የሮያሊቲ ክፍያ የሚጀመርበት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።
የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረቶች የሚጠናከሩበትና ሥራ የሚጀምሩበት ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል።
ፕሮጀክቱ በሰላም ኢትዮጵያ እና በሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በዩኔስኮ የገንዘብ ድጋፍ የተቀረፀ ሲሆን፤ የሚተገበረው በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን እና በኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማህበራት ህብረት ትብብር ነው።
ፕሮጀክቱ የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች በባለሙያዎችና በሕግ አስከባሪዎች እንዲሁም በመንግሥት አካላትና በሞያ ማህበራት ዘንድ ስላላቸው ተጠቃሚነት ግንዛቤ የሚፈጥር ነው።
መብቶቹን የማክበር ባህልንም የሚያሳድግ እንደሆነ ዛሬ በተካሄደው የፕሮጀክቱ የማስተዋወቂያ መድረክ ተገልጿል።
ፕሮጀክቱ የሕግ ማዕቀፎች ዝግጅትና የኮፒ ራይት ምዝገባን፤ እንዲሁም ባለሙያዎች የፈጠራ ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲጠብቁ የሚያስችሉ የተለያዩ ስልጠናዎችን መስጠትን ያካትታል።
ለሚቀጥሉት 18 ወራት የሚተገበረው ፕሮጀክቱ በዘርፉ እና በዘርፉ ተዋንያን ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ተብሏል።
የአዕምሯዊ ንብረት መብቶች ማጠናከር ፕሮጀክቱ በተለይ የስነ ስዕል፣ ቅርፃቅርፅ፣ ፊልም፣ ቲያትር፣ ሙዚቃና ውዝዋዜ እና መሰል የኪነጥበብ ዘርፎችን በከፍተኛ ሁኔታ ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #royality