Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
አርቲስት እናኑ ደጉ አረፈች ።
ቀብር ቀብር ዛሬ 8:00 ሰአት ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ነው
**
***
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር እንቁ የባህል ድምፃዊ ብሎም በሀገራችን ካሉ ቱባ የባሕል ሙዚቃዎችን ከሚጫወቱ ጥቂት ድምፃውያን መካከል አንዷ የነበረችው አርቲስት እናኑ ደጉ ሁለት ኩላሊቶቿ ስራ በማቆማቸው በህክምና ስትረዳ ቆይታ በትናንትናው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች ። ቀብር ዛሬ 8:00 ሰአት ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ከቤተሰቦቿ መረጃ ደርሶኛል ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
መሀሪ ብራዘርስ ባንድ አባላት የወላጅ አባታቸውን የሙዚቃ ስራዎች ዳግም ለአድማጭ ሊደርሱ ነው።

መሀሪ ብራዘርስ ባንድ አባላት የወላጅ አባታቸውን የሙዚቃ ስራዎች ዳግም ለሙዚቃ አፍቃሪያን ለማድረስ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ እንደሚገኙ ሙዚቀኛ ሔኖክ መሀሪ ገለፀ።

የወላጅ አባታቸውን እና ሁለገብ ሙዚቀኛ የነበሩትን መሀሪ አብርሃ ስራዎችን የባንዱ መሪ ሔኖክ መሀሪ በድምፅ እንደሚጫወት ሙዚቀኛው ተናግሯል።

በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ እና ተደማጭ የነበሩ ስራዎች ተመርጠው በባንዱ እየተሰሩ መሆናቸውን የገለፀው ድምፃዊው ሙሉ የአልበም ሰራው በቅርቡ ተጠናቆ ለሙዚቃ አፍቃሪያን ለማድረስ መታቀዱን ለመሰንበቻ ተናግሯል።

ከእዚህ በተጨማሪ የስምንት ወጣት ድምፃውያን ስራዎች በመሀሪ ባንድ ፕሮዲውሰርነት እየተሰሩ ይገኛሉ ሲል በተጨማሪነት አስታውቋል ።

ከተመሰረተ 17ዓመታት እያለፈው የሚገኘው መሀሪ ብራዘርስ ባንድ የተለያዩ ሙዚቀኞችን በማጀብ ትልልቅ የሙዚቃ ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ ይታወቃል።

ሙዚቀኛ ሔኖክ መሀሪ ከእዚህ ቀደም በአፍሪማ መድረክ ቀርቦ ማሸነፍን ጨምሮ በኮክ ስቱዲዮ አፍሪካ ተጋብዘው የሙዚቃ ስራዎችን ማቅረብ ከቻሉ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ድምፃውያን መካከል ይጠቀሳል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምፃዊ ልኡል ሃይሉ ከ3 ዓመታት በፊት ያሰራጨው አልበም በአዲስ ባለመብት ዳግም መለቀቁን አስታወቀ።

ዕውቁ የሙዚቃ ባለሙያ ኤልያስ መልካ በህይወት ሳለ ለሙዚቃ አፍቃሪያን ከደረሱ የመጨረሻ አልበሞች ውስጥ አንዱ የሆነው "እሳቱ ሰዓት" አልበም ዳግም እንዲሰራጭ መደረጉን ተናግሯል።

ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ከመሰንበቻ ጋር ቆይታ ያደረገው ወጣቱ ድምፃዊ ልዑል ሀይሉ የአልበም ስራው ከእዚህ ቀደም በአውታር መተግበሪያ አማካይነት ቢሰራጭም በሚፈለገው ልክ ተደራሽ ሆኗል ብሎ እንደማያስብ ተናግሯል።

ከእዚህ በተጨማሪ ድምፃዊው ከእዚህ አልበም ስርጭት ጋር በተገናኘ ምንም አይነት ክፍያ አለማግኘቱ ቅሬታ እንደፈጠረበት በቆይታው አንስቷል።

አልበሙ ባለቤት አልባ መሆኑን ተከትሎ ከባለ መብቱ እውቅናና ፍቃድ ውጪ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ በተለያዩ መንገዶች ሲሰራጭ ነበር ሲል ድምፃዊው ተናግሯል።

ይህንን አይነቱን ክፍተት ለማስተካከል እና ተገቢውን ጥቅምና የባለመብትነት ጉዳይ ለተገቢው አካል መስጠት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የአልበም ስራው ሊቀቅ ችሏል።

ከመጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በ"ናሆም ሬከርድስ" ባለመብትነት አልበሙ እንደተሰራጨ ያስታወቀው ድምፃው አዲሱ ስምምነት የኮንሰርት ስራዎችን ጨምሮ አልበሙ ተደራሽ የሚሆኑባቸው መንገዶች ይኖራሉ ሲል አስታውቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
🌟 70K SUBSCRIBERS ON YOUTUBE! 🌟

Thank you for being part of this incredible journey! Your support, enthusiasm, and engagement have brought us to this amazing milestone.

Let's keep the celebration going and look forward to even more exciting content ahead! 🥳

Please Subscribe us on👇
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
👍1👏1
ለግጥምና ዜማዎቼ የሂሩት በቀለ ድምፅ የልቤን ያደርስልኛል።

ክቡር ዶ/ር አርቲስት ተስፋዬ አበበ(ፋዘር)

ከ40 በላይ ትያትሮች ተጫውተዋል። ለተዋቂ ሙዚቀኞችም የበዙ ግጥምና ዜማዎችን አበርክተዋል።

ከአራቱ ቅኝቶች የባቲ ቅኝትን ይመርጣሉ፤ የጥላሁንን ገሰሰ እዩዋት ስትናፍቀኝ እና ያም ሲያማ ሙዚቃዎችን በተለየ መንገድ ይመርጡዋቸዋል።

የአስናቀች ወርቁ እንደ እየሩሳሌም የተሰኘው ሌላው የልብ ስራቸው ነው።የአለማየሁ እሸቴ ቆየት ያሉ ሙዚቃዎችንም ደጋግመው ያዳምጡዋቸዋል።

ዘመን ከማይሽረው የራሳቸው ስራዎች አብልጠው የሚወዱትን ጠየቅናቸው ከጥቂት ዝምታ በኋላ ምላሻቸውን አስከተሉ«የሂሩት በቀለ ኢትዪጵያ ሀገሬ እንደ ህዝብ መዝሙር እየተደመጠ ወቅት የሚሻገር ስራ ነውና አስቀድመዋለሁ» አሉን።

ሌላው የግጥምና ዜማ ስራቸው መማር ያስከብራልን ቀጥለው አነሱ።
ለመሰነባበት ጥቂት ሲቀረን ከአሁን ሙዚቃዎች መርጠው የሚሰሙትን አጫወቱን ፣ የፍቅር አዲስ ነቃጥበብን መረጡ ። የትኛው ስራዋን?እሷ የነካችሁ ሁሉ ይስማማኛል ነበር ምላሻቸው !

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የለዛ አዋርድ የአመቱ ምርጥ አልበም የመጨረሻ እጩዎች
1, ሔዋን ገብረወልድ - ሔዋን
2, አብነት አጎናፍር - አለቀ
3, ሮፍናን - ስድስት
4, ዲበኩሉ ታፈሰ - የቱ ጋር ነህ?
5, ግርማ ተፈራ - ግን የት ሃገር?

ድምፆትን ለመስጠት 👉http://vote.leza.show

እባክዎ መልዕክቱን ያጋሩ :
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የለዛ አዋርድ የአመቱ ምርጥ ነጠላ ዜማ የመጨረሻ እጩዎች
1, ቴዲ አፍሮ - ናዕት
2, ዩሃና - ገላጋይ
3, ማስተዋል እያዩ - ጀግና
4, አስቻለው ፈጠነ - እናትዋ ጎንደር
5, ቬሮኒካ አዳነ - አበባዬ

ድምፆትን ለመስጠት 👉http://vote.leza.show

እባክዎ መልዕክቱን ያጋሩ :
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
ነገ በመላ ሀገሪቱ :-

* ይወጣል
* ይለቀቃል

* ለተወዳጁ ድምፃዊ
* ለኢትዮጵያ ልጅ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ መፅሀፍ ተፃፈለት

"ቴዎድሮስ እስኪነግስ" የተሰኘው በብላቴናው የሕይወት ውጣውረድ ላይ ያተኮረው መፅሐፍ ነገ ይወጣል

የሰው ልጅ በኖረበት በየትኛውም የዓለም ስፍራ ባለጸጋ ሆነ ድሃ፣ አለቃ ሆነ ምንዝር በምድር በቆየባቸው ዘመናት የፈጸመው መልካምም ሆነ መጥፎ ተግባር በትውልዶች የህይወት ገጽ ውስጥ በአንዳች መልኩ መስፈሩ አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ የህይወት ፍሰት ውስጥ ያለፈ ሁሉም ሰው ደግሞ የኋላ ዳና፣ የዛሬ አሻራ፣ የነገም ራዕይ አለው፡፡ እነሆ የክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ገርማሞ ( Teddy Afro ) የትላንት ፣ ዛሬና ነገ መልክ፡፡

መጽሐፉን ከነገ ጀምሮ በነዚህ መደብሮች ማግኘት ይችላሉ;-

* ስታዲየም ነጃ መጽሐፍ መደብር 0910990259
* ለገሀር በጋሻው መጽሐፍ መደብር 0911656729
* ለገሀር ማድያ ያሬድ መጽሐፍ መደብር 0913094097
* ሜክሲኮ ኤልያስ አምደ መጽሐፍ መደብር
* መሳለሚያ ሆናልያት ህንፃ ቢሮ ቁጥር 156 ተኬ ማን ፕሮሞሽን 0911518012 ወይም 0921935862
* አራት ኪሎ 0901197837
* ካዛንቺስ መላ ህንጻ ጦቢያ መጽሐፍ መደብር 0913108312
* ፒያሳ አፒር ታረቀኝ መጽሐፍ መደብር 0983294565