Waliya Entertainment
287 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ኤባ የሙዚቃ አልበም ታህሳስ 5 ሊወጣ ነው።
#Maleda
ናሆም ሪከርድስ የድምጻዊ ተስፋዬ ጥላሁን (ማሾ)ን የሙዚቃ አልበም ለማሳተም፣ በሲዲ ለማሰራጨትና በቲዩብ ቻናሉም ለመልቀቅ መስማማቱን ዛሬ በኢሊሌ ሆቴል በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስረድተዋል።

ኤባ (EEBBAA) በውስጡ 14 ሙዚቃዎችን የያዘ ሲሆን ብርሃኑ ድጋፍ (ሚሊሻ) ሙዚቃን በማቀናበር፣ ሰሎሞን ኃ/ማርያምና ታምራት ድሪባ በሚክሲንግ፣ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሺዎታ በማስተሪንግ፣ ይትባረክ ክፍሌ በማስተሪንግ፣ ኢብራሂም ማሞ፣ ሄኖክ ለማ (ጎፈር)፣ ኮሜዲያን ታኬ፣ ፋሲል ከበደ፣ አናን ሙሜ እና ሌሎችም በግጥም እንደተሳተፉበት ተገልጿል። አልበሙ

የአርሲ፣ የሸዋ፣ የሐረርጌና የቦረና የኦሮምኛ ሙዚቃዎች ያሉት ሲሆን ኢትዮጵያዊውን ጀግና አብዲሳ አጋንም የሚያወድስ ሙዚቃ እንደተካተተበትና ታህሳስ 5/2016ዓ.ም በናሆም ሪከርድስ የቲዩብ ቻናል በኩል ለህዝብ እንደሚደርስ ተነግሯል።

በአርሲ አቡራ አካባቢ የተወለደው ድምጻዊ ተስፋዬ ጥላሁን ወደ አዲስ አበባ በልጅነት ዕድሜው ከመጣ ወዲህ ከፍተኛ የሙዚቃ ፍቅር ስላደረበት ወደ ሙዚቃው አለም እንደተቀላቀለ በመግለጫው ተገልጾልናል።

Here is the link for all social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt