Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
"ካቀናበርኳቸው ሥራዎች ''ህመሜ'' የተሰኘውን የፀደንያ ገ/ማርቆስ ሙዚቃ ን አብልጬ እወደዋለሁ"

የመዚቃ አቀነባሪ አቤል ጳዉሎስ

በዘመኑ የተሠሩ ዝነኛ ዜማዎቹን ግጥማቸውን ከሙዚቃው ጋር ግሩም አድርጎ አወዳጅቷቸዋል። ከድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን እስከ ፀደንያ ገ/ማርቆስ ሙዚቃዎች ደረስ ደማቅ የቅንብር አሻራውን በብዙሃኑ የአልበም ሥራዎች ላይ አሳርፏል፡፡

ወጣቱ የሙዚቃ አቀናባሪ አቤል ጳውሎስ ቆየት ያሉ ሥራዎችን የማዳመጥ ልምድ እንዳለው የሚናገረው የሙዚቃ ባለሙያው አቤል ጳውሎስ፣ የቴዎድሮስ ታደሰ "የባህር ፈርጥ ነሽ" የተሰኘውን ተወዳጅ ሙዚቃ ቀዳሚው ስፍራ ላይ አስቀምጧል።

በዚህ ሥራ ላይ የሙያ አጋሩ አበጋዝ ክብረወርቅ የሙዚቃ ቅንብር ተጨምሮበት የቴዎድሮስ ታደሰ የአዘፋፈን ዘዬ ለዜማው ልዩ ውበት እንዳጎናፀፈው አጫውቶናል፡፡

በቀጣይነት የአቤል ሙሉጌታን ተገርሜ ሙዚቃ የምርጫዎቹ አካል አድርጎ በመዘርዝሩ ውስጥ አካቶታል።

አቀናባሪው በጥሩ ዝግጅት ተጠንቅቆ ለሚሠራቸው የራሱ ቅንብሮች የሚሰጠው ቦታ የተለየ ስለመሆኑ ካነሳልን በኋላ የራሱ የቅንብር ውጤት የሆነውን "ህመሜ" የተሰኘውን የፀደንያ ገ/ማርቆስ ሙዚቃ በተለየ መንገድ ከሥራዎቹ መካከል አብልጦ እንደሚወደው አስታውቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍2
ዛሬ ማርች 8 የሴቶች ቀን ነው።
ከወጣት ሴት ዘፋኞች እርሶ የማን አድናቂ ኖት?
Anonymous Poll
32%
ቬሮኒካ አዳነ
11%
ተአምር ግዛው
11%
ራሄል ጌቱ
0%
ሃና ግርማ
5%
ዘቢባ ግርማ
0%
ሜላት ቀለመወርቅ
26%
ሄዋን ገብረወልድ
16%
ሌላ (Others)
1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በሚያሸልመው ውድድር 6 የኢትዮጵያዊያን ስራዎች ለፍፃሜ ቀርበዋል ።

በኮራ የሙዚቃ ሽልማት ስነስርዓት 6 ኢትዮጵያዊያን በየዘርፋቸው 20 ለፍፃሜ ከቀረቡ ግለሰቦች እና ቡድኖች መካከል ተካተዋል ።

በባህላዊ (Traditional music ) ዘርፍ አስቻለው ፈጠነ ፣ በሴቶች ዘመናዊ ሙዚቃ (urban music ) ሄዋን ገብረወልድ ፣ በጥምረት ዘርፍ ( collaboration ) ጄሲ ሮያል ፊቸሪንግ ኒና ግርማ ፣ በሂፖፕ ልጅ ሚካኤል ፣ በቡድን ጃኖ ባንድ ሆነው ለመጨረሻ እጩነት ቀርበዋል ። ዳናይት ግርማ ደግሞ ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በሚለው በመዝናኛው ዘርፍ ተካታለች ።

በየምድቡ አሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች 50,000 ሺ የአሜሪካን ዶላር የተዘጋጀ ሲሆን ውድድሩ በ20 ዘርፍ ተመድቧል ። ኢትዮጵያም በ6 ዘርፎች ለመጨረሻው ውድድር የበቁ ተወዳዳሪዎች አግኝታለች ።

እስከ ሚያዝያ 4 2024 የፈረንጆች ዓመት ማለትም በቀጣይ አንደወር ውስጥ አሸናፊዎችን ለመለየት በተከታዩ አድራሻ ድምፅ ስለሚሰጥ በየዘርፏ የምትፈልጉትን 3 እጩዎች መምረጥ እንደምትችሉ ኮራ አዋርድ አስታውቋል ።
$50,000.
the KORA app and website.
🔗: https://bit.ly/49WorWn
#Kora2024 #Top20

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
" ለመላው የማኅበራችንና ፣ አገራችን የ #ሙዚቃ ባለሙያዎች በሙሉ "

የኢትዩጲያ የሙዚቃ ኮፒራይት የጋራ አስተዳደር ማኅበራችን በቅርቡ የሚጀመረውንና ፣የሙዚቃ ሮያሊቲን ጨምሮ አጠቃላይ የመብት ማስከበሩን ሂደት በተጠናከረ የሕግ ድጋፍ ለማስጀመር #ኢትዮሊጋልሺልድ #ELS ከተባለው የጠበቆች ድርጅት ጋር አዲስ ሥምምነት ተፈጽሞ ወደ ሥራው ተገብቷል ። በመሆኑም በማኅበራችን አባላቶችና፣ በመላው አገራችን ያላችሁ የሙዚቃ ባለሙያዎች የመብት ጥሰትንና ፣ መሠል ጉዳዮችን በተመለከተ ሥራው የተጀመረና ፣ጉዳዮቹን ይዛችሁ ወደ ማኀበሩ በመምጣት ግልጋሎቱን ማግኘት እንደምትችሉ እናሣውቃለን። #EMCCMO #ethiopianmusic

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የዕውቁ የግጥምና ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀ መፅሀፍ ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ሊቀየር ነው።

ዕውቁ የግጥምና ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀ መፅሀፉን ወደ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማነት ለመቀየር በእንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ አሳወቀ፡፡

መፅሀፉን በቅድሚያ በፊልም ለማምጣት ታስቦ ጥያቄ ቀርቦ እንደነበር ያስታወቀው ባለሙያው በመፅሀፉ ውስጥ ያሉ ሃሳቦች ተቆራርጠው እንዳይቀሩ በማሰብ በተከታታይ ድራማ መልክ ለማቅረብ መታቀዱን ገልጿል፡፡

ላምባን ጨምሮ የእግዜር ድልድይ እና ሌሎች ተወዳጅ የፊልም ስራዎች ላይ በዝጅግት ተሳትፎ ሲያደርግ የሚታወቀው የፊልም ባለሙያው አንተነህ ሀይሌ በአዘጋጅነት እንደሚሳተፍ አለማየሁ ደመቀ በተጨማሪነት አንስቷል፡፡

የመፅሁፉ ሁለተኛ ክፍል በቅርቡ ለገበያ እንደሚቀርብ የገለፀው አለማየሁ የዮቶር ቁጥር 1 ሕትመትም ወደ 14ተኛ ላይ እንደደረሰ ያስታወቀ ሲሆን ይኽኛውም ዕትም ተያይዞ ለገበያ እንደሚቀርብ አስታውቋል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
የባላገሩ ምርጥ ዉድድርን 3ኛ በመዉጣት ያሸነፈው ቅዱስ ዳምጤ ወደ ትዉልድ ከተማው ጅማ ሲገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

የጅማ ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት፤ የከተማው መስተዳደርና የባህልና ቱሪዝም ቢሮ በጋራ ባዘጋጁት ደማቅ የአቀባበል ስነ-ስርዓት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና በርካታ የከተማው ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን ቅዱስ ዳምጤ በባላገሩ ምርጥ የውድድር ታሪኩ የትውልድ ስፍራውን በማስተዋወቅ ላደረገው ከፍተኛ አስተዋፅዖ ምስጋናና የ140 ካሬ ሜትር የመሬት ስጦታ ተበርክቶለታል።

ከፍተኛ ፋክክር በተደረገበት የባላገሩ ምርጥ የድምጻዉያን ዉድድር በድንቅ የመድረክ ብቃት ባቀረባቸው የሙዚቃ ስራዎቹ ከፍተኛ አድናቆትን ያተረፈው ቅዱስ ዳምጤ ከሌላኛው ተወዳዳሪ ከእስማኤል መሐመድ (ስሚዝ) ጋር በእኩል ነጥብ የ250 ሺህ ብር ሽልማት እና ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር የሚያወጡ ዘፈኖች ለእያንዳንዳቸው የተሸለሙ ሲሆን ቅዱስ በጥቅሉ የአንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት አሸናፊ በመሆን ሶስተኛ ሆኖ አጠናቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምፃዊ አለማየሁ ሂርጶ ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በኖርዌይ ታሰሩ።

በአውሮፓ ኖርዌይ ከ20 አመት በላይ ቢኖሩም በድንገት በርካታ ኢትዮጵያ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አለባችሁ በማለት ለእስር እንደተዳረጉ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ቅሬታቸውን ለታዲያስ አዲስ ማሰማታቸውን ፋስት መረጃ ሰምቷል። ለእስር ከተዳረጉ ኢትዮጵያዊያን መካከል በህመም ላይ የሚገኘው ድምፃዊ አለማየሁ ሂርጶ እንደሚገኝበት ተነግሯል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኖርዌይ መንግስት ጋር በመነጋገር ለእስር የተዳረጉ ኢትዮጵያዊያን መፍትሄ ይሰጠን ብሏል። ለበርካታ አመታት ትዳር መስርተን እየኖርን ነው ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አንፈልግም ብለዋል።