Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የባላገሩ ምርጥ ዉድድርን 3ኛ በመዉጣት ያሸነፈው ቅዱስ ዳምጤ ወደ ትዉልድ ከተማው ጅማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

የጅማ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት፤ የከተማው መስተዳደርና የባህልና ቱሪዝም ቢሮ በጋራ ባዘጋጁት ደማቅ የአቀባበል ስነ-ስርዓት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና በርካታ የከተማው ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን ቅዱስ ዳምጤ በባላገሩ ምርጥ የውድድር ታሪኩ የትውልድ ስፍራውን በማስተዋወቅ ላደረገው ከፍተኛ አስተዋፅዖ ምስጋናና የ140 ካሬ ሜትር የመሬት ስጦታ ተበርክቶለታል።

ከፍተኛ ፋክክር በተደረገበት የባላገሩ ምርጥ የድምጻዉያን ዉድድር በድንቅ የመድረክ ብቃት ባቀረባቸው የሙዚቃ ስራዎቹ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈው ቅዱስ ዳምጤ ከሌላኛው ተወዳዳሪ ከእስማኤል መሐመድ (ስሚዝ) ጋር በእኩል ነጥብ የ250 ሺህ ብር ሽልማት እና ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር የሚያወጡ ዘፈኖች ለእያንዳንዳቸው የተሸለሙ ሲሆን ቅዱስ በጥቅሉ የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት አሸናፊ በመሆን ሶስተኛ ሆኖ አጠናቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምፃዊ አለማየሁ ሂርጶ ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በኖርዌይ ታሰሩ።

በአውሮፓ ኖርዌይ ከ20 አመት በላይ ቢኖሩም በድንገት በርካታ ኢትዮጵያ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አለባችሁ በማለት ለእስር እንደተዳረጉ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ቅሬታቸውን ለታዲያስ አዲስ ማሰማታቸውን ፋስት መረጃ ሰምቷል። ለእስር ከተዳረጉ ኢትዮጵያዊያን መካከል በህመም ላይ የሚገኘው ድምፃዊ አለማየሁ ሂርጶ እንደሚገኝበት ተነግሯል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኖርዌይ መንግስት ጋር በመነጋገር ለእስር የተዳረጉ ኢትዮጵያዊያን መፍትሄ ይሰጠን ብሏል። ለበርካታ አመታት ትዳር መስርተን እየኖርን ነው ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አንፈልግም ብለዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
5 ቀናት ብቻ!!!

13ኛው የለዛ ሽልማት ድምፅ አሰጣጥ የመጀመሪያው ዙር ሊጠናቀቅ 5ቀናት ብቻ ቀርተውታል።

https://vote.leza.show/

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የስሚዝ እድሜ ብዙ ሰዎችን እያነጋገረ ይገኛል!!!

ሰይፏ "እድሜህ ስንት ነው?

ስሚዝ "28"

ሰይፉ "እስኪ የት የት ሰርተሃል ከለቦች ላይ?"

ስሚዝ "ትምህርቴን ከሚሴ ጨረስኩ፤ ከዛ ደሴ 10 አመት ሰራሁ፣ ባህርዳር 6 አመት ሰራሁ፣ ዱባይ 5 አመት፣ አሁን ደሞ አዲስ አበባ 5 አመት ሆኖኛል ክለብ እየሰራሁ፡፡"

ይህ ማለት የሰራበት ብቻ 26 ሞልቷል ማለት ነው።
እርሶ ስለዚህ ምን ይላሉ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
ሰዋሰዉ መልቲ ሚዲያ እና ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በሙዚቃዉ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ።

ሰዋሰዉ መልቲሚዲያ እና ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በሙዚቃዉ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ። ወደ ኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ በተቀላቀለ በጥቂት ግዜያት ዉስጥ ከአንድ መቶ በላይ አንጋፋና ወጣት ድምፃዉያንን እና ሙዚቀኞችን በማስፈረም ዘርፉን በከፍተኛ ሁኔታ እያነቃቃ የሚገኘዉ ሰዋሰዉ መልቲሚዲያ እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሙዚቃ አልበሞች እና በኤቨንቶች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ዛሬ መጋቢት 06/2016 ዓም ተፈራርመዋል።

ከሰዋሰዉ ድምፃዉያን መካከል አንዱ የሆነዉ እና ከፋሲካ ፆም በኋላ የሚለቀቀዉን የአማኑኤል ሙሴ አልበም ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ የስፖንሰርሺፕ ድርሻዉን መዉሰዱ በዛሬዉ እለት ይፋ ተደርጓል።

በዝናር ዜማ የድምፃዉያን ስብስብ እራሱን ከህዝብ ጋር ያስተዋወቀዉ አማኑኤል ሙሴ ድንቅ ችሎታና አቅም ያለዉ ተስፈኛ ወጣት ድምፃዊ መሆኑ በመድረኩ የተነሳ ሲሆን ‘’ጥቁር ዉሃ’’ የተሰኘዉ አልበሙም በሳፋሪኮም አጋርነት በሰዋሰዉ አፕ የሚለቅቅ መሆኑ ተነግሯል።

ድምፃዉያኑ በመልቲሚዲያው በኩል ለአልበማቸዉ ከሚያገኙት ገንዘብ በተጨማሪ ከስፖንሰር አድራጊዉ ካምፓኒም ክፍያ እና ልዩ የሆኑ ጥቅማ ጥቅሞችን የሚያገኙ ይሆናል ይህም ሰዋሰው ለድምፃውያኑ ከሚያደርጋቸው ስኬቶች አንደኛው ነው ተብሏል።

ይህን አስመልክቶ የሰዋሰዉ መልቲሚዲያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብቱ ነጋሽ ድምፃዉያን የድካማቸዉን ዋጋ እንዲያገኙ ከዚህም በላይ መስራት ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን ፣ እንደ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ያሉ ግዙፍ ካምፓኒዎች ወደ ሀገራችን የሙዚቃ ኢንዱስትሪ መቀላቀላቸዉ ዘርፉን በሚገባ እንደሚደግፈዉም አንስተዋል።

Follow us on Social Medias
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
1👍1
የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ የትዳር አጋር የሆነችው አርቲስት አምለሰት ሙጬ የለንደን ካፌ የምግብ ዝግጅት እና አቅርቦት አገልግሎት ድርጅት የብራንድ አምባሳደር ሆና ተሾመች፡፡

የለንደን ካፌ ሳተላይት ሬስቶራንት እና የምግብ ዝግጅት በኤንኤችዋይ አስመጪ እና ላኪ ሥር በመሆን በሬስቶራንቱ ንግድ ከ20 ዓመታት በላይ ቆይቷል ፡፡

ድርጅቱም በአጠቃለይ 6 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን 2ቱ በአዲስ አበባ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍያ ውስጥ ይገኛል። 4ቱ ደግሞ ማስፋፍያ ተደርጎባቸው በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች እና ተዛማጅ ቅጂዎች የጋራ አስተዳደር ማህበር ለአባላቱ አስቸኳይ ጥሪ አስተላልፏል ።

አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ለሙዚቀኞች !

የፊታችን ሰኞ የካቲት 9 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እስከ 6:00 ድረስ ካዛንቺስ በሚገኘው የኢትዮጵያ አዕምሮ ንብረት ጥበቃ ባለሥልጣን መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ በመገኘት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ ሥራው በቅርቡ ስለሚጀመረው የሙዚቃ ሮያሊቲ ክፍያ የአሰባሰብ ሁኔታውንና የክፍፍል ድርሻን በተመለከተ ፣ እንዲሁም የመብት ጥሰትን ለማስከበር በአዲስ መልኩ ስለተደራጀው የሕግ ድጋፍን አስመልክቶ አጠቃላይ የሥራ ሪፖርት ይቀርባል። በመሆኑም የማኅበራችን አባል የሆናችሁና ፣ ጉዳዮ በቀጥታ የሚመለከታችሁ አካላቶች በሙሉ በዕለቱ በቦታው እንድትገኙ ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
ጊልዶ ካሳ የሚሰራቸው ዘፈኖች በኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ተመልካች አላቸው ተባለ!!

የሙዚቃ አቀናባሪው ጊልዶ ካሳ የሰራቸው የሙዚቃ ቅንብሮች በኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ ተጠቃሚ በሆነው በዩቲዩብ ከፍተኛ ተመልካች ካላቸው ሙዚቃዎች መካከል እንደሚመደብ ከሰዋሰው የህዝብ ግኑኝነት አዳነ አረጋ ፋስት መረጃ ተመልክቷል።

ባለፉት ጥቂት አመታት ባብዛኛ በጊልዶ ካሳ ግጥም እና ዜማ እንዲሁም ቅንብር የተሰሩ ስራዎች (የተወሰኑት ብቻ በቅንብር የተሳተፈባቸው ናቸው)

- ያሬድ ነጉ እና ሚለን (ቢራቢሮ) 31 ሚሊየን ቪው
- ሙሉአለም እና ኤፍሬም (ተሸንፊያለው) 25 ሚሊየን ቪው
- ሳንቾ (አታሳዩኛ) 20 ሚሊየን ቪው
- ማይኮ እና አስጌ (አኩኩሉ) 16 ሚሊየን ቪው
- ያሬድ ነጉ (ዞራ ዞራ) 14 ሚሊየን ቪው
- ሳንቾ (ታናሞ) 9.4 ሚሊየን ቪው
- ሚኪ ጎንደርኛ እና ሳንቾ (ሌባ) 10 ሚሊየን ቪው
- ዳጊ ዲ (በቃ) 16 ሚሊየን ቪው
- ጊልዶ (ላገባ ነው) 13 ሚሊየን ቪው
- ጊልዶ እና ሶል (ሲመሽ) 6.8 ሚሊየን ቪው
- ጊልዶ እና ሄኖክ (ብሶብኛል) 7 ሚሊየን ቪው
- ጊልዶ እና እንየው (ቢቻልሽ) 7 ሚሊየን ቪው
- ዳዊት መንግስቱ (ንገሪኝ) 6 ሚሊየን ቪው
- ፀገነት ሀ/ማርያም (ማሂላንዶ) 7.7 ሚሊየን ቪው
- ቤቲ ጂ እና አስጌ (ዞኖ ዞካ) 7.7 ሚሊየን ቪው
- ሳሚ ጎ (ኢትዮ ሼክ) 8.6 ሚሊየን ቪው
- ቡሪክ (ከኔ በላይ) 4.8 ሚሊየን ቪው

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
👍1
ድምፃዊት ዘቢባ ግርማ:-

ሳላውቅ ያስከፋኋችሁ ወገኖች በእግዚአብሔር ስም እና ሆዴ ውስጥ ባለችው ልጄ ስም ይቅርታ
እጠይቃችኋለሁ።

ሰው ግን አልተረዳኝም።
በርካታ የስድብ መሃት እየወረደብኝ ነው።
ሆድሽ ውስጥ ያለውን ልጅ አያሳቅፍሽ ሁሉ ያሉኝ አሉ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ከየተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ አዳዲስ ስራዎች በቅርቡ ሊታተሙ ነው።

መስከረም 17 ቀን 2015አም በድንገታዊ ህመም ህይወቱ ያለፈው አርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅ ህይወቱ ከማለፉ በፊት ሲሰራቸው የተበሩት የሙዚቃ ስራዎች ከተለያዩ አቀናባሪዎች እየተሰበሰቡ እንደሆነ እና በቅርቡ ለአድማጮቹ ሊደርሱ እንደሆነ ዋልያ ኢንተርቴይመንት መረጃውን ተሰምቷል።

5 የሚሆኑ የሙዚቃ አቀናባሪዎች ጋር እየተሰሩ የነበሩ 17 የሚደርሱ የሙዚቃ ስራዎች እስካሁን እንደተሰበሰቡ የጉዳዩ አስተባባሪ የሆኑት የግጥም እና የዜማ ደራሲ ዘላለም መኩሪያ ለዋልያ ኢንተርቴይመንት መረጃውን አድርሰዋል።

አብዛኞቹ ሙዚቃዎች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን የተወሰኑት ግን የሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ስራ እየተሰራላቸው ይገኛል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ለኢትዮጵያ ለሀገር እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ ያሉት

የኢትዮጵያ ሙዚቀኞች ( ዘፋኞች) የሙዚቃችን Copy Rights መብታችን ይጠበቅ

ሙዚቃችን እየተሰረቀ ና እየተቆራረጠ መፖሰት ይቁም::

የሙዚቃ መብታችን ሙሉ በሙሉ ይከበር በሚል ዙሪያ

* አመርቂ
* የኢትዮጵያን የድሀውን ማህብረሰብ ኑሮ የሚቀይር ና
* ለሀገር እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ ያለው ውይይት በተሳካ ሁኔታ አካሄዱ::