Waliya Entertainment
291 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
"ዱርዬ ተሰብሰብ "

ከአመታት በፊት ተ/ሀይማኖት ፊትለፊት ያለው አንበሳ ጫማ መደብር ያለበት ህንጻ ሰፊ በረንዳ የጎዳና ተዳዳሪዎች መናሀሪያ ነበር ። እና እዚህ ቦታ ፌስታል ሙሉ ክትፎ ይዞ የሚመጣ አንድ ሰው ነበር ፨

ይህ ሰው ኬኔዲ መንገሻ ነው ፡፡ ኬኔዲ አንዳንዴ ነሸጥ ሲያደርገው ወደዛ ይሄድና ዱርዬ ተሰብሰብ እያለ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ሰብስቦ በጊዜው ተ/ሀይማኖት ሱማሌ ተራ አካባቢ ዝነኛ ከነበረው ግዛው ክትፎ ቤት ገዝቶ ያመጣውን ክትፎ አብሯቸው እየተሻማ ይበላና ለያንዳንዳቸው የሻይ ሰጥቶ በብርቱካንማ ሬኖ መኪናው ይሄዳል ።
.......
አስገራሚው ነገር ኬኔዲ የትኛውም ታዋቂ ሰው የማያደርገውን ይህን መሳይ ነገር ሲያደርግ. .. በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ዝነኛ ከነበሩ አርቲስቶች መሀከል አንዱ ነው ። ሆኖም ዝናው አንድም ቀን ትከሻውን አጉብጦት አያውቅም ።
.......
አንድም ቀን በኩራት ልቡ ሳያብጥ ፡ አንድም ቀን ላይ ሆኖ አድናቂዎቹን ቁልቁል ሳያይ ፡ እንደጠዋት ፀሀይ ብልጭ ብሎ አፍታም ሳይቆይ ይህችን ምድር ተሰናብቶ ሄደ ።
RIP
የሰውነት ጥግ ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ከኤሮስፔስ ወደ ሙዚቃ !

ሙላቱ አስታጥቄ ለትምህርት ወደ አውሮፓ ሲያመራ እድሜው 20 እንኳን አልሞላውም ። ከጥሩ ቤተሰብ ነው የተገኘው የሀብታም ልጅ ነበር ማለት እንችላለን ። በጥሩ ኢትዮጵያዊ ባህል እና ስነልቦና ያደገ ።
በ16 አመቱ በዌልስ ኤሮ ስፔስ ኢንጂነሪንግ ማጥናት ጀመረ ። የሚማርበት ዩንቨርስቲ ተማሪዎቹ ከመደበኛ ትምህርታቸው በተጨማሪ ሌሎች ትምህርቶችን በትርፍ ጊዜያቸው እንዲማሩ ያበረታታል ።
እናም ወጣቱ ሙላቱ አስታጥቄ ሙዚቃን ማጥናት ጀመረ ። እንድያውም ከነአካቴው ስለጠፈር ምርምር ትምህረት ይቅርብኝ ብሎ ሙሉ ለሙሉ ሙዚቃው ላይ አተኮረ ። ወደ ለንደን አምርቶ በትሪኒቲ ኮሌጅ ሙዚቃን አጠና ። ከዛም ለንደን ላይ በጃዝ ሙዚቃዎች መሳተፍ ሲጀምር ቀጠል አድርጎም ሙዚቃዎችን ማጥናት ተያያዘ ። አሰብ አድርጎ ደግሞ የኢትዮጵያን ሙዚቃ በአለም አቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ እንደሚቻል ያምናል እናም በትምህርት ልቆ ለመገኘት ወደ አሜሪካ ተጉዞ በቦስተን በርክሌ ሚዩዚክ ኮሌጅ በመማር የመጀመሪያው አፍሪካዊ ሆነ ።

በ60ዎቹ ከላቲኖች ጋር በመሆን ''Afro Latin jazz'' ቁጥር 1እና 2 በአሜሪካ ሀገር ሰራ ።
በ1969 እኤአ ላይ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ እጅግ ተወዳጅነትን ያገኘበትን ስራ አጥንቶ ጨርሶ 1972 እኤአ ላይ አሜሪካን ሀገር በማምራት አስቀረፀ። ይህ ስራ የላቲን ፣የአፍረካ ፣ፈንክ እና ሌሎችንም አለም አቀፍ ሙዚቃዎች ስልት አዋህዶ የተቀናበረ ኢትዮ ጃዝ ሙዚቃ ነው ። ''ሙላቱ ኢትዮጵያ '' የተሰኘ ኢትዮ ጃዝ አልቀም ተሰርቶ እጅግ ተወዳጅነትን አገኘ ።

ይህ ስራ ከተለቀቀ የፊታችን ሰኞ 52ኛ አመቱን ይያዛል ።

Follow us on
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
3ኛው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 22/2016 (አዲስ ዋልታ) የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ የህልፈት ቀንን ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጀው ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ለ3ኛ ጊዜ በስካይ ላይት ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በ11 ዘርፍ ድምፃዊያንን እጩ ያደረገው ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ የምርጫ ሂደቱ የህዝብ እና የዳኞችን ምርጫ ያማከለ ነው ተብሏል።

አርቲስቱ በህይወት በነበረበት ጊዜ የአፋን ኦሮሞ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ላይ ትልቅ አሻራ ያለውና ግጥምን ከዜማ አዋህዶ በርካታ ጉዳዮችን እያነሳ ያቀነቀነ ወጣት አርቲስት ነበር፡ በስራዎቹም በርካታ ነጠላ ዜማ እና አልበሞችን ለህዝብ አድርሷል።

የአርቲስቱን ህልምና ራዕይ ከግብ ለማድረስ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ተቋቁሞ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በዚህም በአርቲስቱ ስም በየበጎ አድራጎት ስራ እና ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድን ጨምሮ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

በዛሬው እለት የተዘጋጀው መርኃ ግብርም የአርቲስቱን 4ኛ ዓመት መታሰቢያ እና 3ኛ ዙር ሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ ምክንያት በማድረግ ነው።

በመርኃ ግብሩ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ አርቲስቶች፣ የአርቲስቱ ቤተሰብና አድናቂዎች ተገኝተዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music