የተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የመጨረሻ አልበሙ ከምን ደረሰ?
ብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እና አድናቆትን ያተረፈው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የመጨረሻ አልበሙን እየሰራ በሚገኝበት ሰአት ላይ በህመም ምክንያት ማረፉ ቢታወቅም አጅናቂዎቹና የሙያ አጋሮቹ አልበሙን ከጥግ ሊያደርሱት ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው። ነገር ግን የድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ እህት የሆነችው ድምፃዊ ትግስት አፈወርቅ ለታዲያስ አዲስ እንደገለፀችው የዜማ እና የግጥም ደራሲ የሆነው ዘላለም መኩሪያ ማዲንጎ በድምፅ ሙሉ በሙሉ ገብቶ ያልጨረሰውን ስራ ከማዲንጎ ድምፅ ጋር የሚመሳሰል አንድ ድምፃዊ ድምፁን በመቅዳት የማዲንጎ ስራ አስመስሎ ለመሸጥ እየሰራ እንደሆነ ቤተሰቦቹ በጭራሽ ይሄን ነገር እንደማይቀበሉትም ተናግራለች።
አልበሙን በዋናነት እየሰሩ የሚገኙት ኢንጅነር ፋንታ ወጨፎ እና ዘላለም መኩሪያ ሲሆኑ ለዚህ ጥያቄ ዘላለም መኩሪያ ስራችውን የጀመሩት በየስቱዲዬው ያሉትን ስራዎች በማሰባሰብ ሲሆን ስራዎቹ አሁን ላይ ያሉት የመለማመጃ ወይም Sample ብቻ እንደሆኑ ሌሎች ድምፃዊያንንም የማስገባቱ ስራ ለሙከራ ያህል የተደረገ እሱንም በሃሳብ ደረጃ የተተወ መሆኑን ገልጿል።
አያይዞም አሁን አልበሙ የማሰባሰብ የመምረጥ እና እንዴት አድርጎ የመለማመጃ ድምፁን ወደ አሪፍ ሙዚቃ መቀየር ይቻላል የሚለውን ገና የማሰብ ደረጃ ላይ እንደሆነ የሚወጣበትም ቀን ያልተወሰነ መሆኑን ገልፀዋል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Madingo_afewerk