General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
😢10👍76🏆3👏1
አርብ:- ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ላላቸው የኮሌጁ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ተካሄደ!!

መጪውን የገና /የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት/ በዓል ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ላላቸው የኮሌጁ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡

ኮሌጁ ከ400 ሺ ብር በላይ ወጪ አድርጎ ከ6ሺ ብር በታች ደመወዝ ለሚከፈላቸው 200 ሰራተኞች የዓይነት ስጦታ በማበርከት ለበዓሉ እንኳን አደረሳችሁ ብሏል፡፡

የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ጫና ላይ ላሉ የስራ ባልደረቦች የመተሳሰብ እና የመረዳዳት ባህል ለማጠናከር እና የአንዱን ችግር ሌላዉ እንዲጋራ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ኮሌጁ ከዚህም በፊት በነበሩ በዓላት አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑ ሰራተኞች የበዓል መዋያ ድጎማ ሲያደርግ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
20👍9👏5👎1
አርብ:- ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ!!

የሁሉም ኮሌጆች የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዛሬ ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

የግምገማ መድረኩ ዝግጅት እና አስተባባሪ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ሲሆን በዕለቱ በሁሉም ኮሌጆች ያሉ የዘርፉ ምክትል ዲኖች እና የቢሮው የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በግምገማ መድረኩ ላይ የሁሉም ኮሌጆች የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲኖች እንደ ዘርፍ የተቋሞቻቸውን የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም አቅርበው ሀሳብ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም የዘርፉን ስራ አፈፃፀም በስራ ክፍሉ ም/ዲን በአቶ ደሜ መርሻ አማካኝነት ቀርቧል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍95
Forwarded from General Wingate Students Channel (E l i a z 🌙 ኤ ል ያ ዝ | Элиаз)
በጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ የገና በዓልን በማስመልከት ለ2ተኛ ዙር የደም ልገሳ ፕርግራም ተካሄደ። ከኢትዮጵያ ደም ባንክ እና ከጀኔራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሰልጣኝ ካውንስል ጋር በጋራ በመተባበር የተዘጋጀው የደም ልገሳ ፕሮግራም በኮሌጃችን ግቢ ውስጥ ያሉት የአስተዳደር ሰራተኞች ፣ ሰልጣኞች እንዲሁም በግቢ ውስጥ ያሉ ማህበረሰዎች ተሳትፈውበታል ። ይህ ፕሮግራም ቀጣይነት ያለው ስለሆነ ከዚህ በኋላ ላሉት ፕሮግራሞችም ድጋፋችሁ አይለየን በአሁኑ የደም ልገሳ የተሳተፋችሁ በሙሉ እናመሰግናለን። መልካም በዓል።

የሰልጣኝ ካውንስል
14👍6
ቅዳሜ፥- ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ∙ም

‹‹አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡›› ሉቃ 2፡11

ለኮሌጃችን የክርስትና እምነት ተከታይ ሰራተኞች እና ሰልጣኞች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የበጎነት ይሆን ዘንድ እንመኛለን። መልካም በዓል ይሁንላችሁ፡፡

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
70👍19😢5🙏3🏆2
🙏6026👍12👎5😢5👌3