ሐሙስ፥- ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ∙ም
በዚህ ዓመት በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊስ መሠረት እስከ ደረጃ 6 ቅበላ ይደረጋል ተባለ!!
ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መሰረት ከዚህ ቀደም እስከ ደረጃ 5 ብቻ ተገድቦ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የእድገት መሰላል እስከ ደረጃ 8 ድረስ እንዲሆን መደረጉ ይታወሳል፡፡
ይህም ፖሊሲው ደረጃ ስድስትን ከመጀመሪያ ድግሪ፣ ደረጃ ሰባትን ከማስተርስ እንዲሁም ደረጃ ስምንትን ከዶክትሬት ዲግሪ /PhD/ ጋር ትይዩ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ስለሆነም በዚህ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ መግባት ቢፈልጉ በደረጃ 6 ገብተው መሰልጠን እንደሚያስችላቸው ተመላክቷል፡፡
ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በደረጃ 6 የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች እንደሚስተናገዱ የጠቆሙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪያት ካሚል ሲሆኑ በዚህ ዓመት በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በክልሎች አማካኝነት የሰልጣኞች ምደባ ይካሄዳል ብለዋል፡፡
በዚህም በተያዘው የሥልጠና ዘመን 632 ሺህ በላይ ተማሪዎች የሥራ ገበያውን የሰው ሀይል ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ ከደረጃ 1-ደረጃ 5 እንደ ውጤታቸው ተመድበው እንደሚሰለጥኑም ነው ክብርት ሚኒስትሯ የገለጹት፡፡
በወጣው መቁረጫ ነጥብ መሰረትም ደረጃ አንድ እና ሁለት 110,015 ፤ በደረጃ ሦሰት እና አራት 412,557 እንዲሁም በደረጃ አምስት 110,015 እንደሚሳተፉ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በደረጃ ስድስት ደግሞ 2000 የሚሆኑ ሰልጣኞችን ለቀመበል ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል፡፡
የ2016 የስልጠና ዘመን የተዘጋጀው መቁረጫ ነጥብ የ2015 ትምህርት እና የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12 ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
ከ2014 ዓ.ም በፊት ለነበሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ደግሞ በስልጠና ዘመኑ በነበረው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
Credit: መረጃውን እወቁልኝ ብሎ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ያጋራው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ነው።

👍24
ሐሙስ:-ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም
አዲስ በተቀረፀው የሰልጣኞች ስነ ምግባር መመሪያ ዙሪያ ከሰልጣኞች እና ከሰልጣኞች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ካላቸው አካላት ጋር ውይይት ተደረገ!!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ቢሮ ተዘጋጅቶ በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ 15 የመንግስት ቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ላይ በሚተገበረው የሰልጣኞች የስነ ምግባር መመሪያ ዙርያ ከሰልጣኞች እና ከሰልጣኞች ጋር ቀጥታ ግንኙነት ካላቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።
በ4 ክፍሎች እና በ27 አንቀፆች የተሰነደው መመሪያ ሰልጣኞች ህግና ደንብ አክብረው እንዲማሩ፣ በተቋሙ ውስጥ ሁሉን አቀፍ አዎንታዊ ተሳትፎ እንዲኖራቸው፣ ተቋማዊ ሥርዓት እንዲሰፍን፣ የስልጠና ጥራት እንዲረጋገጥ እና ምቹ የመማር ማስተማር አካባቢን ለመፍጠር ታቅዶ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡
መመሪው የስነ ምግባር ግድፈት ዓይነቶች እና የእርምት እርምጃዎችን ብቻ ሳይሆን ሰልጣኞች መጠቀም ያለባቸውን ሙሉ መብት እና መወጣት ያለባቸውን ግዴታ በስፋት ይዘረዝራል፡፡
በመመሪያው ዙሪያ ከሰልጣኞች ጋር ውይይት የተደረገው ዛሬ ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ደግሞ ትናንት ህዳር 5 ቀን ነው፡፡
በኮሌጅ ደረጃ በስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን የሚመራ የሰልጣኞች ዲሲፕሊን ኮሚቴ እንደሚዋቀር ተገልጿል።
መመሪያው ረቂቅ በመሆኑ ከመፅደቁ በፊት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይቶ የጋራ ለማድረግ ታስቦ የተደረገ ነው ያሉን ደግሞ የኮንስትራክሽን ስልጠና ክፍል ተጠሪ እና በመመሪያ ዝግጅቱ የጀነራል ዊንጌት ተወካይ የሆኑት አሰልጣኝ ኤፍሬም ጥላሁን ናቸው።

👍23❤1
ሰኞ 10/03/2016 ዓ.ም ምዝገባ ይጀመራል በምስሉ ላይ የተገለፀውን ቅደም ተከተል በመከተል በ https://www.aatvetb.edu.et/ ድህረገፅ ገብተው ይመዝገቡ
Galmeen Wixataa (10/03/2016 A.L.H) eegalma, marsariitii https://www.aatvetb.edu.et/ seenuun tartiiba suuraa irratti mul'atu hordofuun galmaa'aa.
Registration Will start Monday( Nov 20/2023), log in to the website https://www.aatvetb.edu.et/ and register by following the order shown in the image.

👍12
Forwarded from Bank of Abyssinia
ባንካችን አቢሲንያ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን የአፖሎ የተማሪ አምባሳደር በማድረግ፣ አፖሎን ለደንበኞች በማስተዋወቅ እና በምዝገባ ባሳኩት መጠን የኮሚሽን ክፍያ ለመክፈል አስፈላጊውን ዝግጅት ጨርሷል፡፡ ስለሆነም የአፖሎ አምባሳደር ለመሆን ፍላጎት ያላቸውን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አወዳድሮ ለመውሰድ ተዘጋጅቷል፡፡ ከተጨማሪ የገቢ ምንጭ ባለፈ ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ ተመርቀው ሲወጡ የሥራ ልምድ ይሆናቸው ዘንድ ያላቸውን ችሎታ የሚያሳድጉበት፤ እንዲሁም እንደሚያሳዩት ውጤትና ተነሳሽነት ሌሎች ሽልማቶችን የሚያገኙበትን አጋጣሚ አቢሲንያ ባንክ ፈጥሯል፡፡
የዚህ እድል ተሳታፊ ለመሆን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ነጥቦች፣
የከፍተኛ ትምህርት እየተከታተላችሁ መሆኑን የሚገልፅ የተማሪ መታወቂያ፤
የአፖሎ አካውንት ባለቤት መሆን፤ ከ150 ቃላት ባልበለጠ ራሳችሁን የሚገልፅ አጭር ፅሁፍ እና
በቀላሉ ለመሙላት በተዘጋጀው የማመልከቻ ገጽ ከ150 ቃላት ባልበለጠ ለምን የአፖሎ አምባሳደር ለመሆን እንደፈለጋችሁ መግለፅ ብቻ ናቸው፡፡ ስለሆነም ከታች ያለውን መስፈንጠሪያ በመጠቀም ይመዝግቡ፡፡
https://apolsup.bankofabyssinia.com/studentAgent
ከአፖሎ ጋር ተፍ ተፍ በሉ፡፡
ከስራ በፊት ስራ ጀምሩ፡፡
ጠቀም ያለ የሪፈራል ኮሚሽንም አግኙ!

👍14