ተወዳጁ ድምፃዊ እዮብ መኮንን ህይወቱ ያለፈበት 11ኛ ዓመት በአድናቂዎቹ በተለያዩ ዝግጅቶች እየታሰበ ነው:
እዮብን በጥቂቱ
👉ገና በማለዳው የዕድሜ ዘመን ይህቺን ዓለም ከተሰናበቱ ተወዳጅ ድምፃውያን መካከል ለኢትዮጵያ የሬጌ ሙዚቃ ከፍታ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው ተወዳጁ ድምፃዊ እዮብ መኮንን ተጠቃሽ ነው።
👉ይህ ተወዳጅ የሙዚቃ ሰው በሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ ከተማ ጭናቅሰን ገብርኤል እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ተወልዶ እንዳደገ ግለ ታሪኩ ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን።
👉ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስም የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ተወልዶ ባደገባት ጅግጅጋ ውስጥ በሚገኘው "ጅግጅጋ አንደኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በከፊል ሊከታተል ችሏል።
👉በወላጅ አባቱ መኮንን ዘውዴ የስራ ባህሪ ምክንያት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ወደ አስመራ አቅንቶ ተከታትሏል።
👉የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን እየተከታተለ ልቡ ወደ መዚቃው ያጋደለው እዮብ መኮንን የሙዚቃ ፍቅር የገባቸው እና ሙዚቃን ይሰሩ ከነበሩ ልጆች ጋር መለማመድ መቻሉ ይበልጥ ስኬታማ እንዲሆን አድርጎታል።
👉ሙዚቃን ሲጀምርም የቦብ ማርሊን እና የክቡር ዶ/ር አሊ ቢራን ስራዎች በመጫወት ድምፁን ማሟሸት ችሏል።
👉በእዚያን ወቅት ላይ ከሙዚቃ ስራ ልምምዱ በተጨማሪ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወረ ፎቶ ያነሳ ነበር።
👉ያነሳቸውን ፎቶግራፎች ለማሳጠብ ሐረር በምሄድበት ጊዜ ናሽናል የተባለ ሆቴል እየተጋበዝኩ ይዘፍን እንደነበር የድምፃዊው ግለ ታሪክ ያስታውሰናል።
👉ወደ አዲስ አበባ ገብቶ ሙዚቃን በከፍታ መጫወት ህልሙ የነበረው ድምፃዊ እዮብ መኮንን 1991 ዓ.ም ይህ ህልሙ ተሳክቶ በእነ ድምፃዊ አሸናፊ ከበደ አማካይነት ወደ አዲስ አበባ መምጣት ችሏል።
👉አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ ፋልከን ክለብ ውስጥ ገብቶ መጫወት የጀመረ ሲሆን በወቅቱ ከአማርኛ በተጨሜሪ ሱማሊኛ፣ ኦሮሚኛው እና እንግሊዝኛዎን በስፋት ይጫወት ነበር።
👉ከእዚህ ጉዞው በኋላ ከተወዳጁ የሙዚቃ ሰው ኤልያስ መልካ ጋር ተገናኝቶ 'እንደ ቃል' የሚል መጠሪያ የሰጠውን አልበሙን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ማድረስ ችሎ ነበር።
👉አልበሙ ለሙዚቃ አፍቃሪያን በደረሰበት የመጀመሪያ ወቅት ደብዛዛ ቢመስልም በጊዜ ሂደት በስፋት መደመጥ መቻሉ ተከትሎ ዛሬም ድረስ በልዩነት የሚጠቀስ በትልቅነቱ የሚወደስ አልበም እንደሆነ በርካቶች ይመሰክሩለታል።
👉ይህ ተወዳጅ ድምፃዊ ያለውን አቅም ያክል ሳይጠገብ በ2005 ነሃሴ 7 ቀን ሳይታሰብ በድንገት በስትሮክ ህመም ከቤቱ ደጃፍ ላይ ወድቆ ይገኛል።
👉በወቅቱ በሁኔታው የተደናገጡት እና ያዘኑት የድምፃዊው የሙያ አጋሮች፣ አድናቂዎቹ እና ወዳጆቹ ጤናው መሻሻል እንዲያመጣ ለማድረግ ርብርብ ቢያደርጉም ያ ሳይሆን ቀረና የሰላሳዎቹ የዕድሜ መቋጫ ሳይሻገር ቀረ።
👉በስተመጨረሻም ህይወቱን ማትረፍ ሳይቻል በመቅረቱ ነሃሴ 12 2005 ላይ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
👉የእርሱ ህልፈተ- ሕይወት ከተሰማ ከ4 ዓመታት በኋላ ማለትም በህይወት እያለ ጀምሮት የነበረው አልበም ' እሮጣለሁ ' የተሰኘ መጠሪያ ተሰጥቶ ሊደመጥም ችሏል።
👉ይህ ተወዳጅ ድምፃዊና "የኢትዮጵያ ሬጌ ሙዚቃ ንጉስ" ተብሎ እስከመወደስ የደረሰውን አቀንቃኙን እዮብ መኮንን ከእዚህ ዓለም በሞት የመለየቱ ዜና የተሰማው 11 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ነበር::
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Eyob_mekonen