" ሻንጣዎቼን ሊሰጠኝ አልቻለም" ሲልቨር
ታዋቂዋ ሩዋንዳዊት ዳንሰኛ ሼሪ ሲልቨር እንደገለፀችው ወደዛንዚባር ጉዞ ያደረገችው በትሬስ የሙዚቃ አዋርድና ፌስቲቫል ላይ ስራዋን እንድታቀርብ በመጋበዟ ነበር፡፡ በማህበራዊ ሚዲያዋ ላይ ባሰፈረችው ሀሳብ ስትናገር ‹‹በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዝኩት ለእኔና ከኔ ጋር አብረውኝ ለሚሰሩ ባለሙያዎች አስር ትኬት ቆርጬ ነበር፡፡ ይሁንና አየር መንገዱ ዛንዚባር ያደረሰኝ ቢሆንም ሻንጣዎቼን ግን ሊሰጠኝ አልቻለም›› ብላለች፡፡
ጨምራም ‹‹በሻንጣዎቹ ውስጥ ያሉት በዚህ ትልቅ ኮንሰርት ላይ የምለብሳቸው ልብሶች ነበሩ፡፡ ያለፉትን ሶስት ቀናት አየር መንገዱ ሻንጣዎቼን እንዲያስረክበኝ ብጠይቀውም ሊሰጠኝ አልቻለም፡፡ አሁን ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም፡ በጣም ተበሳጭቻለሁ›› ያለችው ዳንሰኛዋ ልብሶቹ በልዩ ትእዛዝ ለኮንሰርቱ የተሰሩ መሆናቸውን ገልፃለች፡፡ ሻንጣዎቹን ካላገኘች ስራዋ እንደሚበላሽባትም አስታውቃለች፡፡
በዛንዚባር የሚከናወነው የትሬስ አዋርድና ፌስቲቫል ዛሬ የተጀመረ ሲሆን ሲልቨር ስራዋን እንድታቀርብ ፕሮግራም የተያዘላት ነገ ረቡዕ ነው፡፡ በጉዳዩ ላይ አየር መንገዱ እስካሁን ያለው ነገር የለም፡፡
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #tracemusic