Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የመሃሙድ አህመድ የስንብት ፕሮግራም አርቲስቱን ከማስከበር ይልቅ ለገንዘብ የተሰራ ነው ሲሉ የተለያዩ አድናቂዎቹ ተናገሩ።

የመሃሙድ አህመድ የስንብት ፕሮግራም በቅርቡ በሚሊኒየም አዳራሽ በ ጆርካ ኢቨንት እና በዳኒ ዴቪስ አማካኝነት መዘጋጀቱ ይታወቃል። ምንም እንኳን አርቲስቱን ለማክበር የተዘጋጀ ፕሮግራም ቢሆንም ነገር ግን በቦታው ላይ የተገኙት አድናቂዎቹ በጣም የወረደ ዝግጅት እንደሆነ ከድምፅ ጥራት ጀምሮ በሰአቱ አለመጀመር እንዲሁም ከተጋበዙት ትላልቅ ድምፃዊያኖቹ ውስጥ የመሃሙድ ስራን የተጫወተው አንድ ሙዚቀኛ ብቻ መሆኑ እንዲሁም የ vip ትኬት የገዙት ሰዎች ልዩ ምግብ እና መጠጥ እንደሚዘጋጅላቸው ቢተዋወቅም ነገር ግን በጣም ውድ የሆኑ መጠጦችን በገንዘባቸው እንዲገዙ ዝቅ ያሉ መጠጦች እንደ ቢራ አይነቶቹ ጭራሽ እንዳይኖሩ መደረጋቸው ታዳሚዎች የተጭበረበሩ እንደመሰላቸው አዘጋጆቹ ለመሃሙድ አህመድ የማይረሳ ምሽትን ከመፍጠር ይልቅ ለራሳቸው ገንዘብ ማካበትን እንደፈለጉ ያስታውቃሉ ሲሉ የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ቅሬታቸውን ገልፀዋል።

የፕሮግራሙ አዘጋጆች ከኢትዬፒካሊንክ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስም ለዝግጅቱ ከ42 ሚሊየን ብር በላይ ከራሳቸው ማውጣታቸውን የገለፁ ሲሆን የተለያዩ ችግሮች ቢያጋጥሟቸውም ችግሮችን በተገቢ ሁኔታ በመፍታት ሁሌም የሚኮሩበትን ዝግጅት በብቃት ማዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Mehamud_ahmed #jorkaevent