Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
በእንግሊዝ ያሉ ቅርሶችን ለማስመለስ የተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች እንቅስቃሴ

እንደ ሙላቱ አስታጥቄ እና አቤል ተስፋዬ (ዘዊኬንድ) ያሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያን በአለም መብዛታቸው ቅርሶችን ለማስመለስ እየረዳ ይገኛል ተባለ፡፡

ኢትዮጵያ በጣሊያን ቬነስ ከተማ በተካሄደው በዓለም አቀፉ የቢናሌ የባህል ኤግዚቢሽን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳትፋለች፡፡ መድረኩ አለም አቀፍ የጥበብ ሰዎች ሥራቸውን ያቀረቡበት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ታዋቂው ገጣሚና ደራሲ ለምን ሲሳይ እና ኢትዮጵያዊው ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ ተሳትፈውበታል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያዊው ሰዓሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ ስራቸውን አቅርበዋል፡፡

በወቅቱ ገጣሚ ለምን ሲሳይ እንደገለፀው የእንግሊዝ ሙዚየም ከእይታ ደብቆ በምስጢር አስቀምጧቸዋል ያላቸውን ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ጠይቋል፡፡

በዚህም ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያን በአለም ደረጃ እየበዙ መምጣታቸው ቅርሶችን በማስመልስ ሂደት ውስጥ ሰፊ ሚና እንደሚኖራቸው ገልጿል፡፡

ለአብነትም እንደ ሙላቱ አስታጥቄ፣ አቤል ተስፋዬ (ዘዊኬንድ)፣ መአዛ መንግሰቴ፣ ሩት ነጋ እና ሊያ ከበደን ጨምሮ የሌሎች በርካታ ኢትዮጵያዊያን ተፅዕኖ ፈጣሪነት የኢትዮጵያን የቅርስ ማስመለስ ጥያቄዎች ችላ እንዳይባሉ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ጠቅሷል፡፡

ቅርሶቹ በመቅደላ ጦርነት ወቅት የተወሰዱ ቅርሶች ሲሆን በተጨማሪም 11 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታቦታት እንደሚገኙበትም ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡

ገጣሚ ለምን አክሎም የእንግሊዝ ሙዚየም በ50 ሚሊየን ፓውንድ እድሳት ሊደረግለት እቅድ መያዙን ገልጾ ከዕቅዱ ውስጥም ቅርሶችን መመለስ ሊገኝበት እንደሚችል ተስፋውን ገልጿል፡፡

https://t.me/waliyaentmt
https://t.me/waliyaentmt
የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት ለድምጻዊት ቤቲ ጂ "የክብር ኮከብ አዛዥነት ማዕረግ" ሽልማትን አበርክቷል።

ድምጻዊቷ የኢትዮጵያ ሙዚቃና ባህል ለዓለም በማስተዋወቅና በበጎ ተግባራት ላይ በመሰማራት ላበረከተችው አስተዋጽኦ ነው ሽልማቱን የሰጠው። ሽልማቱን ከኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤት ሊቀመንበር ከ ልዑል ኤርሚያስ ሣህለ ሥላሴ እጅ ተቀብላለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምፃዊት መሰሉ

የባንክ ሰራተኛ ፕሮቶኮል መጠበቅ ግዴታው ነው እኔም የስራዬ ሁኔታ ነው እንጂ መድረክ ላይ እንደምሆነው አደለውም።

ስራዬ ነው፣ ስሜት ነው ሰለዚህ በዛ መንገድ እዩት ተረዱት።

የመድረኳ መሰሉ የኔ ማንነት አደለም ከስራ ውጪ እና ቤት ሌላ ሰው ነኝ።

የወርቁ አይተነው ሚሰት ለምን ትዘፍኛለሽ አትበሉኝ ጥሩ ወዳጄ ነው የልጄ አባት ነው እንጂ አሁን ባሌ አደለም።

ሰራዬን ልሰራበት እኔ እንደማንኛው ሰው ተከራይቼ ነው የምኖረው ብዙ ሰዎች እየደወሉ አስረጂን ይላሉ።

እኔ ሰርቼ በላቤ ነው የምኖረው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ሳሚ ዳን በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ

"ትላንት በሀና ቤት (HOH) ልጆችን ለመጎብኘት ሄደን ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍን፡፡
አወይ ልጅነቴ ....ሄዷል ለካ
የሀና ቤት (HOH) ቆሼ ሠፈር የሚገኝ ችግረኞች የሚረዱበት ፤ ልጆችም ተምረው ሠው የሚሆኑበት ቤት ነው።"

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #SamiDanMusic
ድምጻዊት ሀሊማ አብድራህማን የምታደንቃቸው 3 የምንግዜም ምርጥ ሙዚቃና ሙዚቀኞች እነማናቸው?

ፈገግታ ከፊቷ ጠፍቶ አያውቅም ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎቹዋ እና የአልበም ስራዋ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነትን አስገኝቶላታል። እዩሀ አበባዬ፤ ከቃል በላይና ከገበታ በታች ከተደመጡ የሙዚቃ ስራዎቹዋ ቀዳሚውን ስፍራ ይይዛሉ።

ድምፃይቷ ከጆሮዋ የማትነጥላቸውን የምንግዜም ምርጥ የሙዚቃ ምርጫዎቹዋን ነግራናለች

ከኢትዮጵያ ቅኝቶች የትዝታ አድናቂ ናት። ለስላሳ ሙዚቃዎችን አጥብቃ ታደምጣለ። በቀዳሚነት ከገበታ በታች ስራዋ ይለይባታል የእንቁጣጣሽ ማብሰርያ ሙዚቃዋ እዮሀ አበባዬንም ትወደዋለች

ጠየቅን!
ከአንጋፋ ሙዚቀኞች የማን አድናቂ ነሽ?

ሙዚቃዎቹዋን አብዝቼ እጫወታለሁ እሷ የኔ የምንግዜም ተወዳጅ ምርጫ ናት ሁሉም ስራዎቹዋ ጨርሶ አይጣሉም ናፈቀኝ ደሞ ይለይብኛል ከአነጋገሯ የጂጂ ቀንደኛ አድናቂ ሰለመሆኗ ለመገመት አይከብድም።

ተከታይ ምርጫዋን አስከተለችና የጎሳዬ ተስፋዬ ማን በነገረሽ አይኔን ከምርጫ መዝገቧ ላይ አሰፈረች

ሶስተኛ ምርጫዋን በህመሟ ጊዜ አብረዋት ለተጨነቁ የሀገር ልጆች ሁሉ እንድንጋብዝው ጠየቀችንና ቀጠለች "ለወትሮም ሙዚቃውን ደጋግሜ እሰማው ነበር አሁን ደሞ ድኜ ከተነሳው በኋላ ይበልጥ ተለየብኝ የነዋይ ደበበ ውለታሽ አለብኝ ስራ ከህይወቴ ጋር የተቆራኘ የሁልጊዜ ምርጫዬ ነውና በህመሜ ከጎኔ ለነበራችሁ ለሁላችሁም ይጋበዝልኝ" !!!!

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#waliya_entmt
👍1
ታዋቂውና ተወዳጁ ድምፃዊ አብነት አጎናፍር ዛሬ ልደቱ ነው

🎂🎂Happy Birthday🎂🎂

ከአብነት አጎናፍር ስራዎች የቱን ትወዱታላችሁ?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt
👍1
በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ደማቅ አሻራ ካሳረፉት መካከል የሆነዉ አንጋፋዉ ድምጻዊ ሙሉቀን መለሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ዋልያ ኢንተርቴይመንት ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ መጽናናትን ይመኛል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዪጵያዊያን ወገኖች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ።

በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ዋልያ ኢንተርቴይመንት ይመኛል።

ዒድ ሙባረክ !

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ኩኩ ሸብስቤ በ ሙሉቀን መለሰ ህልፈት የተሰማትን ሀዘን ገለፀች።
"በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ጉልህ ስፍራ የነበረው የቀድሞው ድምፃዊ የሙያ አባቴ እና አጋሬ ሙሉቀን መለሰ ህልፈት ህይወት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን ሲሆን ሙልቀን በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ላኖረው ታላቅና ድንቅ አሻራ ክብሬ ዘላለማዊ ነው ። ለመላው ቤተሰቦቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ መፅናናትን እመኛለሁ።
ነፍስ ይማር 🙏"

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የባህልና ጥበባት ኢንዱስትሪ ጉባኤ የሙዚቃና ፊልም ኤዲሽን የመክፈቻ ስነስርዓት በትናንትናው እለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስ መኮንን አዳራሽ ተጀመረ።

በጉባኤው ላይ ፓናሊስቶች እንዲሁም ተሳታፊዎች በሥርዓተ ትምህርቱ አገር በቀል እውቀት ያለመደገፉን ሁኔታ፣ ከአእምሯዊ መብት ጋር በተያያዘ የቅጂ መብት ላይ ያለው ችግር፣ የሙዚቃና ፊልም ቢዝነስ እንደ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስገኙ ዘርፎች አለመታየታቸው፣ በሙዚቃ ትምህርት ውስጥ ቴክኖሎጂ እምብዛም ጥቅም ላይ አለመዋሉ፣ ፊልም ለመስራት የሚጠቅሙ ቁሳቁሶች ላይ ከፍተኛ ቀረጥ መጣሉን ወ. ዘ. ተ እንደ ተግዳሮት አንስተዋል። የኢትዮጵያ ቱባ ባህል ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ያለው ፍላጎት በዓለም አቀፍ ገበያ መጨመሩ፣ ቴክኖሎጂን በቀላሉ ለማግኘት የመቻሉ ሁኔታ ለፊልምና ሙዚቃ ዘርፉ እንደ መልካም እድሎች ተነስተዋል።

ተግዳሮቶችን ለማለፍና እድሎችን በአግባቡ ለመጠቀም በዘርፉ ባሉ ባለሞያዎች ዘንድ ጠንካራ አብሮ የመስራት ሁኔታ ሊፈጠር እንዲሁም ሕዝብና መንግስት ዘንድ ስለፊልምና ሙዚቃ ያለው አመለካከት ሊቀየር እንዲሁም የልጆች ተሰጥኦ ገና በለጋነታቸው እንዲዳብር ሊደረግ ይገባልም ተብሏል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music