Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
እውቋ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ ኬቲ ፔሪ የጠፈር ጉብኝቷን አጠናቃ ተመለሰች

የፖፕ ኮከቧ ኬቲ ፔሪን ያካተተው የብሉ ኦርጂን ኩባንያ የጠፈር ቡድን ሰኞ ማለዳ ወደ ጠፈር ለጉብኝት ተጉዟል።

በረራው በሙሉ የሴቶች ቡድን የተደረገ ሲሆን እንደ ኩባንያው ገለጻ ይህ በረራ ከአውሮፓውያኑ 1963 ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በሴቶች የተደረገ የጠፈር በረራ ሆኗል::

ከታዋቂዋ አቀንቃኝ ኬቲ ፔሪ ጋር፣ የብሉ ኦርጂን ባለቤት የሆነው የጄፍ ቤዞስ እጮኛ ላውረን ሳንቼዝም በጉብኝቱ ውስጥ ተካታለች።

ኬቲ ፔሪ ከብሉ ኦርጂን የጠፈር በረራ አጠናቃ ወደ ምድር እንደተመለሰች ደስታዋን እና ምስጋናዋን ገልጻለች።

ሙዚቀኛዋ ልምዷን "ሕይወትን የሚቀይር" በማለት ስትሰይም በረራው ስለሚሰጠው ጥልቅ የአመለካከት ለውጥ አፅንዖት ሰጥታ ተናግራለች::

"ይሄ ከሁሉ የላቀ መንፈሳዊ ተሞክሮ ነው" በማለት ነው የገለፀችው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #kettyperry