቹ ከባቢ በመፍጠር ለሁሉም ሌሎች ተግባራት መነቃቃትን ይፈጥራል የሚል እምነት ስላደረብኝ እና ለዚህ ደግሞ ሰራተኛውን የመጠነ ዘመናዊ የሰራተኞች መዝናኛ ክበብ መኖሩ ግድ መሆኑን ስለተገነዘብኩ ይህንን እድሳት ለማድረግ አቅጄ ወደ ስራ ገባሁ፡፡›› ይላሉ አሰልጣኝ ሳሙኤል፡፡

በዚህ ዕድሳት ላይ ስታንዳርዱን ያስጠበቁ ልዩ ልዩ አዳዲስ ተግባራት የተከናወኑ ሲሆን በአጠቃላይ 530 ካሬ ሜትር የሚሸፍን ስራ በጥራት እና በስፋት ተከናውኗል፡፡ ሁሉም ነገር በአዲስ መልኩ ነው የተሰራው፡፡ ለዚህ ስራ እውቀታቸውን የገለፁ፣ ክህሎታቸውን ያሳዩ፣ ልምዳቸውን ያጋራ ባለ አሻራዎች ብዙ መሆናቸውን ከአሰልጣኙ አንደበት ሰምተናል፡፡ ሰፊውን የሲቪል ስራ ኮንስትራክሽኖች፣ በሚያምር ውበት የኤሌክትሪክ ዝርጋታውን ኤሌክትሪክሲቲዎች፣ በሚስብ ዲዛይን የጥልፍ እና መጋረጃ ስራዎችን ጋርመንቶች፣ ማራኪ የእንጨት ስራዎችን ውድ ወርኮች፣ ውብ አደረጃጀቱን ሆቴሎች፣ ልዩ ልዩ የብረታብረት ምርቶችን ሜታል ወርኮች ወዘተ በመተባበር ሁሉም በባለቤትነት ስሜት አሻራቸውን እንዳስቀመጡ ታውቋል፡፡

ይህ ስራ የእንጨት፣ የብረት ብረት፣ የኤሌክትሪክ ግባዓቶችን ጨምሮ አጠቃላይ ወጪ ወደ 13.5 ሚሊዮን ብር ኢንቨስት እንደተደረገበትም ከአሰልጣኝ ሳሙኤል መረጃ አግኝተናል፡፡

ለሰራተኞች ምቹ መዝናኛ ክበብን ከማደስ ባሻገር የስራው ሂደት ያመጣው ፋይዳ ይኖር ይሆን የሚል የመሰናበቻ ጥያቄ ለአርትቴክተሩ አነሳን፡፡ ‹‹በዚህ ስራ ላይ የተካፈሉ ብዙዎች እርስ በእርሳቸው በሙያቸው ልምድ ልውውጥ አድርገዋል፣ ከማሰልጠን ባሻገር ያለውን ሙያዊ ብቃት አሳይተዋል እንዲሁም ለሰልጣኞቻቸው የተግባር ልምምድ እንዲያደርጉ ዕድል ፈጥሮላቸዋል የሚል ሀሳብ ሰጥተውናል፡፡

አሰልጣኝ ሳሙኤል ከዚህ ፕሮጀክት ውጪም ስማርት ክላስ መፍጠር የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ ተጋርተው ለሁሉም ዲፓርመንቶች የተገጠሙ ኢንተራክቲቭ ቦርዶች እውን እንዲሆኑ ትግበራው ላይ የአንበሳውን ድርሻ ወስደዋል፡፡

በዚህ ድንቅ ውበት ተከሽኖ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነውን መዝናኛ ክበብ በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት እሰጣለሁ ብለው ጨረታውን ያሸነፉ ባለሀብት ዛሬ ስራቸውን በይፋ የጀመሩ ሲሆን የዛሬውን የምሳ መስተንግዶ ለሁሉም ሰራተኞች በባለ ሀብቱ ሙሉ ወጪ በግብዣ መልኩ እንደሚሸፈን ታውቋል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍9👎1
ረቡዕ:- መጋቢት 11 ቀን 2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ

በኮሌጁ ሶሻል ኮሚቴ የፍጆታ እቃዎች አቅራቢ ኮሚቴ የመጋቢት ወር 2016 ዓ.ም ስኳር ለማምጣት መዘጋጀቱን ገልፆ የአቅርቦቱ ተጠቃሚ የሆናችሁ ሰራተኞች በሙሉ እስከ አርብ /መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም/ ድረስ ክፍያውን አጠናቁ ብሏችኋል፡፡

ኮሚቴው
👍5
Forwarded from addis Azimeraw
👍8
ሐሙስ:- መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

ስነምግባር

ስነምግባር ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከህብረተሰብ፣ ከተለያዩ ተቋማት /ለምሳል ከሃይማኖት እና ሌሎች/፣ ከህግ እና ፍትህ አካላት ወዘተ የሚመነጭ ሲሆን ስነ ምግባር ሰላምን ለማሰፈን፣ ሁሉም ሰው በእኩልነትና በመከባበር እንዲኖር ለማድረግ፣ የጋራ ተጠቃሚነትንና እድገትን ለማምጣት፣ ወዘተ ይጠቅማል፡፡
ስነ ምግባር ወሳኝ የሆኑ የህይወት መርሆዎችን በመከተል የሚኖር ሲሆን በመርህ ለመኖር ደግሞ ሁለንተናዊ የሆነ የሞራል ባህርይ መላበስ ያስፈልጋል፡፡
የኮሌጁ የስነምግባርና ጸረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍1
ሐሙስ:- መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

ሁሉን አቀፍ ተቋማዊ የልማት ገጽታዎቻችን እንደ ቀጠሉ ናቸው!!

ኮሌጁ በዚህ በጀት ዓመት እጅግ በርካታ የስራ ስኬቶችን ያስመዘገበበት ጊዜ ሲሆን በርካታዎቹ ስራዎች ተጠናቀዋል፤ የተወሰኑት ጥቂት ጊዜን ይሻሉ አንዳንዶቹ ደግሞ እቅድ ተይዞላቸዋል፡፡

ተቋሙን ምቹ የስራ ከባቢ እና ለእይታ ሳቢ ለማድረግ እየተከወኑ ካሉ ዘረፈ ብዙ ትጋቶች መካከል ትልቁን ሚና የሚጋሩት የኮንስትራክሽን ዘርፍ አሰልጣኞች ናቸው፡፡ ስልጠና ዘርፉ በተለያዩ አሰልጣኞች ታቅደው እየተተገበሩ ያሉ በርካታ ፕሮጀክቶችን የያዘ ሲሆን በዚህ ምልከታችን በሁለት አሰልጣኞች እየተሰራ ያለን የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና የአደባባይ ስራ በአጭር እንቃኛለን፡፡

በሁለት በኩል መተላለፊያ የሚሆኑ እና በቴራዞን ንጣፍ ለመስራት እቅድ የተያዘላቸውን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ጨምሮ በልዩ ልዩ አበባዎችና ሳሮች እንዲያሸበርቁ ታልሞ እየተሰራ የሚገኝን መለስተኛ አደባባይ ለመስራት ሲታትሩ ሁለት የዘርፉን አሰልጣኞች በካሜራችን ዐይን ተመልክተናል፡፡

600 ካሬ ሜትር ገደማ በሚሸፍን ቦታ ላይ የመንገድ እና የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን እየሰሩ ያሉ 2 አሰልጣኞች መርጋ አብዲሳ እና ገረመ ፍሪሳ ናቸው፡፡ አሰልጣኞቹ በኮሌጁ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በመመልከት እነሱም የራሳቸውን አሻራ ለማኖር በማስብ ለመስራት መነሳታቸውን ተናግረዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ አካባቢ የሚገኝ ሲሆን ከዚህ በፊት የነበረው ገጽታ ምቾትን የሚነሳ ነበር፡፡ ይህ ፕሮጀክት አሁን ላይ 80 ከመቶው መጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ አሰልጣኞቹ የገለፁ ሲሆን ከ20 ቀናት ባልበለጡ ጊዜያት ለማጠናቀቅ ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ውበት ማምጣት ብቻ ሳይሆን ኮሌጁን የሚገልጽ ልዩ ልዩ አስተማሪ ይዘት እና ቅርጽ እንዲኖረው ይደረጋልም ተብሏል፡፡ እኛም እንደሁል ጊዜው ብርቱ እጆች እና በጎ ተግባሮች ይቀጥሉ እያልን ቀጣይ በሌሎች ተመሳሳይ ቅኝቶች እስከምንመለስ ቸር ቆዩን፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍41
አርብ:- መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

ለሬጅስትራር ጽ/ቤት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ!!

ለኮሌጁ ሬጅስትራር ጽ/ቤት ባለሙያዎች በደንበኛ አያያዝ ዙሪያ ዛሬ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ስልጠና ተሰጠ፡፡

የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ ለጽ/ቤቱ ባለሙያዎች የተሰጠው ስልጠና በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ ፈታኝ ነገሮችን የሚያሳይ እና ማሻሻያ ስልቶችን የሚጠቁም ነው፡፡

ስልጠናውን ያዘጋጀው በስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን ቢሮ ስር የጥናት፣ ምርምርና ፐብሊኬሽን የስራ ክፍል ሲሆን ሬጅስትራር ጽ/ቤት ከሰልጣኝ ቅብላ እስከ ስልጠና ማጠናቀቂያ ሰርተፍኬት ስጦታ ድረስ ባለው ጌዜ ከደንበኞች ጋር ሰፊ እና ቀጥተኛ ግንኙነት ስላለው ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም እና የደንበኞችን ፍላጎት ያማከለ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማስቻል ታቅዶ መዘጋጀቱን ከስራ ክፍሉ አስተባባሪ ምስራቅ ደለሳ ማረጋገጥ ችለናል፡፡

አስተባባሪዋ አክለውም የጥናት፣ ምርምርና ፐብሊኬሽን የስራ ክፍል ተግባራዊ ጥናት እና ምርምር በማድረግ ክፍተቶች እንዲሞሉ ማድረግ ሲሆን ይህ ስልጠና እንዲሰጥ የተደረገውም በጥናቱ ግኝት መሰረት መስተካከል ካለባቸው ትግበራዎች አንዱ ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡ ስልጠናው የተሰጠው ደግሞ በሄኖክ አብርሃም ነው፡፡

የኮሌጁ ደንበኞች የመጀመሪዎቹ ሰልጣኞች ናቸው፤ ሁለተኛዎቹም ሰልጣኞች ናቸው፤ ሶስተኛ እና አራተኛም እነሱ ስለሆነም በሁሉም የስራ እንቅስቃሴ ሰልጣኝ ተኮር ስራዎችን መስራት የሁል ጊዜ ተቀዳሚ ትኩረታችን ነው፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍163
ማክሰኞ:- መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ

ለኮሌጁ ሰልጣኞች በሙሉ

የኮሌጁ የስነምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት በስነምግባር ምንነትና አስፈላጊነት፤ በሰልጣኞች የስነምግባር ክበብ ምንነትና ጥቅም እንዲሁም ብልሹ አሰራር ከተማሪዎች የስልጠና አሰጣጥ አንጻር ያለውን ትርጉም በተመለከተ ለ2 ቀናት ስልጠና አዘጋጅተናል፡፡

በመሆኑም ከመጋቢት 18 – 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ---- 11፡00 ሰዓት ለ2 ተከታታይ ቀናት አስተዳደር ህንፃ 4ኛው ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስልጠናው ስለሚሰጥ በዕለቱ እና በሰዓቱ እንድትገኙ እናሳውቃለን ፡፡

የኮሌጁ የስነምግባርና ጸረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት
👍1