Waliya Entertainment
295 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ፈታ ሾው በትልቅ የሙዚቃ ሽልማት መጣ!!!

ከዚህ በፊት ሁለት አርቲስቶችን በመጋበዝ የትክክለኛ ዘፋኙን የአፍ እንቅስቃሴ አስመስሎ በመስራት (Lip sync) ሲያወዳድር የነበረው ፈታ ሾው በመባል የሚታወቀው ተወዳጁ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አሁን ደግሞ በትልቅ የሙዚቃ ሽልማት ዝግጅት ብቅ ሊል ነው።

ከዝግጅቱ ዋና አዘጋጅ ጌታነህ ፀሃዬ እንደሰማነው ዝግጅቱ እስካሁን ከለመድናቸው የሙዚቃ ሽልማት ፕሮግራሞች በብዙ መልክ የተለየ እንዲሁም ብዙ የሽልማት ዘርፎችንም እንደያዘ ገልፀዋል።

አያይዘንም ስለ ፈታ ሾው የመመለስ ሁኔታ አለው ወይ ብለን በጠየቅናቸውም መሠረት ፈታ ሾው በቅርብ ጊዜ በአባይ ቲቪ የሚመለስ እንደሆነ የገለፁልን ሲሆን ቅድሚያ ዝግጅቶች አልቀው የተወሰኑ ክፍሎችም አንደተቀረፁ ገልፀውልናል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Feta_show
አፍሪክለብ ኦቨርሲስ ኮንሰልተንሲ ሼር ካምፓኒ ድምፃዊ ቤተልሔም ሸረፈዲንን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ

አፍሪክለብ ኦቨርሲስ ኮንሰልተንሲ ሼር ካምፓኒ ድምፃዊ ቤተልሔም ሸረፈዲንን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን በዛሬው እለት በሳፋየር አዲስ ሆቴል ባካሄደው የድርጅት ትዉዉቅ መርሀገብር አስታውቋል

በመርሀገብሩ ላይ እንደተጠቀሰው መንግስት ለጀመረዉ የኢኮኖሚ ግንባታ የበኩሉን ለመደገፍ አፍሪክለብ አቨርሲስ ኮንሰልተንሲ ሼር ካምፓኒ የተማሩ ፣ የሰለጠኑና በከፊል የሰለጠኑ ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በዉጭ ስራ ዓለም በመሰማራት ራሳቸዉንና ቤተሰባቸዉን እንዲጠቅሙ እንዲሁም አገራችን ኢትዮጵያ ከዚህ የምታገኘዉ ዘረፈ ብዙ ጠቀሜታ ማለትም ከዉጭ ስራ ዕድል ተጠቃሚዎች ወደ አገር ዉስጥ የሚገባዉ የዉጭ ምንዛሪ ፤ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሽግግር ከፍተኛ ጥቅም እንደምታገኝ ታሳቢ በማድረግ የዉጭ የስራ እድልን በህጋዊ መንገድ ለማስኬድ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡

ደርጅቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የዉጭ አገር ስራ ዕድል ፈለጊ ኢትዮጵያዉያን የማማከርና የማሳለጥ አገልግሎት ፣ የዉጭ አገር የትምህርት እድል ማፈላለግ፣ ማማከርና ማሳለጥ ፣ በኦንላይን የዉጭ አገር ቋንቋ ስልጠና መስጠት ፣ የዉጭ አገር የንግድና የምርት ማስተዋወቅ ዝግጅቶች ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ነጋዴዎችና አምራቾች የማማከርና የማሳለጥ ስራዎች መስራት ፣ በዉጭ አገር ህክምና ለሚፈልጉ ኢትዮጵያዉያን ቪዛ የሚያገኙበት ሂደት ማማከርና ማሳለጥ እንዲሁም ኢትዮጵያዉያን ዜጎች የቱሪስት ቪዛ የሚያገኙበትን ሂደት ማማከርና ማሳለጥ እንደሆኑ ተገልጿል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
ፈታ ሾው በአባይ ቴሌቪዥን በአዲስ መልክ ሊጀመር ነው ተባለ።

የፈታ ሾው ወደ ሚዲያ ሊመለስ እንደሆነ ዛሬ ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም በአባይ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

ከአመታት በኋላ በአዲስ አመት መስከረም 1 በአባይ ቴሌቪዥን ፈታ ሾው "ፈታ ሙዚቃ ሽልማት" የተሰኘ አዲስ ነገር ይዘው መምጣቱን አርቲስት ጌታነህ ፀሐዬ ገልጿል።

በፈታ ሙዚቃ አዋርድ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ያለምንም ቀጥተኛ ውድድር ላበረከቱት አስተዋጾ ለሰራቸው እውቅናን የሚያገኙበት ሁሉን ያካተተ እና አሳታፊ መድረክ ለመፍጠር እንደሆነ ጌታነህ ተናግሯል።

ዝግጅቱ የኢትዮጵያን ባህላዊ እና ዘመናዊ ገፅታዎች ለማንፀባረቅ በትኩረት የታቀደ የሸልማት ትእይንት ብቻ ሳይሆን የባህል አከባበርም ነው ተብሏል።

የፈታ ሙዚቃ አዋርድ ነሀሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በብሄራዊ ቴአትር ሸልማት ሰርዓቱ የሚካሄድ ሲሆን መስከረም 1/2017 ዓ.ም በአባይ ቴሌቪዥን ይተላለፋል።

ፈታ ሙዚቃ አዋርድ በ2016 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን ሰኬት ከማክበር ባለፈ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን እንደያዘ የማክበር እና የመጠበቅን ስርዓት በማስቀጠል የሙዚቃውን ብሎም ሙዚቀኛውን ማስከበር ነው ተብሏል።

ፈታ ሾው "ፈታ በአባይ" በተሰኘ ስያሜ በአዲስ አመት በአባይ ቴሌቪዥን መተላለፍ ይጀምራል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"አንድ ቃል" ነሐሴ 17

የተወዳጁ ድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ "አንድ ቃል" የተሰኘው ሶስተኛው የሙዚቃ አልበሙ በዕለተ ዓርብ ነሐሴ 17 ይለቀቃል።

ከዚህ በፊት ከሰራቸው ስራዎች የቱን ትወዱታላችሁ?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
#Album #michaelbelayneh #Andkal
የቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበም በ17 ሚሊየን ብር ተሸጠ።

በብዙ ተወዳጅ ዘፈኖቿ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈችው ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ አዲስ አልበሟ ነሃሴ 17 ለህዝብ ተመልካቹ የሚቀርብ ሲሆን በ160ሺ የአሜሪካ ዶላር ወይም ከ17ሚሊየን ብር በላይ መሸጡን ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከውስጥ አዋቂዎች ማወቅ የቻለ ሲሆን ይህም በኢትዬጲያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ሪከርድ የሰበረ እንደሆነም ማወቅ ችለናል።

አልበሙን የገዛው "Zojak worldwide" የተሰኘው የአሜሪካ አሳታሚ ድርጅት ሲሆን በዋናነት የተለያዩ መተግበሪያዎች ላይ የአርቲስቶችን ስራ የሚያከፋፍል ነዉ።

አልበሙ 12 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ቅድሚያ ለ 2 ዘፈኖች ሺዲዬ በአሜሪካ ሃገር እንደተሰራላቸው አልበሙ በሚለቀቅበትም ቀን በእኩል ሰአት እንደሚለቀቁም በተጨማሪም ግዢው ቪዲዬ ክሊፖችንም እንደሚጨምር ለማወቅ ችለናል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Veronica_adane
ያወቀ ይሸለማል🏆🏆🏆

የልጅቷን እና የአባትዋን ስም በስትክክል ለመለሱ ለ3 ልጆች የ 100ብር ካርድ ይሸለማሉ!!!!

ለመሸለም ሼር ማድረግ የግድ ነው!!!

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ዶክተር ድሬ በኦሊምፒክ ለመወዳደር እንደሚፈልግ አስታወቀ

የ59 ዓመቱ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ድምፃዊና ገጣሚ ዶክተር ድሬ “ኢንተርቴይንመንት ቱናይት” በተባለ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ቀርቦ “በ2028 ኦሊምፒክ ላይ ለመሳተፍ እየሞከርኩ ነው፤ የምሬን ነው፤ የቀስት ኢላማ ውድድርን ከመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ እወዳደር ነበር” ብሏል።

ዶክተር ድሬ ወይንም በመዝገብ ስሙ አንድሬ ሮሜል ያንግ “አሁን በግቢዬ ውስጥ መለማመጃ አዘጋጅቻለሁ፤ በኦሊምፒክ ለመሳተፍ በ77 ጫማ ርቀት ብቁ መሆን እንደሚጠይቅ ሰምቻለሁ፤ ሆኖም እኔ በ90 ጫማ ርቀት እየተለማመድኩ ነው” በማለት ለጉዳዩ ትኩረት እንደሰጠው ገልጿል።

የ2028 ኦሊምፒክ አዘጋጇ ደግሞ የዶክተር ድሬ መኖሪያዋ ሎስ አንጀለስ ከተማ መሆኗ ደግሞ ዝነኛው የሙዚቃ ባለሙያ በውድድሩ የመሳተፉ ውሳኔ አይቀሬ ይመስላል።

ዶክተር ድሬ ዴዝሮው ሪኮርድስ የተባለ የሙዚቃ ስቱዲዮ እና ቢትስ ኤሌክትሮኒክስ የተባለ ኩባንያ ባለቤት ሲሆን ለቱፓክ፣ ስኑፕ ዶግ፣ ኤምነም፣ 50 ሴንት፣ ቲአይና ሜሪ ጄ ብላይጅ ለመሳሰሉ ታላላቅ ራፐሮች ሙዚቃ አዘጋጅቷል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #dr_dre
አህመድ ማንጁስ የመጀመሪያ ሙሉ አልበም ስራውን ማጠናቀቁን አስታውቋል ።

"ከብዙ ድካም እና ልፋት በሗላ #አልጣሽ የተሰኘው የመጀመሪያ ሙሉ አልበሜን ወደእናንተ አድናቂዎቼ እና ወዳጆቼ ለማድረስ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ:: በቅርብ ቀን #አልጣሽ አልበም ይለቀቃል።" - አህመድ ማንጁስ

በአልበሙ ላይ አንጋፋ እና ወጣት ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን

በዜማ
- አበበ ብርሀኔ 6 ዜማ
- አቤል ሙልጌታ 4 ዜማ እና ግጥም
- አህመድ ተሾመ ( ዲንቢ ) 1 ዜማ

በግጥም
- ይልማ ገብረአብ 4 ስራ
- ናትናኤል ግርማቸው 1 ስራ
- መሰለ ጌታሁን 1 ስራ
- ተስፋ ብርሀን 1 ስራ

በቅንብር
- አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ 8 ሙዚቃ
- አቤል ጳውሎስ 3 ሙዚቃ

እንዲሁም ሁሉንም 11 ሙዚቃዎች ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ አድርጏቸዋል::

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Ahmed_manjus
🔥የልቤን አልበም🔥ይመረቃል

የልቤን የተሰኘው የ ድምፃዊ መሳይ ተፈራ የሙዚቃ አልበም ምርቃት ድግስ ቅዳሜ ነሃሴ 18  2016 ወዳጅና የሙያ አጋሮቹ በተገኙበት ይመረቃል::

ቦታ:-ማሪዮት ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል
የሚጀምርበት ሰዓት :12 ሰአት

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #yelben #messay_tefera
በኢትዮጵያዊያን በዩቲዩብ በብዛት ተመልካች ያገኙ 10 የሳምንቱ ሙዚቃዎች

በዚህ ሳምንትም የአብዱ ኪያር ተደማጭነትን ማንም ሊቀድመው አልቻለም፣ የሰላማዊት ዮሐንስ አዲስ ሙዚቃ ተደማጭነቱ ከአብዱ ኪያር ቀጥሎ እንደተጠበቀ ነው። የዜናዊ ኃ/ማርያም እና የእስጢፋኖስ ቶማስ አዲስ ሙዚቃዎች በዚህ ሳምንት የደረጃ ሰንጠረዡን የተቀላቀሉ አዲስ ሙዚቃዎች ናቸው።

1ኛ🔸አብዱ ኪያር (ገለመሌ) 🎶 662,158 እይታ
2ኛ🔸ሰላማዊት ዮሐንስ (ሰንቢደ) 🎶 466,042 እይታ
3ኛ ዜናዊ ኃ/ማርያም (ሓደ ሓደ) 🎶 446,676 እይታ
4ኛ እስጢፋኖስ ቶማስ (እኔን ብሎ አኩራፊ) 🎶 439,686 እይታ
5ኛ🔸አብዱ ኪያር (ቡቡዬ) 🎶 423,810 እይታ
6ኛ🔸አብዱ ኪያር (አይዞን) 🎶 316,048 እይታ
7ኛ🔻አንዱዓለም ጎሳ (ቢሊሌ) 🎶 303,614 እይታ
8ኛ🔻ሙሉዓለም ታከለ (የት ነሽ) 🎶 293,645 እይታ
9ኛ🔻ቬሮኒካ አዳነ (እናነይ) 🎶 274,932 እይታ
10ኛ🔻ናሆም መኩሪያ (ባዳ ባዳ) 🎶 258,718 እይታ

ደረጃ ያሻሻሉ
🔻 ደረጃ የቀነሱ
🔸ባሉበት ደረጃ የቆዩ

🎶 በሳምንቱ ውስጥ በኢትዮጵያዊያን በዩቲዩብ በብዛት የታዩ ሙዚቃዎችን በትክክለኛ ዳታ ላይ ተመርኩዞ የቀረበ ምርጥ አስር ሙዚቃ ሰንጠረዥ ነው።

🎶 ቁጥሮች በሳምንት ውስጥ የጨመሩትን እይታ ብቻ ነው የሚያሳየው።

አርብ ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ተወዳጁ ድምፃዊ እዮብ መኮንን ህይወቱ ያለፈበት 11ኛ ዓመት በአድናቂዎቹ በተለያዩ ዝግጅቶች እየታሰበ ነው:

እዮብን በጥቂቱ

👉ገና በማለዳው የዕድሜ ዘመን ይህቺን ዓለም ከተሰናበቱ ተወዳጅ ድምፃውያን መካከል ለኢትዮጵያ የሬጌ ሙዚቃ ከፍታ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው ተወዳጁ ድምፃዊ እዮብ መኮንን ተጠቃሽ ነው።

👉ይህ ተወዳጅ የሙዚቃ ሰው በሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ ከተማ ጭናቅሰን ገብርኤል እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ተወልዶ እንዳደገ ግለ ታሪኩ ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን።

👉ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስም የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ተወልዶ ባደገባት ጅግጅጋ ውስጥ በሚገኘው "ጅግጅጋ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በከፊል ሊከታተል ችሏል።

👉በወላጅ አባቱ መኮንን ዘውዴ የስራ ባህሪ ምክንያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ወደ አስመራ አቅንቶ ተከታትሏል።

👉የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እየተከታተለ ልቡ ወደ መዚቃው ያጋደለው እዮብ መኮንን የሙዚቃ ፍቅር የገባቸው እና ሙዚቃን ይሰሩ ከነበሩ ልጆች ጋር መለማመድ መቻሉ ይበልጥ ስኬታማ እንዲሆን አድርጎታል።

👉ሙዚቃን ሲጀምርም የቦብ ማርሊን እና የክቡር ዶ/ር አሊ ቢራን ስራዎች በመጫወት ድምፁን ማሟሸት ችሏል።

👉በእዚያን ወቅት ላይ ከሙዚቃ ስራ ልምምዱ በተጨማሪ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ፎቶ ያነሳ ነበር።

👉ያነሳቸውን ፎቶግራፎች ለማሳጠብ ሐረር በምሄድበት ጊዜ ናሽናል የተባለ ሆቴል እየተጋበዝኩ ይዘፍን እንደነበር የድምፃዊው ግለ ታሪክ ያስታውሰናል።

👉ወደ አዲስ አበባ ገብቶ ሙዚቃን በከፍታ መጫወት ህልሙ የነበረው ድምፃዊ እዮብ መኮንን 1991 ዓ.ም ይህ ህልሙ ተሳክቶ በእነ ድምፃዊ አሸናፊ ከበደ አማካይነት ወደ አዲስ አበባ መምጣት ችሏል።

👉አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ ፋልከን ክለብ ውስጥ ገብቶ መጫወት የጀመረ ሲሆን በወቅቱ ከአማርኛ በተጨሜሪ ሱማሊኛ፣ ኦሮሚኛው እና እንግሊዝኛዎን በስፋት ይጫወት ነበር።

👉ከእዚህ ጉዞው በኋላ ከተወዳጁ የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ ጋር ተገናኝቶ 'እንደ ቃል' የሚል መጠሪያ የሰጠውን አልበሙን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ማድረስ ችሎ ነበር።

👉አልበሙ ለሙዚቃ አፍቃሪያን በደረሰበት የመጀመሪያ ወቅት ደብዛዛ ቢመስልም በጊዜ ሂደት በስፋት መደመጥ መቻሉ ተከትሎ ዛሬም ድረስ በልዩነት የሚጠቀስ በትልቅነቱ የሚወደስ አልበም እንደሆነ በርካቶች ይመሰክሩለታል።

👉ይህ ተወዳጅ ድምፃዊ ያለውን አቅም ያክል ሳይጠገብ በ2005 ነሃሴ 7 ቀን ሳይታሰብ በድንገት በስትሮክ ህመም ከቤቱ ደጃፍ ላይ ወድቆ ይገኛል።

👉በወቅቱ በሁኔታው የተደናገጡት እና ያዘኑት የድምፃዊው የሙያ አጋሮች፣ አድናቂዎቹ እና ወዳጆቹ ጤናው መሻሻል እንዲያመጣ ለማድረግ ርብርብ ቢያደርጉም ያ ሳይሆን ቀረና የሰላሳዎቹ የዕድሜ መቋጫ ሳይሻገር ቀረ።

👉በስተመጨረሻም ህይወቱን ማትረፍ ሳይቻል በመቅረቱ ነሃሴ 12 2005 ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

👉የእርሱ ህልፈተ- ሕይወት ከተሰማ ከ4 ዓመታት በኋላ ማለትም በህይወት እያለ ጀምሮት የነበረው አልበም ' እሮጣለሁ ' የተሰኘ መጠሪያ ተሰጥቶ ሊደመጥም ችሏል።

👉ይህ ተወዳጅ ድምፃዊና "የኢትዮጵያ ሬጌ ሙዚቃ ንጉስ" ተብሎ እስከመወደስ የደረሰውን አቀንቃኙን እዮብ መኮንን ከእዚህ ዓለም በሞት የመለየቱ ዜና የተሰማው 11 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ነበር::

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Eyob_mekonen
#ይመልሱ_ይሸለሙ

የትናንት ወዲያው ጥያቄዉን ከመለሱት ዉስጥ የ 100ካርድ ተሸላሚዎች

1, Beharadin Jemal
2, Abdurahman Nuri
3, Ethio First Ethio

ሲሆኑ አሸናፊዎቹም ስልክ ቁጥራችሁን ኢንቦክስ በማረግ ሽልማታችሁን መውሰድ ትችላላችሁ።

👉 በየሳምንቱ ጥያቄ በመመለስ ይሸለሙ!!!

እስከዛ የዩቲዩብ ገፃችንን ሰብስክራይብ በማረግ ይሸለሙ።

Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt

@waliyaentmt