Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
👤 Aschalew Fetene | አስቻለው ፈጠነ
🎵 Aschale | አስቻለ
━━━━━━━━━━━━━━
➠ RELEASED: 2024
➠ GENRE: #Ethiopian
➠ TYPE: #Album
➠ TRACKS: 14
➠ FORMATS: #Mp3
➠ CHANNEL: @Waliyaentmt
━━━━━━━━━━━━
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Aschalew_fetene #Album #Ethio_albums #Waliya_Entertainemnt
👍1🔥1
ትናንት ከተለቀቁት አልበሞች ውስጥ የቱን ይበልጥ ወደዱት?
Anonymous Poll
42%
ቴዲ ዮ - ይለያል
31%
የማ - የደጋ ሰው
27%
አስቻለው ፈጠነ - አስቻለ
👍2
ድምፃዊ ኤፍሬም አማረ እና ተዋናይት ፍርያት የማነ የመጀመሪያ ልጃቸውን ካገኙ በኋላ ከመላው አድናቂዎች ለተሰጣቸው የደስታ መልዕክት እናመሰግናለን ብሏል። በተለይ ተዋናይት ፍርያት የማነ ባለፉት ሶስት አመታት የደረሰባትን በዝምታ ለምን እንዳለፈች በቅርቡ ሁሉንም ይፋ እንደምታደርግ ገልጻለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
Waliya Entertainment
ትናንት ከተለቀቁት አልበሞች ውስጥ የቱን ይበልጥ ወደዱት?
የደጋ ሰው ፤ የጂጂ ደቂቅ 

የባለቅኔዋ ቃል 'እምዬ እናት ዓለም እስቲ አንቂኝ ከእንቅልፌ' የሚል ነው፡፡ የባለቅኔዋን ልመና እና የእምዬን አደራ ዝቅ ብለው የተቀበሉ ጎበዛዝት መጥተዋል፡፡

ስማችሁ ማን ነው ቢባሉ ፤ የደጋ ሰው የተባሉ በጎ ወራሽ ናቸው፡፡

በባዶ ቤት የሸፈትን ÷

መለኞቹ ደግ ነገር ሲያዩ ÷ ታጠቅ የአገር ልጅ ይህ ነገር የኛ ነው ይላሉ፡፡
የደጋ ሰው ምልምል የኛ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ንዋይ ከማትነጥፈዋ እመቤት እያለበ የሚያጠጣ ግት ነው፡፡

ጋሽ ብርሃኑ ድንቄ ስለራሷቸው ትውልድ ሲናገሩ ÷ የኔ ትውልድ 'በባዶ ቤት የሸፈተ' ነው ይላሉ፡፡

ይህ የዘመናይ ሽፍታነት የአገርን የልብ ተክልን ካለማወቅ ፣ ነብስ የሚነበብበትን ባለአገርን ካለመረዳት ፣ የፍቅር ገት የሆነውን አድባርን ከመናቅ የተገኘ ትእቢት ነበር፡፡

ዘመናይ ሁነው በባዶ ቤት የሸፈተው ትውልድ እና ዘመን 'የኢትዮጵያን መንፈስ' ቀላዋጭ አድርጓል፡፡ በጀነራል አቢይ አበበ ቋንቋ አገር የምትኖርበትን ዘዴ አጥብቆ ካለማወቅ ማጥ ውስጥ ከቶናል፡፡ (Poverty of the spirit)

የታላቁ የሀዲስ ዓለማየሁ የጠራ እውቀት ኢትዮጵያዊ መንፈስ እና ስርዓተ ማኅበር የተጎዳበትን መንገድ ከስር እስከ ራሱ ተናግረውት ነበር፡፡ 'የራስን የኑሮ ልማድ እየተው ባእድ ስራተ ማህበር ይዞት የመጣው መንፈስ ውርሱ ውሎ አድሮ አደገኛ ነው ብለው ነበር፡፡

የሆነብን ይህ ነው ÷

የአገሩን ዜማ የማያውቅ ፣ የወንዙን ገደላ ገደል የማይረዳ ÷ የእናቱን ጉርሻ ባእድ የሆነበት ÷ የወንድሙ ልሳን የሚያቀረሸው ÷ የባለአገሩን ሙያ የረሳ ከርስቱ ፤ ከግርማው የተሰደደ ትውልድ እና ዘመን ላይ ደረስን፡፡ (Shared Nationhood in crisis)

የጋሽ ብርሃኑ ድንቄ ኑዛዜ እና የጋሽ ሀዲስ ዓለማየሁ ፍርሃት እኛ በብሌኑ አየነው፡፡ (Syndrome circle) 

የማየው ወጋገን ምንድን ነው?

በፍሩድ ቋንቋ የተጨቆነው ኢትዮጵያዊ መንፈስ ተመልሷል፡፡ ይህ መንፈስ የአባታችሁን ተው ተብሎ የተዘመተበት ÷ ራስን በራስ የማዳን ጸጋ የለህም የተባለውም ነው፡፡ (Return of the repressed)

የደጋ ሰው አልበም ምርቃቱ የተጨቆነውን እና የተዘመተበትን ኢትዮጵያዊ መንፈስ አድባር መቆሚያው አድርጎ ፣ ቅጥ ባለው ቃል ልሳንኑ እያሰፈረ ፣ እመቤቴ ኢትዮጵያ ሆይ ተመለሺ ÷ ተመለሺ እያለ ሰርግና ምላሽ ላይ አደረሰን፡፡

አልበሙ እንደ አገሬ ሰው የደራ ፍቅርን ከጀግንነት ጋር የሚያጋባ ፣ ጠበቅ ያለ የአእምሮ ግጥሚያን በቅኔ እና በወርቅ የሚያቆም ፣ ባእድ የሆነውን ድምጽ እና ባሕልን በኢትዮጵያዊ መንፈስ አጥምቆ ለዓለም የሚንጠራራ ክፍት መሆኑ ከእህህ ወዲያ ያለውን አገራችንን እንድንተልም ያነቃል፡፡ (The narrative tone)

ፈረንጁ ዶናልድ ዶናሃም ይህን የመዳን እና ክፉ ቀንን የማሸነፍ ትግልን Spiritual Hibernation ብሎታል፡፡ ክፉ ቀን እንዳይመታህ ከመሸሸግ ይልቅ መዳኛውን ከባሕልህ ማህፀን ፣ ከሕብረተሰብህ ምንጭ እና ከተራራህ ውስጥ ፈልገህ ማግኘትን ይጠይቃል፡፡

ይህ ተጋድሎ በፕ/ር ማእምር እንዲህ ይሉታል 'Epistemic resistance creates the intellectual and cultural grounds for the emergence of Ethiopia'

ለዛ ነው ወደ አገርህ ስትቀርብ ፣ ወደ ባለአገርህ አንገትህን አዙረህ ስትመለከት መዳኛውን ቅጠል ፣ መቆሚያውን እግር ይገኝበታል፡፡ ይህን የመዳን ቀን ተጋድሎ ፕ/ር አበበ ዘገየ Close to the source ይሉታል፡፡

የደጋ ሰው አልበም ÷

የኢትዮጵያ መንፈስ መገኛ የሆነችው እምዬ እናት ዓለም አንቅታው ÷
ሐብታቷን ዳሶ በዜማ ፣ በድምጽ እና በሕይወታዊ እሙንነት ጠርቶ የኛ ሁኗል፡፡ (Maximizing Indigenous Values)

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music