ዶክተር ድሬ በኦሊምፒክ ለመወዳደር እንደሚፈልግ አስታወቀ
የ59 ዓመቱ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ድምፃዊና ገጣሚ ዶክተር ድሬ “ኢንተርቴይንመንት ቱናይት” በተባለ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ ቀርቦ “በ2028 ኦሊምፒክ ላይ ለመሳተፍ እየሞከርኩ ነው፤ የምሬን ነው፤ የቀስት ኢላማ ውድድርን ከመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮ እወዳደር ነበር” ብሏል።
ዶክተር ድሬ ወይንም በመዝገብ ስሙ አንድሬ ሮሜል ያንግ “አሁን በግቢዬ ውስጥ መለማመጃ አዘጋጅቻለሁ፤ በኦሊምፒክ ለመሳተፍ በ77 ጫማ ርቀት ብቁ መሆን እንደሚጠይቅ ሰምቻለሁ፤ ሆኖም እኔ በ90 ጫማ ርቀት እየተለማመድኩ ነው” በማለት ለጉዳዩ ትኩረት እንደሰጠው ገልጿል።
የ2028 ኦሊምፒክ አዘጋጇ ደግሞ የዶክተር ድሬ መኖሪያዋ ሎስ አንጀለስ ከተማ መሆኗ ደግሞ ዝነኛው የሙዚቃ ባለሙያ በውድድሩ የመሳተፉ ውሳኔ አይቀሬ ይመስላል።
ዶክተር ድሬ ዴዝሮው ሪኮርድስ የተባለ የሙዚቃ ስቱዲዮ እና ቢትስ ኤሌክትሮኒክስ የተባለ ኩባንያ ባለቤት ሲሆን ለቱፓክ፣ ስኑፕ ዶግ፣ ኤምነም፣ 50 ሴንት፣ ቲአይና ሜሪ ጄ ብላይጅ ለመሳሰሉ ታላላቅ ራፐሮች ሙዚቃ አዘጋጅቷል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #dr_dre