ሐሙስ:- ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም
የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሸን ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት የቀጣይ ስራ እቅድ ውይይት አካሄደ!!
የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሸን ቴክኖሎጂ /ICT/ ዲፓርትመንት የቀጣይ ሁለት ዓመት የዲፓርትመንቱ የስራ እቅድ ውይይት ጥር 23 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሄደ፡፡
ዲፓርትመንቱ የ2 ዓመት እቅድ ያዘጋጀው አዲስ የዲፓርትመንት ኃላፊ በመመረጡ ሲሆን አዲሱ ኃላፊ ቀጣይ 2 ዓመት በሚኖረው ቆይታ እንደ ዲፓርትመንት የሚሰሩ አበየት ተግባራትን ለስልጠና ክፍሉ አሰልጣኞች ገለፃ ያደረገ ሲሆን ከዚህ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን በማረም እና አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት የስልጠናውን ሂደት ለማዘመንና ተጓዳኝ ተግባራትን ለማከናወን እቅድ መያዙን ገልፃል፡፡
ዲፓርትመንቱ በአሁኑ ሰዓት 21 አሰልጣኞች እና በርካታ ሰልጣኞች ሲኖሩት የስራ እቅዱን ያቀረቡት አዲሱ የስልጠና ዘርፍ ኃላፊ አሰልጣኝ ኃይማኖት ታደሰ ናቸው፡፡
ሁሉም የስልጠና ዘርፎች አዳዲስ የዲፓርትመንት ኃላፊ የተመደበላቸው ሲሆን ከዚህ በፊት የነበሩ ተጠሪዎች የስራ ጊዜያቸውን አጠናቀው ለአዲሶቹ አስረክበዋል፡፡
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍9❤2
Forwarded from Ambachew Gets Su
የተከበራችሁ ዲኖች እንደምን ዋላችሁ የአሰልጣኞች የሙያ ብቃት ምዘና (ሶኦሲ) በቢዝነስ ሙያዎች እሁድ ጥር 26/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን እየገለጽን የቀጣይ የአይሲቲና የእሁዱን ምዘና ፕሮግራም ማለትም አሰልጣኞች በየትኛ የምዠና ጣቢያ እንደሚመዘኑ ዛሬውኑ የምንልክላችሁ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ተመዛኝ አሰልጣኞች እንዲያውቁት ይደረግ
አርብ:- ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም
በኮሌጁ ከእዳ ወደ ምንዳ በሚል መነሻ ሀሳብ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል!!
ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኞች በተገኙበት ከእዳ ወደ ምንዳ በሚል መነሻ ሀሳብ ዛሬ ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ስልጠናው እየሰጠን ላለው ተቋማዊ የስልጠናና መሰል አገልግሎት የበለጠ አቅም ይፈጥርናል በማለት በመግቢያ ንግግራቸው ገለፃ የሰጡት የኮሉጁ ዋና ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ሲሆኑ ዋና ዲኑ አክለውም በስልጠናው የሚቀርቡ ሁሉንም ሰነዶች እንደ ኮሌጃችን ነባራዊ ሁኔታ በመተርጎም የምንሰጠውን አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ ይጠቅመናል ብለዋል፡፡
ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ተከታታይ ሁለት ቀናት የተያዘለት ሲሆን ለስልጠናው የተለያየ ይዘት ያላቸው 4 ሰነዶች ተዘጋጅተው እየቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ስልጠና የሚሰጥባቸው 4ቱ ሰነዶች የግዢ ትርክት ግንባታ፣ ሀብት የመፍጠር ጉዟችን ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የቀጣይ አቅጣጫዎች፣ የሰላም ባህልና አመለካከትን የመገንባትና የመምራት ክህሎት፣ እና በኢትዮጵያ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በተደረገው ጥረት የተስተዋሉ ስኬቶች፣ ፈተናዎችና የቀጣይ ትኩረት የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ይህ ስልጠና ከኮሌጁ ባሻገር በአሁኑ ሰዓት እንደ ከተማ አስተዳደር በሁሉም የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት ለሚገኙ ሰራተኞች እየተሰጠ የሚገኝ መሆኑ ታውቋል፡፡

❤5👍5
እሁድ፡- ጥር 26 ቀን 2016 ዓ.ም
በኮሌጁ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ተካሄደ!!
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የተመራ ልዑካን ቡድን ዛሬ ጥር 26 ቀን 2016 ዓ.ም በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ።
በልዑካን ቡድኑ ከቢሮው ሃላፊ ባሻገር ምክትል ቢሮ ሃላፊዎች፣ የቢሮው ዳይሬክተሮች እና የሁሉም ኮሌጆች ዲኖች የተገኙ ሲሆን በኮሌጁ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ልዩ ልዩ የስልጠና ፋሲሊቲዎችን በመጎብኘት ልምድ እንዲጋሩ ተደርጓል።
ኮሌጁን በአይ ኤስ ኦ /ISO/ የጥራት አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ ከማስደረግ ጀምሮ ልዩ ልዩ አስደማሚ ተግባራትን በቅንጅት ሰርቶ እምርታዊ ለውጥ ይመጣ ዘንድ የተጠቀሙበትን የመሪነት ፍልስፍና ለልዑካን ቡድኑ ያጋሩት የኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ናቸው።
በሌላ በኩል የቢሮው ሃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው ለውጥ ለማምጣት በቂ ግብዓት አለን ነገር ግን ውስጣዊ ተነሳሽነት እና ቅንጅታዊ አስራር በመፍጠር ታሪክ መቀየር እንደምንችል ከዛሬው ጉብኝት ሰፊ ትምህርት አግኝተናል ብለዋል። አቶ ጥራቱ አክለውም እኛም ወደ ፊት መቀጠል የምንችለው ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ ለውጥ ስናመጣ ብቻ ነው በማለት ተናግረዋል።
በዛሬው የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ከጀነራል ዊንጊት ፖሊ ቴክኒክ ባሻገር በደጃዝማች ወንድይራድ ቅድመ መደበኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፣ በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ በመገኘት ያሉ መልካም ስራዎችን ለመቅሰም ተሞክሯል።
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍15❤1