Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
🎂መልካም ልደት ለ አርቲስት ኤሊያስ የማነ (ኪዊ)🎂

በ90 ዎቹ ገነው ከነበሩ ሙዚቃዎች መሀል "ይበቃል" የተሰኘ በብዙዎቹ ዘንድ ተወዳጅ የነበረውን ሙዚቃን እና "አንቺ ስትሳሚ" የተሰኘ አልበምን በሙዚቃ ሊቅ ኤልያስ መልካ አቀናባሪነት ያደረሰን ሲሆን በህትመት ላይ ባጋጠመ መጠነኛ እክል ምክንያት አልበሙ ከገበያ ላይ እንደተሰበሰበ የምናስታውሰው ነው። ወደፊት በድጋሚ ገበያ ላይ ለማዋልም እየተሰራ እንደሆነ ከአንዳንድ ምንጮች መረዳትም ችለናል።

ኤልያስ ኪዊ መኖሪያውን ከሃገር ውጪ በተለያዩ ሀገራት ያደረገ ሲሆን በአሁኑ ሰአት በአውስትራሊያ እየኖረ ይገኛል ከአንድ አመት በፊት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በዝክረ ኤልያስ መልካ 3 ላይ ተገኝቶ ከኤልያስ ጋር የነበራቸውን ትውስታ በሰፊው አካፍሎን እንደነበር የሚታወስ ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #kiwi