Waliya Entertainment
295 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ድምጻዊ ዮሐናን የካሴት ኦድዮ ስራዎች የብራንድ አምባሳደር ሆነ

ካሴት የኦዲዮ ስራዎችን ማለትም ዘፈን፣ መዝሙር፣ ወግ፣ ትረካ፣ ግጥም በጃዝና መሰል ስራዎችን ለአድማጮች በጣም ቀላል በሆነ መንገድ ለመሸጥ ታልሞ የተሰራ የቴሌግራም ቦት እንደሆነ ዛሬ ሐምሌ 29/2016 ዓም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ተደርጓል።

ካሴት በኦንላይን ኮሙኒኬሽን የበለፀገ ሲሆን አድማጮች በቀላሉ በስልካቸው ላይ ሌላ አዲስ መተግበሪያን መጫን ሳያስፈልጋቸው በሚያዘወትሩት ቴሌግራም ላይ @kasetrobot ብለው ቦቱን በመቀላቀል መጠቀም እንደሚችሉ በመግለጫው ተገልጿል።

አቶ ናሆም በለጠ ካሴትን ያበለፀገው ድርጅ የኦንላይን ኮሙኒኬሽን መስራች እና ስራ አስኪያጅ ናቸው "አርቲስቶች በካሴት ቴሌግራም ቦት ስራዎቻቸው ለገበያ ሲያውሉ አድማጮች የገዙትን አልበም ለሌሎች መላክና መስጠት የማያስችል በመሆኑ የኮፒራይት ጥሰትን ይከላከላል፡፡ በተጨማሪም እያንዳንዱን ሽያጭ መከታተል ሚያስችል የድሀረ-ገፅ መግቢያ ስለሚኖራቸው አሰራሩን ግልጽ ያደርገዋል" ብለዋል።

በ3 ቋንቋዎች አማርኛ፣ እንግሊዘኛ እና አፋን ኦሮሞ አማራጭ የቀረበ ሲሆን በሰከንዶች ውስጥ አልበሙን በቴሌብር እና ኤም.ፔሳ ገዝተው ማዳመጥ እንደሚቻል በመግለጫው ተብራርቷል።

በቅርብ ጊዜ በርካታ ተወዳጅ ሙዚቃዎችን ለህዝቡ እያደረሰ የሚገኘው ተወዳጁ ወጣት ድምፃዊ ዮሐና ከፍተኛ ክፍያ በተባለልት የካሴት ብራንድ አምባሳደር በመሆን በመድረኩ ሹመቱን ተቀብሏል።

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Yohanna #Music
ዮሐና አሸናፊ በአዲስ አመት አዲስ አልበም ይዞ እየመጣ ይገኛል በዚህ የመጀመርያው የአልበም እንደሚለቀቅ ያበሰረው ዮሐና አሸናፊ ነው፡፡

በማህበራዊ ገፁ ይንን ብሏል፡፡
“ጤና ይስጥልኝ ነግቷል አዲስ አመት መጥቷል ….. አዲሱ አመት አኔ ጋር አዲስ አልበም ይዟል!እናንተጋስ?” ሲል ገልጿል”፡፡ ብሏል፡፡
...

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yohanna