General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ:- የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም

ለ3ኛ ዙር የስራ ላይ ልምምድ የህይወት ክህሎት ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች አጠናቀቁ፡፡

ለ3ኛ ዙር የስራ ላይ ልምምድ የህይወት ክህሎት ስልጠና የወሰዱ ወጣቶች ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም አጠናቀቁ፡፡

ኮሌጁ በዚህ ዙር ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የተቀበላቸውን 395 ሰልጣኞች ስልጠና አጠናቆ የክፍለ ከተማውና የወረዳው የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አስመርቋል፡፡

ወጣቶቹ በ10 ቀናት በቆታቸው መሰረታዊ የህይወት ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ፣ የስራ ዝግጁነት ብቃቶችን እንዲጨብጡ እና የህይወት ልምዳቸውን እንዲያጎለብቱ ታልሞ የተሰጠ ሲሆን ከስልጠና በኋላ ለ6 ወራት ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ለተግባር ስራ ልምምድ የሚሄዱ መሆኑ ታውቋል፡፡

ኮሌጁ ከዚህ በፊት ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የመጡ ወጣቶችን በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዙር ስልጠና ሰጥቶ ወደ ተግባር ስራ ልምምድ እንዲወጡ አድርጓል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍71
አርብ:- የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም

የሐዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች በኮሌጁ ጉብኝት አደረጉ!!

የሐዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

በዕለቱ በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የሐዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማናጅመንትና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት ሲሆኑ ኮሌጃችን በአይ ኤስ /ISO/ 9001፡2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ መሆኑ ተከትሎ እነሱም በዚህ ሂደት ላይ በመገኘታቸው የአሰራር ልምድ ለማግኘት ፈልገው መምጣታቸው ተገልጿል፡፡

በዕለቱ የሐዋሳ ልዑካኑ ቡድን አባላት በኮሌጁ የተሰሩ አብየት ፕሮጀክቶችንና የተሟሉ ግብዓቶችን በምልከታ፣ ልዩ ልዩ ተግባራትን በገለጻ፣ እና የለውጥ አሰራሮችን በውይይት ልምድ እንዲወስዱ ተደርጓል።

የሐዋሳ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በቴክስታይልና ጋርመት ቴክኖሎጂ ዘርፍ እንደ ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን በEASRIP ፕሮጀክት አማካኝነት በርካታ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍14👏42
ጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ማህበረሰብ በሙሉ ዛሬ(12/06/16) 4 ሰዓት ላይ የወንድማችን የሰልጣኝ ቤካም ሌንጂሶ የመታሰብያ የሻማ ማብራት ፕሮግራም ስላለ በፕሮግራሙ ላይ ባስኬት ball ሜዳ እንድትገኙ እናሳስባለን።
😢30👍10🙏81
ጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሰልጣኝ የነበረው የቤካም ሌንጂሶ የመታሰብያ የሻማ ማብራት ፕሮግራም የኮሌጁ አመራሮች፣አሰልጣኞች፣ አስተዳደር ሰራተኞች እና ሰልጣኞች እንዲሁም የቀድሞ ጓደኞቹ በተገኙበት ተካሄደ።
😢65👍8🙏53
ረቡዕ:- የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

የኮሌጁ ዲኖች እና የተለያዩ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ!!

የኮሌጁ ዲኖች እና የተለያዩ ባለሙያዎች ዛሬ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተገኝተው ጉብኝት አደረጉ፡፡

በኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መለሰ ይግዛው የተመራ ልዑክ ኢንስቲትዩቱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሰራቸውን እና እየሰራቸው ያሉ አስደናቂ ተግባራትን ተመልክቷል፡፡ በጉብኝቱ ተቋሙ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በፋናንስ አገልግሎት፣ በአየር ንብረት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በሰላምና ደህንነት፣ በሮቦቲክስ፣ በተፈጥሮ ቋንቋ ቅንብር እና መሰል ዘርፎች ላይ ያከናውናቸውን ስራዎች ማየት ተችሏል፡፡

ኮሌጁ የዲጂታል ሲስተምን ተጠቅሞ ከትውልዱ ፍላጎት እና ከቴክኖሎጂው ዕድገት ጋር የተቀናጀ ስልጠና ለመስጠት ያስችለው ዘንድ ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የትብብር ሰነድ እያዘጋጀ ሲሆን ይህም በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ ለማሳካት አንዱ አጋዥ መንገድ እንደሚሆነው ተገልጿል፡፡

ቀጣይ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በሚደረገው ስምምነት ኮሌጁ በዲጅታላይዜሽን ላይ እየሰራ ያለውን ዘርፈ ብዙ ትግበራ የበለጠ ለማስፋት እና ለማዘመን አቅም ይፈጥርለታልም ተብሏል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍163👎3
ሐሙስ:- የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

የኮሌጁ ሆቴልና ሆስፒታሊቲ ማሰልጠኛ አዲሱ ህንፃን ስራ ለማስጀመር ርክክብ ተደረገ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሆቴልና ሆስፒታሊቲ ማሰልጠኛ አዲሱን ህንፃ ስራ ለማስጀመር ከየካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ርክክብ ተደረገ፡፡

የሆቴል እና ሆስፒሊት ዲፓርትመንትን ስልጠና አንድ ምዕራፍ የሚያሻግር ነው የተባለለት አዲስ ህንፃ ባለ አራት ወለል ሲሆን ለሆቴል አገልግሎት የሚያገለግሉ ግብዓት እንዲሟላለት ተደርጓል።

በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር እቅድ የተያዘለት የሆቴል እና ሆስፒታሊቲ ስልጠና ክፍል ማሰልጠኛ ህንፃ ዲፓርትመንቱ ለተግባር ልምምድ ወደ ተለያዩ ሆቴሎች የሚያደርገውን ደጅ ጥናት የሚያስቀር ወይም የሚቀንስ ሲሆን ለኮሌጁ ማህበረሰብ እና ለውጭ አገልግሎት ፈላጊዎች ደግሞ የሆቴል አገልግሎት የሚያገኙበት ነው።

ህንፃው በውስጡ መሠረታዊ የሆቴል አገልግሎትን የሚሰጡ ክፍሎች የተሟሉለት ሲሆን ሆቴሉ ስራ ሲጀምር ከስልጠና ባሻገር የኮሌጁን የውስጥ ገቢ በማሳደግ ረገድ ትልቅ ተስፋ ተጥሎበታል።

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍17🏆32